ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing ግጥሞች. | 2 guests
Pages: 1
Posted on 10-18-17, 06:51 am


Karma: 90
Posts: 586/838
Since: 02-29-16

Last post: 33 days
Last view: 33 days
አንድ የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ፣
እንዲህ ሲል ተጣላ ከብርጭቆው ጋራ።
እኔ ነኝ መብራቱ ብርሃን የምሰጥ፣
ጨለማን አትፍቸ የምገላልጥ።
አንተ ግን እፊቴ እንዲህ ተደንቅረህ፣
ዙሪያየን ከበ ኸ ኝ እንዲህ ተደንቅረህ።
አልገባኝም ከቶ የምትሰራው ስራ፣
ብርሃኔ ሩቅ ደርሶ ደምቆ እንዳያበራ።
ተሠራጭቶ በጣም እንዳይዘረጋ፣
አንተን ፈጠረብኝ መንገድ የምትዘጋ።
እንቅፋት እየሆንህ ስራዬን አታጥፋ፣
ገለል በል ከፊቴ ብርሃኔ ይስፋፋ።
አገልግሎቴማ ከሆንብኝ ጥፋት፣
እውነትማ ላንተ ከሆንኩህ ዕንቅፋት።
ልሂድልህ ብሎ ሲልቅለት ቦታ፣
ከጎን የነፈሰ የነፋስ ሽውታ፣
መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፍታ።
አጭር እየሆነ ተመልካችነቱ፣
መለየት አቅቶት ጥቅሙን ከጉዳቱ።
እወቁኝ እወቁኝ እያለ ሲነሣ፣
ሰውም እንደዚሁ ያመጣል አበሳ።

ምንጭ:
ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)
Pages: 1