ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 3 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 10-30-17, 07:49 am


Karma: 90
Posts: 605/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
ሁለት ሴቶች ኣንድን ወንድ በFacebook ይተዋወቁና ከረዥም ጊዜ ቡኃለ ለመገናኘት ቀጠሮ ይይዛሉ። ታድያ ይህ ሰው ውጭ ኣገር ይኖር ስለነበር ሁለቱም ሴቶች ምንም እንኳን ጏደኛሞች ቢሆኑም የጥቅም ነገር ነውና ለኔ ነው ለኔ ነው እያሉ መጣላት ይጀምራሉ። ሰውየውም ሁለቱንም ባንዴ ቀጥሮ ወደሱ እንድሄዱ ያደርጋል። ሴቶቹ ታድያ ሁለቱም ብሃሪያቸው እጅግ የተለያየ ነበር። ኣንደኛዋ መልካምና ከኣፏ የእግዚአብሔር ቃል የማይጠፋ ጥሩ እምትባል ኣይነት ናት። ኣንደኛዋ ደግሞ በተቃራኒው ችኩልና እራስ ወዳድነት የሚያጠቃት ኣይነት ሴት ናት። ይህ ሰው ወደቀጠራቸው ቦታ ተያይዘው ሲደርሱ ግን የጠበቃቸው ነገር ኣስንጋጭ ሆነ።ያ ለኔ ለኔ ሲሉት የነበረው ሰው ኣካል ጉዳተኛ ሆኖ ኣገኙት። ዊልቸር ላይ ተቀምጦ "እንኳን ደህና መጣችሁ" ብሎ ደስ በሚል ፈገግታ ቢቀበላቸውም እነሱ ግን ፊታቸው ክስል ብሎ "እንዴት ኣርገን ናምልጥ" እሚል ስሜት ውስጥ ነው የገቡት። እንደምንም ሰላምታ ከተለዋወጡ ቡኃላ "እንግዲህ ይህን ያክል ከተዋወቅን ወደ ዋናው ቁም ነገር እንግባ" ኣላቸውና ብቻ ብቻቸውን ማውራት እንደሚፈልግ ነግሮ ኣንዳቸው ውጭ እንዲቆዩ ጠየቃቸው።ችኩሏ ሴት ፈጠን ኣለችና "እኔ እወጣለሁ ኣውሩ"ብላ ተነስታ ወጣች።ሰውየውም ለመልካሟ ልጅ የጋብቻ ጥያቄ ኣቀረበላት ልጅቷም በጣም በተደናገጠ ስሜት ማውራቷን ቀጠለች። እንዲህም ኣለችው "እስከ ዛሬ ድረስ በፍቅር ክንፍ ብየልህ ነበር፤ዛሬ ሌሊት ግን እግዚአብሔር ተገለጠልኝ፣መንገዴንም እንዳስተካክል ነገረኝ"እያለች ከመፅሐፍ ቅዱስ እያጣቀሰች ብዙ ኣውራች። እሱም ተስፋ ባለመቁረጥ ለማግባባት ሞከረ እሷ ግን "እኔ ኣልሆንህም ሌላ ፈልግ" ኣለችው። እሽ ብሎ "ሌላኛዋን ጥሪልኝ"ኣላት።ችኩሏ ልጅ ግባችና እሚላትን በጥሞና ስታዳምጥ ከቆየች ቡኅላ "ጥያቄህን ተቀብየዋለሁ።ማን ያውቃል ፈጣሪ ይፈውስህ ይሆናል፣እኔ ሙሉ ኣካል ኣለኝ ኣያለሁ፤እሰማለሁ፤እንቀሳቀሳለሁ።ይህ የሆነው ደግሞ በ እግዚአብሔር ፍቃድ ነው።ኣንተም እግዚአብሔር ፈቅዶ ትፈወስ ይሆናል ስለዚህ ኣገባሃለሁ"ኣለችው። ደስ ብሎት "በቃ እሽ ጏደኛሽን እንሸኛት" ብሎ በዊልቸር እየተገፋ ወደ ውጭ ወጣ። ያቺ መልካም ኣንደበት ያላትና ልቧ ግን የጎደፈ ሴት ለመሄድ እጅግ ቸኩላለች። ችኩሏና ልታገባው የወሰነችው ሴት እየገፋች መልካም መሳይዋ ልጅጋ ደረሱ።እንዲህም ኣላት "በ እግዚአብሔር ቃል ተሞልተሻል።ግን ተግባርሽ እንደ ንግግርሽ ኣደለም።ይሄን እውቀትሽን ተጠቀሚበት"።ኣላትና ልታገባው ወደወሰነችው ሴትም ዘወር በማለት "ኣንቺን ደግሞ ሰርፕራይዝ ኣረግሻለሁ"።ካለ ቡኅላ ከተቀመጠበት ሳይክል ብድግ ብሎ በመቆም ምንም ኣይነት የጤና ችግር እንደሌለበት ኣሳያቸው። ኣስመሳይዋም በህፍረት ኣንገቷን ደፍታ "መልካም ጋብቻ ያርግላችሁ"።ብላ ውልቅ ኣለች።
Pages: 1