ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing ግጥሞች. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 11-03-17, 05:57 am


Karma: 90
Posts: 608/838
Since: 02-29-16

Last post: 34 days
Last view: 34 days
"እልፍ ትዝታ"
ያኔ በአፍላ ፍቅራችን
ሃሳብ ሳይዛነፍ መራራቅ ሳይመጣ
አያውቀው ልባችን የፍቅርንም ጣጣ፡፡
ጎዳናው ይመስከር
አንድ አምሳል በመሆን የተራመድንበት
ጨረቃም ትመስክር
በደስታ የሸኘነውን የፍቅራችንን ሌሊት
ጸሃይዋም ትመስከር የቀን እማኝ ሆና
ንጹህ እንደነበረ የልባችን ገመና
ምሽቱም ይመስክር በጠቆረ ሰማይ
ስለ ፍቅር ስንቆም ጨፍነን እንደምናይ
በጋውም ይመስክር በሞቃት አየሩ
ፍቅርሽ እንደነበር ለልቤ ክብሩ
ክረምቱም ቃሉን ይስጥ ሰማዩ ጨፍግጎ
ስለ ፍቅርሽ ልቤ ወዳንቺ አርጎ
ከልብሽ መሽጎ
ማደሩስ መች ጠፍቶሽ
አጉል ቀን ቀልብ ነስቶሽ
የመሰከረው ቀን በስህተት አድልጦሽ
ብትወድቂም ለቃልሽ
ሁሌም ያወሳሻል እልፍ ትዝታዬ
የፍቅርን መከራ በክፉ እጣዬ
ስዳስስ ቆይና በቀዘቀዘ ልቤ
ይዞኝ ሽው እንዳለ ያለፈ ሃሳቤ
ተው እንጂ ጃል ልቤ በዛሬ ተጠራ
ከግራህ ጎድንህ ሌላ ሄዋን ስራ
አላየህም እንጂ ያንተዋ ሄዋንም አለች የሆነ ስፍራ
ልብህን አታጥቁር ፈልጋት ሳትፈራ
ብሎ እንደመራኝ ደርስኩ ካንቺ ጋራ
የህልሜ አደራ
እልፍ ትዝታዬ አንቺን ብሎ ይፍራ፡፡
===== ===== =======
በሀሩ ሙዜ በ 14/02/10

Pages: 1