ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 7 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 10-12-17, 06:53 am (rev. 1 by Ye Arada Lij on 10-12-17, 06:54 am)


Karma: 90
Posts: 580/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
(ብዙ ወንዶች ስለምን ላጤ ሆኑ? ስለምንስ ፍቅረኛ ለመያዝ፣ ዴት ለማድረግና ለመጣበስ ግድ የለሽና ዳተኛ ሆኑ?)
* * * * *
እንዴት መሰለሽ እህቴ፣ እስኪ ሌላውን ሰበብ አስበቦች አስቀምጠን፣ መጀመሪያ በአካል- በፌስቡክ - በሰው በሰው - ስራ ቦታ - ወዘተ... ከመተዋወቅ እስከ የመጀመሪያ ፍቅር መስራት ቀን ድረስ ያለውን የወንድ ልጅ ደረቅ ወጪ በችጋራም ጠባሽ ወንድ ሒሳብ እናስላው፡፡
-
የመጀናጀኛ የስልክ ካርድ ወጪ 200 ብር
ቻት ለማድረግ የኢንተርኔት ወጪ 100 ብር
በእህትነት ምሳ ገተታ 140 ብር
ማኪያቶ፣ ሲኒማ ወዘተ ገተታ 120 ብር
ሚኪያቶና ሲኒማ ምናምን ቢደግምሽ 120 ብር
(ጠቅላላ ቅድመ ፍቅር ወጪ - 680 ብር)
____________________________________
ወንድየው አንድ ወር ሙሉ ኢነርጂና ጊዜውን ፈጅቶ፣ እትት ግትት ብሎ፣ 'እኔ ለእውነተኛ ፍቅርና ለትዳር ነው የፈለኩሽ' ብሎ ምሎ ተገዝቶ ካሰመጠ ቡሃላ፣ አኪሩ ቀንቶለት በሆነኛው ቀን 'እሺ ይሰጥሃል' ብለሺው ማታ ቀጠረሽ እንበል፡፡
-
(አሁንም የችጋራም ፍቅር ሰሪ ሒሳብ ነው ምናሰላው)
ቀለል ያለ፣ የድሃ ካፕሎች እራት 200 ብር
3*2፣ በትንሹ 6ቢራ 70 ብር
የደከመ፣ ባለ ቀዝቀዛ ሻወር አልጋ 250 ብር
ጧት ቁርስ፣ ሁለት ዱለትና ጀበና ቡና 90 ብር
-
(ጠቅላላ ድኅረ ፍቅር መስራት ወጪ - 610 ብር፡፡ አንድ ላይ - 680+610= 1,290 ብር)
____________________________________
(አስቢው እንግዲህ!)
አንድ ላጤ ወንድ፣ ምንም ነገር ሳትቀፍዪው፣ ስጦታም ሳይሰጥሽ፣ ከመተዋወቅ እስከ መጀመሪያ ፍቅር መስራት ድረስ በትንሹ 1,290 ብር ያወጣል፡፡ ይሄ የእከካም ድሃ ላጤ ወንድ ወጪ ነው፡፡
-
ፍቅራችሁ በቀጠለ ቁጥር ወጪው ይብስ ይጨምራል እንጂ አይቀንስም፡፡
(ችግር ነው፣ ያበሻ ወንድ)
'ሂሳብ እንጋራ' ካልሺው የወንድነት ኮምፕሌክሱ ሊንጫጫ ነው፡፡ የጸዳ አቅም ኖሮሽ ሙሉ ወጪውን ከሸፈንሽማ በምንተፍረት ሳይቆምበት፣ ጀርባውን ሰጥቶሽ እንደተሳቀቀ ሊያድር ነው፡፡ 'ግዴለህም አታካብድ' ብለሽ የምትፈለጪ ከሆነና 'እሺ' ካለሽ እመኚኝ፣ ይሄ ሊጠብስሽም ሊተኛሽም አልመጣም፡፡ ብርሽን ሊግጥ እንጂ!
-
(የላይኛውን አረፍተ ነገር ልድገመው)
ወንድየው ወድዶሽ ፍቅራችሁ በቀጠለ ቁጥር ወጪው ይብስ ይጨምራል እንጂ አይቀንስም፡፡
(እና?)
ያመልጣላ! ይነካዋልልልልልልል . . . ቀላል ይነካዋል?! አንዴ ፍቅር ከሰራችሁ ቡሃላ ሁለተኛ ደግሞ አያገኝሽም፡፡ ስልክም አያነሳም፡፡ ካነሳም 'ቢዚ ነኝ አይመቸኝም፣ አልቻልኩም' እያለ ሰበብ አስባቡን ሊደረድር ነው፡፡ አንቺም 'ለዛ ነገር ብቻ ነበር የፈለገኝ ለካ' ብለሽ ተበሳጭተሽ ፌስቡክ ላይ feeling down, feeling hurted ምናምን እያልሽ ትፖስቻለሽ፡፡ አዳዲስ ወመኔ አዳኞችም Like ይሉልሻል፡፡ ያ ልጅ ግን የሆዱን በሆዱ ይዞ ነው የሸሸሽ፡፡
ወይኔ ወንድሜን!
-
-
-
____________________________________
(እና፣ የዚህ በቅጡ ያልተፈተሸ ማህበራዊ ስንክሳር መፍተሄው ከቶ ምንድር ነው?)
-
.
(ሀ) ሸገርን ለኦሮሚያ ሰጥቶ ፊንፊኔ ዙሪያ በርካሽ ቤት መከራየት፡፡
.
(ለ) ሆን ብሎ ማርገዝ፡፡
.
(ሐ) አፍን አጣምሞ እንደ ናርሲስት አስሬ ሰልፊ መፖሰት፡፡
.
(መ) በጉዳዩ ዙሪያ ከእኔ ጋራ በውስጥ መስመር መነጋገርና፣ ለችግሩ የማያዳግም ሁነኛ ምክርና የመፍትሄ ሃሳብ ማግኘት፡፡
-
-
እህቴ ሆይ፣ መልሱን (መ) አልሽን? አልተሳሳትሽም! አንቺ እኮ ምርጥ ልጅ ነሽ፡፡ በይ በውስጥ መስመር ብቅ በይ፡፡
-
ከኔ በቀር ሌላ ወንድ በፍፁም እንዳታማክሪ፣ እንዳትናገሪ፣ እንዳታምኚ እሺ

(ፍቅር ያቸንፋል!
Posted on 10-12-17, 07:11 pm


Karma: 100
Posts: 429/610
Since: 08-27-16

Last post: 21 days
Last view: 9 days
Pages: 1