ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing ግጥሞች. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 11-03-17, 06:05 am


Karma: 90
Posts: 610/840
Since: 02-29-16

Last post: 30 days
Last view: 30 days
"ጊዜ በሚዛኑ"
የታሪክ ሂደቱ የአኗኗሩ ዘይቤ
የሰው ልጅ እይታ ስብእና እሳቤ
በጊዜ ተለይተው ሲታይ በፈረቃ
ህይወት ስትታዘብ ከሁሉም ነገር ልቃ
ኑሮ ጉራማይሌ እንደየዘመኑ
ሁሉን ያሳየናል ጊዜ በሚዛኑ።
እንደዚህ ናት ህይወት አታላይ ናት አለም
ካየነው ባለፈ የምናየው የለም
ጊዜ አሳፋሪ ዘመን ተሻጋሪ
የምኞትን አለም በተግባር መስካሪ
ትላንትን በችግር እንዲሁም በማጣት
ዛሬን በጥጋብ ደርሶ በመቀናጣት
ለአጭር ህይወት እርቃንን መመኘት
ስናየው አይግረመን ገጥሞን በህይወት ሂደት
አታላይ ናት አለም እንደዚህ ናት ህይወት፡፡
===== ===== =========
በሀሩ ሙዜ 12/02/10

Pages: 1