ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 10-22-17, 03:14 am


Karma: 100
Posts: 420/760
Since: 03-20-17

Last post: 15 days
Last view: 15 hours
ልማዳዊ/ባህላዊ ጋብቻ በኢትዩጵያ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም ልማዳዊው ጋብቻ ህጋዊ ውጤት ይኖረው ዘንድ ግን በክፍለ ከተማው የጋብቻና ክብር መዝገብ ምዝገባ ቢሮ ውስጥ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ ባልና ሚስት በልማዳዊ ጋብቻ ከተጋቡ በኋላ ህጋዊ በሆነው የጋብቻና ክብር መዝገብ ላይ በፈለጋቸው ጊዜ ጋብቻቸውን ማስመዝገብ የሚችሉ ቢሆንም በግዜ ማስመዝገቡ ግን ይመከራል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ባልና ሚስቱ ለምዝገባ በሚሄዱበት ጊዜ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነሱም
1. የባህላዊው/ልማዳዊው ጋብቻ ውል ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ፣
2. በባልም ሆነ በሚስት ወገን የሚመጡ ሁለት ሁለት ምስክሮች፡፡ እነዚህ ምስክሮች የነዋሪነት መታወቂያቸው ዋናውንና አንድ አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
3. የባልና ሚሰቱ መታወቂያ ሲባል መታወቂያቸው ጊዜው ያለፈበት ሳይሆን የታደስ መሆን አለበት፣
4. ባልና ሚስቱ ነዋሪነታቸው ጋብቻው በሚመዘገብበት ክፍለ ከተማ መሆን ያለበት ሲሆን አሊያም ደግሞ ጋብቻቸውን ማስመዝገብ የሚችሉት ባልየው ወይም ሚስትየው ወይም ከሁለቱ አንዳቸው በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ መሆን አለበት፣
5. የባል እንዲሁም የሚስት ፓስፖርት ሳይዝ ሦስት ሦስት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
6. ከላይ በተራ ቁጥር ሁለት ላይ የጠቀስናቸው ምስክሮች ግዴታ ጋብቻው ሲፈፀም የነበሩ /የተገኙ/ መሆን አይጠበቅባቸውም፡፡ ማንኛውም እድሜው 18/አስራ ስምንት/ አመት የሞላና ባልና ሚስቱን በደንብ የሚያውቅ እንዲሁም ስለ ጋብቻቸው በደንብ ሊያስረዳ የሚችል ሰው ምስክር መሆን ይችላል፡፡

Pages: 1