ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing ግጥሞች. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 10-17-17, 07:06 pm


Karma: 90
Posts: 584/879
Since: 02-29-16

Last post: 33 days
Last view: 33 days
ስለሷ ከሆነ

(ሚራ)
***
የዘመናት ምኞት የህይወት ውጥኔን
የሴትነት ልኬት የሰው መስፈሪያየን
ይሄው ዕድል ቀንቶኝ ይዣት መጥቻለሁ
የተከፋ ይጥፋ ደስታን አውጄያለሁ።

ቤቴ ቅጥሩ ይስፋ ጥበቃው ይጠንክር
ታዛዥ አጎብዳጁም አንድ ባንድ ይደርደር።

አንዳች ሳትተነፍስ ቃል ሳይወጣ ካፏ
መሻቷን ፈፃሚ ይሙላ በበራፏ።

ጉልበት ሳታባክን ኃይልን ሳታወጣ
ጠላቷን አስለቃሽ ታጣቂ ሰው ይምጣ።

ገና ሳትታመም ጣር ሳይነካው ጎኗን
መዳኗን የሚያውጅ ፈዋሽ ይሙላው ደጇን።

ዕድሜዋ ሲጨምር እርጅና ሲጫናት
እንደገና ወልዶ "ወፌ ቆመች" የሚል ወላጅም ይኑራት።

መንግስታት ሆይ ስሙ
ጠበኞቹም ሁሉ ዛሬ በኛ ጉዳይ አንድዜ ተስማሙ።

ሃገር ፖለቲካ ምንትስ ሳትሉ
የሷን አንዲቷን ነፍስ ከክፉ ከልሉ።

ማነህ ባለሳንጃ...
እዛ ጋ ተቀምጦ ነገር በማላመጥ ክፋት የሚያቦካ
ስለክብሯ ሲባል መቶ አንድ ይወጋ።

ማነሽ ባለ ሰይፏ...
ሲላክ ቁራ የሆነ እምነቱ የላላ
ስለስሟ ሲባል አንገቱ ይቀላ።

ማነህ ባለ ካባ...
ቃሌን ያከበረ እምነት የተቀባ
እንደ እምነቱ መጠን 'ባንገቱ ወርቅ ይግባ።

ማነህ ባለ ኩታ...
ቃሏን ተቀብሎ መሻቷን ላሳካ
አንድ ጋሻ መሬት ከሃብቴ ይለካ።

እሷ ማለት ለኔ
ያለችውን 'ምሆን ሃገር ናት ድንኳኔ፣
የጎኔ ምቹ አጥንት የኔነት ምጣኔ።

አዎ ይህ ነው ቃሌ
ስለእሷ ከሆነ
ከዛሬ በኋላም እንዲህ ነው አመሌ።

እኔ ማለት ለሷ
የአንደበቷ ግርማ የሷነት አድማሷ፣
ሳልቀባ የነገስኩ የስሜት ንጉሷ።

አዎ ይህ ነው ቃሏ
ስለኔ ከሆነ
ከዛሬ በኋላም እንዲህ ነው አመሏ።

እሷ ማለት እኮ
አሞራ እንዳይነጥቃት፣ ስጠብቃት ላድር የማልኩ በህይወቴ
ቅያሪ የሌላት፣ ለሌላ ማልቸራት ብርቄ ናት ውድ ሃብቴ።

አዎ ይህ ነው ቃሌ
ስለእሷ ከሆነ
ከዛሬም በኋላ እንዲህ ነው አመሌ።
አበጀሁ!!!
Pages: 1