ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 10-26-17, 08:09 am (rev. 2 by ጮሌው on 10-26-17, 08:10 am)


Karma: 100
Posts: 432/760
Since: 03-20-17

Last post: 15 days
Last view: 15 hours
ሚስቴ ጋር የነበረን አመታዊ የሂስ ግለሂስ
መድረክ።
- - - - -
ትናንትና ማታ ከሚስቴ ጋር የበጀት አመቱን
ግምገማ በተሳካ
ሁኔታ አስኬድን። ይሄን መልካም ተሞክሮም ቀምሬ
ለእናንተ
እንዳጋራችሁ ቅንነቴ ተጠናወተኝ። ያው ሻወርና
ግምገማ ከራስ
ሲጀምር ነውና መልካም-ትዳር የሚሰፍነው ብዬ
በቅድሚያ
ራሴን አስቀደምኩ።ቀጥለንም የመገምገሚያ ነጥቦችን አወጣንና
የእኔን ግምገማ
እሷ ቃለጉባኤ እንድትይዝ ተስማምተን
ግምገማው ተጀመረ።
«የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጭ ይታይብሀል!»
አለችኝ ቃለ
ጉባኤው ላይ እስክርቢቶዋን አመቻችታ።
ሲያዩዋት ቃል
የምትቀበል የፍ/ቤት ዳኛ እንጅ አብራኝ የኖረች
የትዳር አጋሬን
አልመስልህ አለችኝ። (ምን የትዳር አጋር ይችማ
የውሀ አጋር
ናት እንጅ)
~
ድንጋጤዬን በደረቁ ዋጥ አድርጌ እሷ ሳታውቅ
የጋራ
ሀብታችንን ያለ አግባብ የመዘበርኩትን፤ በአንድ
የራት ግብዣ
ለትርሲት ብራስሌት የሸለምኳትን፤ ለቤቲ ልደት
ሀብል
የገዛሁላትን... ይሄን ሁሉ ጉዴን እንዴት ደረሰችበት
እያልኩ
ወሽመጤ ቁርጥ ብሎ (የኔና የሀገሪቱ ወሽመጥ
ያልተቆረጠ
ይመስል።) <ማሳያ!> አልኩ እንደ የሌባ አይነደረቅ
ፍጥጥ
ብዬ።
~
«ለትዳር ጊዜ አትሰጥም! ስትበላም ስትጠጣም
ተኝተንም
የስራ ሰአትህን (አልጋ ላይ) ሁሉ ጊዜህን
የምታሳልፈው
ፌስቡክህ ላይ አንዳፈጠጥክ ነው። ሰዓት
ትሸራርፋለህ! የምሽት
ሰዓት እላፊ አዋጁን ትጥሳለህ! ይሄ ደሞ ጊዜን
በአግባቡ
ያለመጠቀም የሚያሳየው ለመልካም ትዳራችን
ሰላም መስፈን
ግዴለሽነትንና ለትዳር ጓድህ ያለህን ቸለልተኝነት
ነው!»
~
ሁፍፍፍ... ደሮ ብታልም ጥሬዋን አሉ፤ ከያዘኝ
የአሸባሪነት
ተግባር ተላቀቅሁና ከዚህ ሞያሌ የሚደርስ
በረጅሙ ተነፈስኩ።
~
እስኪ በዚህ ይለፍ አልኩና <ያው
የውጭ ዲፕሎማሲያችንን ለማጠናከር ብዬ እንጅ
ይሄን ያክል
ችግር ካለው አስተካክላለሁ።> ብዬ
አቀረቀርኩ። «በል ለራስህ ደረጃ
አስቀምጥ!» አለችኝ። ለራስ
ሲቆርሱ አያሳንሱ ነውና <ያው
ያሉብኝ ክፍተቶች ትንሽ ስለሆኑ
አስተካክላለሁ ከፍተኛ ይሰጠኝ።>
አልኩ አሁንም እንዳቀረቀርኩ።
~
«ዌል ጓዱ ለጊዜው መካከለኛ ላይ
ሆነህ ያሉብህን ችግሮች ለወደፊቱ
እንድታስተካክልና በድርጅታዊ
ቁርጠኝነት ተግባራትን እንድትወጣ ተወስኗል።»
አለችኝ ችሎት
ይሁን የትዳር ጓዶች ግምገማ በውል
በማይታወቅበት ሁኔታ።
(ቆይ አገኝሻለሁ አልኩ ለራሴ።)
~
ውሳኔውንና ቃለጉባኤውን ተቀብዬ በተራዬ እኔው
አሯሩጣት
ጀመርኩ።<1ኛ፦ ፀረ-ሰላም የሆኑ ሀይሎች
ጋር ትተባበሪያለሽ! የመንደራችን
ሴቶች ደግሞ ሀገ-መንግስታችንን
ለመናድና ትዳራችንን መቀመቅ
ለመክተት የሚጥሩ ሀይሎች
መሆናቸውን ታውቂያለሽ!
~
2ኛ፦ የሀይማኖት አክራሪነት ፅንፍ
ይታይብሻል! ሳይነጋ ተነስተሽ
ቤተስኪያን ነው! ሲመሽ ቤተስኪያን ነው! ቤት
ውስጥ ወሬሽ
ሁሉ ሀይማኖታዊ ነው!

...ማስታወሻ እየያዝሽ! ለነገሩ እኔም እየፃፍኩት
ነው።3ኛ፦ ሀብትን በአግባቡ
ያለመጠቀምና ድርጅታዊ ሀላፊነትና ትኩረት ማነስ
ይታይብሻል! የቤት አስቤዛ ታባክኛለሽ!
~
4ኛ፦
5ኛ፦
.
.
አላስተረፍኳትም! በመጨረሻም
የማስጠንቀቂያ የፅሁፍ ደብዳቤ ጋር ዝቅተኛ ደረጃ
ሰጥቼ
ቃለጉባኤው ላይ ተፈራረምን። ዳሩ ምን ያረጋል
ጀርባችንን
ተሰጣጠን አደርን እንጅ።
Pages: 1