ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Personal Blog የመጣጥፍ ቦታ. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 10-03-17, 04:57 am


Karma: 90
Posts: 571/798
Since: 02-29-16

Last post: 1 hour
Last view: 1 hour
ጉዞ

ይሄ አዝናኝ እና አስተማሪ ፅሁፍ ለፃፈልን ደረጄ ሀይሌ እጅግ በጣም እናመሰግናለን።
.
የእግር ጉዞ ጥሩ ነው።በተለይ በመቀመጥና በምግብ የሚመጡ በሽታዎችን በቁጥጥር ስር ለመዋል ሀይነተኛ መድሀኒት ነው።የእግር ጉዞ መልካም ነው።ግራ ቀኙን እያዩ ለመዝናናት ወይ ለመማር ትልቅ ጥቅም አለው።እናም ሁሌ ተጓዙ ።
መከረኛው ቮልስ ሳትገዛ በፊት በእግር ጉዞ የሚያስተካክለን ቢኖር ማጅላን ብቻ ነበር።ከቲቪ አንደወጣን የቸርችር ቁልቁል ቀስ እያልን እንወርደዋለን።ኦቾሊኒ እየበላን ስንወዘወዝ ሰፈር የምንደርስበት ሰሀት አይታሰበንብ።
ከብዙ ጉዞዎች የአንዱ ቀን የተለየ ገጠመኝ እስከዛሬ የምረሳው አልሆነም።የተለመደው ጉዞ በሰንጋተራ በኩል ስናደርግ ከሆነ ቡና ቤት ውስጥ የሆነችው ቆንጆ ልጅ ስሜን ተጣራች እኔም ሀብቴም ታገልም ቆምን እጅግ ተገርማ የምታየን ቆንጆ ልጅ በሩ ላይ ቆሞ እንድንገባ ተማፀነችን እርስ በእርስ እየተያየን መገባበዝ ጀመርን።ቆፍጠን ብዬ ደረጃውን ወጣሁና ገባሁ።እነ ታገል ተከተሉኝ።
ልጅቷ ሁለት ድራፍትና ለስላሳ ፊታችን ላይ ገተረቻቸው አሁን መተያየት ሲከጅለን ታገል የራሱን ለስላሳ አፈፍ አርጎ አነሳ።እኛም ድርጅታችንን አነስተኛ የመጀመሪያ ጉንጭ መጠን አጣጣምን።ሁለት እጆቻችንን በእግሮቻቸው መሀል ሸጉረን ቤቱን መቃኘት የዝን።
ልጅቷ ለምን እንዳስገባችኝ በየፊናችን ላይ ገተረቻቸው አሁን መበያየት ሲከከጅለን ታገል የራሱን ለስላሳ አፈፍ አርጎ አነሳ።እኛም ድርሻችንን እንስተን የመጀመሪያ ጉንጭ መጠጥ አጣጣምን።ሁለት እጆቻንን በእግሮቻችን መሀል ሸጉረን ቤቱን መቃኘት ያዝን . . . . ልጅቷ ለምን እንዳስገባችን በየፊናችን እናስባለን ታገል ብቻ ነው ለስላሳው ላይ የሚጠበበው ቆንጆውዋ አጠገባችን መጥታ ተቀመጠች ፍቅር ይሁን አድናቆት ግራ ስለገባን ኳስ ይምጣ ብለን ዝም አልን ዝምታውን በአድናቆት ገፈፈችው።በቴሌቭዥን ስታየን እንደምትደሰት እንደምትኮራ ነገረችን በሀብቴን ቅጥነት እያነሳች የኔን ርዝመት እየሳቀችበት የታገል ጨቅላነት እያባባበት ብዙ አዝናናችን።በላይ በላዩ ስትጋብዘን ትንሽ ወዥበር አለብኝ ።
አመስግነን ልንወጣ ተሰናዳን ከዚህ በፊት እንደዚ ያለ ቤት ገብተን ስለማናውቅ ትንሽ ግር ብሎናል ታገል ብቻናት እየተዝናናች የለችው ምናልባት ብሄረ ፅጌ መስሏት ይሆናል።
ምግብ ብጤ ይዛ ስትመጣ ጉዞአችንን አዘገየነው ያለ ምግብ መጠጥ ጠጥተን ስለማናውቅ ቀበቷችንን ሰፋ አድርገን ተዘጋጀን ያመጣችውን ጥብስና made in china የሚለው ፅሁፍ ጨምሮ ድራሹን አጠፋነው።እንደውሀ ድራፍቱን በላዩ በላዩ ከለበስነው።
የልጅቷ አድናቆት ግብዣ ማለቂያ የለውም ትንሽ ተንፈስ እንዳልን የምስጋና መሀት አዥጎደጉደን ልንወጣ መራቂው ተመረጠ።እሷም ዘወር እያለች ለካ ትቀነድብ ኖሮአል ፊቷ ላይ የሞቅታ መንፈስ መነበብ ጀምሯል ደስታዋን የሚጋሩዋት ጓደኞች ስለዘገዩ በጣም ተናዳለች እንድንቆይ ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም።ክፋቱ ደግሞ ያኔ ሞባይል አልተጀመረም።በምን ትጥራቸው በር በሩን በጉጉት እያየች ሳለ ለመሄድ ተነስታ እፏ ትንሽ ኮልተፍ እያሀ ትለምነን ጀመር መቁረጣችን ስታውቅ በለ መቶ ብር ኖት አውጥታ ሌላ ቦታ እንድ ንጠጣ ኪሴ ውስጥ ሸጎጠችው።ሀብቴ በሩ እንዳይገባ ተከላክሎ ነበር እዝኖ እንዳ ይመስላቸው የኪሴን ቀዳዳነት ያውቀው ስለነበር ነው በወዲህኛው ኪሴ ብሩን አዟዙረን ውልቅ ብለን ወጣን።እኛም ድራፍቱ ታገል ሙቀቱ አስክሮአል ትንሽ እንደተጓዝን ቤት መረጣ ላይ አልተግባባንም።ቸርቸል ቁልቁለቱን ላይ የገባው ደረታችን አሁን ወጣ ብሏል በተለይ እኔ!በሩ እኔ ዘንድ ስለሆነ ሁለት እጄን ከትቼ ቤት ስመርጥ ልንጠጣ ሳይሆን #ልንገዛው_ነው ሚመስለው።
የሆነ ቤት መርጠን ልንገባ ስንገባበዝ ቆንጀዋ ልጅ ከዋላችን በተፍ አለች አስፈቅዳ መምጣቷን እና ትንሽ አብራን ልትጫወት አንደፈለገች ነገረችን በደስታ ተቀብለናለናት።ልንገባ ስንልወደታች የተሻለ ቤት እንዳለ ጠቁማን ወደፊት ቀደም አለች ሞቅታው ከቀድሞ ትንሽ ጨልሯል።
ሳቋ ወጪ ወራጁን ያስገርማል አብረናት ወደታች መንገዱን በያያዝነው በእጇ ባዶ የክብሪት እቃ ይዛለች ታሽከረክራለች ታንቀረቅባለች. . . .
የተባለው ቦታ ናፈቀን መሄድ መሄድ ብቻ ሆነ።አንደርስም ወይ አልናት።ትንሽ እንደሚያስጉዘን ነግራን በክብሪት ቤቱ ጨዋታዋን ቀጠለች።ታንቀረቅባለች ታቀባብላለች።እኔ ንፋስ ነክቶኝ ወደነበርኩበት ተመልሻለው ሀብቴም እንዲሁ ታገል ትንሽ ተመልሰዋል ልጅቷ የራሷን ዘፈን እየዘፈነች ከዋላ ትከተለናለች።የልጅቷ ሞቅታ በንፋስባሰበት የክብሪት ቤቱን ወደ ሰማይ ወረወረችው ከፊት ለፊታቸው የሚመጣው ላንድ ክሩዘር የክብሪት ቤቱ ድንጋይ መስሎት ጎማውን አስጩሆ ዞሮ ቆመ።ልጅቷ ፊቷ በደስታ ፈካ እንዲህም አለች እነ ደረጄ አንዴ ታገሱኝ የማውቀው ሰው መኪና አቆመልኝ ሰላም ብዬው ልምጣ እሺ"......ብለን ሩጫ ወደ ላንድ ክሩሰሩ አደረገች።
በሩ ዘንድ ስትደርስ በሩን ከፍቶ ግንድ የሚያክል ሰውዬ ደረቱን ነፍቶ
ወጣ።እስከ ፒያሳ የሚሰማ ጥፊ ጆሮዋ ላይ አረፈ ።
ዞር ብላ እነደረጄ የሚያውቀኝ መስሎኝ ነበር ለካ አያውቀኝም ብላ ፊቷን አሻሸችው።
#ደረጄ ሀይሌ ሚያዝያ 1986 እውነተኛ ታሪክ።ተፈፀመ።
Pages: 1