ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 10 guests | 3 bots
Pages: 1
Posted on 10-13-17, 07:52 am


Karma: 90
Posts: 581/798
Since: 02-29-16

Last post: 1 hour
Last view: 1 hour
በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ቤተመንግሥት ውስጥ ግብር ተጥሎ እየተበላ እየተጠጣ ነው።
አንዱ ሰውዬ ከቀረበለት ጥሬ ሥጋ ትንሽ ቆርጦ ይበላና የቀረውን እግሩ ስር ወዳለው ዕቃ ያስቀምጠዋል። አሁንም ቆርጦ ይበላና ሌላውን ዕቃው ውስጥ ያስቀምጣል።

ይህን ሁሉ ሲያደርግ አፄ ምኒልክ ፊት ለፊቱ ሆነው ያያሉ። አለቃ ገብረ ሃና ደግሞ ከሰውዬው አጠገብ ተቀምጠው ዝም ብለዋል። አፄ ምኒልክ ሰውዬው ቆርጦ በልቶ የቀረውን የሚያስቀምጠው ለቤተሰቡ ይዞ ለመሄድ መሆኑ ቢገባቸውም አለቃ ይህን እያዩ ምንም አለመናገራቸው ገርሟቸው:

አፄ ምኒልክ: "አለቃ" አሉ።

አለቃ ገብረሃና: "አቤት ጌታዬ?"

አፄ ምኒልክ: "አጠገብህ ያለው ሰውዬ ምን ሆኖ ነው?"

አለቃ ገብረሃና: "ያመዋል ጌታዬ።"

አፄ ምኒልክ: ሳቅ እያሉ "ምኑን?" ብለው ሲጠይቁ

አለቃ ገብረሃና: "እየቆረጠ ያስቀምጠዋል።" ብለው እርፍ!!!!
Posted on 10-13-17, 05:09 pm


Karma: 100
Posts: 430/590
Since: 08-27-16

Last post: 24 days
Last view: 10 hours
Pages: 1