ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Taxes. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 10-21-17, 03:09 pm


Karma: 90
Posts: 595/887
Since: 02-29-16

Last post: 206 days
Last view: 206 days
ተርን ኦቨር ታክስ ምንድነው?

ተርን ኦቨር ታክስ በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት የሚጣል የታክስ አይነት ነው፡፡

ተርን ኦቨር ታክስን ሰብስቦ ገቢ የማድረግ ግዴታ የማነው?

ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገበ ወይም ዓመታዊ የንግድ አንቅስቃሴው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ወይም ድርጅት በአገር ውስጥ ከሚሸጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ ሰብስቦ ለሚመለከተው የታክስ ባለስልጣን ገቢ ያደርጋል፡፡ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶችን የሚሸጥ ማናቸውም ሰው ወይም ድርጅት በሽያጭ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ ከገዥው ሰብስቦ ለታክስ ባለስልጣኑ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ስለሆነም ሻጩ ለታክሱ የመጀመሪያ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

የተርን ኦቨር ታክስ ተመን

በማናቸውም በአገር ውስጥ በሚሸጡ ዕቃዎች ላይ እንስሳትንም ጨምሮ ሁለት በመቶ

በአገር ውስጥ በሚሸጡ በተወሰኑ አገልግሎቶች ላይ ማለትም (የሥራ ተቋራጮች፣ የእህል ወፍጮ ቤቶች፣ የትራክተሮችና ኮምባይነር ሀርቨስተሮች) ሁለት በመቶና

ሌሎች አገልግሎቶች ላይ አስር በመቶ የተርን ኦቨር ታክስ ይከፈላል፡፡

የተርን ኦቨር ታክስ የስሌት መሠረት

ተርን ኦቨር ታክስ የሚሰላበት የዋጋ መሠረት የዕቃው ወይም የአገልግሎት ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ ይሆናል፡፡

የሚከተሉት ከተርን ኦቨር ታክስ ክፍያ ነፃ ናቸው፡­-

ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ መኖሪያ ቤት ሽያጭና የመኖሪያ ቤት ኪራይ፣

የፋይናንስ አገልግሎቶች፣

ለሳንቲሞችና ሜዲሊያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጪ አገር ገንዘቦችና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት፣

በኃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች፣

የሕክምና አገልግሎትና አግባብ ባለው የመንግስት መ/ቤት በሚወጣ መመሪያ መሠረት በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች፣

በትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋዕለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች፣

የኤሌክትሪክ፣ የኪሮሲን የውሃ አቅርቦት፣

የትራንስፖርት አገልግሎት፣

ማናቸውንም የሥራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚሰጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚፈፀም ክፍያ፣

60% እና ከዚያ በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚያቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣

መጽሐፍት፣

ሌሎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሆኑ ሁሉ ናቸው፡፡

የተሰበሰበን የተርን ኦቨር ታክስ ስለማስታወቅ

የደረጃ‹‹ሀ›› ግብር ከፋዮች ተብለው የሚታወቁና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የመመዝገብ ግዴታ የሌለባቸው ታክስ ከፋዮች በየወሩ፣

የደረጃ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በኢትጵያ የበጀት ዓመት ወይም በገቢ ሰብሳቢው መ/ቤት ሲፈቀድ በአውሮፓ ዘመን አቆጣጠር ከዓመቱ የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ የሶስት ወር ጊዜ ባበቃ በቀጣዩ አንድ ወር፣

የደረጃ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች የበጀት ዓመቱ እንዳለቀ /ከሐምሌ 1 – 30/ ነው፡፡

የተሰበሰበን የተርን ኦቨር ታክስ በወቅቱ ያለማስታወቅ አስተዳደራዊ መቀጫዎችን ያስከትላል

በተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ቁጥር 308/1995 መሰረት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የታክስ ማስታወቂያ ግዴታውን ያልተወጣ የተርን ኦቨር ታክስ ከፋይ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ያልተከፈለውን ታክስ 5 በመቶ፤ 25 በመቶ እስኪ ሞላ ድረስ፣

የሚከፈለው መቀጫ ከብር ሃምሳ ሺህ አይበልጥም፣

በማናቸውም ሁኔታ የሚጣለው ቅጣት ቀጥሎ ከተመለከቱት ከዝቅተኛው ያነሰ አይሆንም፣ ብር አስር ሺህ፣ በታክስ ማስታወቂያው ላይ መመልከት ከነበረበት የታክስ መጠን 100% ይሆናል፡፡

የተርን ኦቨር ታክስ ክፍያ ማዘግየት አስተዳደራዊ መቀጫዎችን ያስከትላል

መከፈል በነበረበት ወር ላልተከፈለ ታክስ መከፈል ከነበረበት ቀን ባለጊዜ ውስጥ ታክስ ከፋዩ ወለድ የመክፈል ግዴታ አለበት፣

የሚከፈለው ወለድ የማስከፊያው ልክ ባለፈው የሩብ ዓመት በንግድ ባንኮች ስራ ላይ በዋለው ከፍተኛ የማበደሪያ ወለድ መጣኔ ላይ 25 በመቶ ታክሎበት ነው፡፡

Pages: 1