ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 5 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 09-28-17, 03:00 am


Karma: 90
Posts: 568/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
ፍቅረኛሞቹ አንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ነው የሚማሩት፡፡ ብዙ ጊዜ ተለያይተው
አያውቁም፡፡ አንድ ቀን ግን ያለልማዳቸው ተለያዩ፡፡ ሴትዋ ወደ ዩኒቨርስቲው
ሳትመጣ ቀረች፡፡ "ፍቅረኛዋ ምን ሆና ይሆንየቀረችው?" እያለ በሐሳብ
እየተጨነቀ እያለ ስልኩ ተደወለ፡-
እሱ፡ ሃይ የኔ ማር
እሷ፡ ሃይ እንዴት ነህ
እሱ፡ ውዴ ዛሬ ወደ ግቢ አልመጣሽም በሰላም ነው? በጣም ናፍቀሽኛል!
እሷ፡ በሰላም ነው የኔ ቆንጆ፡፡ ትንሽ አሞኝ ሐኪም ቤት ሄጄ ነበር፡፡
እሱ፡ ምንድን ነው! ምን ነካብኝ የኔ ንግሥት?
እሷ፡ አይ ምንም ከወቅቱ የአየር ሁኔታጋር የተያየዘነው፡፡ አሁን ደህና ነኝ
ተሽሎኛል፡፡
እሱ፡ አሁን የት ነው ያለሽው እመጣለሁ?
እሷ፡ ኖኖ ችግር የለውም አትምጣ፡፡ አባዬ ከኔ ጋር ስላለ አይመችም፡፡ ግን እስቲ
አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?
እሱ፡ እሺጠይቂኝ
እሷ፡ ምን ያህል ታፈቅረኛለህ?
እሱ፡ የዛሬ ደግሞ ምን ዓይነት ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ካለው ሁሉአብልጬ
አፈቅርሻለሁ፡፡ ሕይወቴ ዓለሜ አንቺ ነሽ ሌላ ሕይወትሆነ ዓለም የለኝም፡፡
እሷ፡ ዋው አመሰግናለሁ!
እሱ፡ ግን ለምን ጠየቅሽኝ?
እሷ፡ ዝምታ
እሱ፡ ችግር አለ? በጥልቅ ስሜት እንደማፈቅርሽ እያወቅሽ ለምን ጠየቅሽኝ?
እሷ፡ አረ ምንም ምን ያህል እንደምታፈቅረኝ ለማወቅ ያህል ነው፡፡ ግን እኔን
ታስብልኛለህ?
እሱ፡ በጣም! በዚህ ዓለም ያለችኝ እስትንፋሽ ላንቺ ነው የማበረክታት፡፡ እኔ ሞቼ
አንቺ እንድትኖሪ ነው የሁልጊዜ ምኞቴና ሕልሜ፡፡
እሷ፡ እርግጠኛ ነህ እስትንፋሽህ ለኔ ትሰጠኛለህ?
እሱ፡ ምንም አትጠራጠሪ! ግን ችግር አለ? ምንድን ነው ያለአመልሽ መጠራጠር
አበዛሽ?
እሷ፡ አረ ምንም ያጋጠመ ችግር የለም፡፡ ሁሉም ነገር ሰላም ነው የኔ ጌታ፡፡
እሱ፡ እኔ እንጃ እስቲ ይሁን፡፡እኔ ግን ምን እንደሆነእንጃ ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል፡፡
እሷ፡ ምንም አትፍራ ግን ለእርሷ ብለህ ሙት ብትባል ለእኔ ብለህ ትሞታለህ?
እሱ፡ አዎ ላንቺ ብዬ ራሴን አጠፋለሁ፡፡ ላንቺ ብዬ ገመድ አንገቴ ላይአስገብቼ
ራሴን ቂቅ አድርጌእገድላለሁ፡፡
እሷ፡ ዋው ሪሊ!
እሱ፡ በጣም እርግጠኛ ነኝ፡፡ አንቺ ልጅ ግን ለምንድን ነው እነዚህ ጥያቄዎች
የምትጠይቂኝ? በሰላም ነው?
እሷ፡ ኖ ሁሉም ነገር ሰላም ነው ዝም ብዬ ለማረጋገጥ ያህል ነው፡፡ አየህ
ስለቀጣዩ ሕይወታችን ለማሰብ ስላንተ እርግጠኛ መሆንአለብኝ፡፡
እሱ፡ ኦኬ
እሷ፡ አባዬ እየጠራኝ ነው ባይ የኔ ቆንጆ
እሷ፡ ቻው ከልብ አፈቅርሻለሁ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ካምፓስ ውስጥ እሱ ከወንድ ጓደኛው ጋር ተገናኙ፡፡
እሱ፡ ሃይ ፍቅረኛየ አይታሃታል እንዴ? ዛሬም አልመጣችም መሰለኝ?
ጓደኛ፡ ባለጉዳይ ያላየሃት እንዴት እኔ አያታለሁ?
እሱ፡ ባክህ ትናንት ምን እንደሆነች በመዓት ጥያቄዎች ስታጣድፈኝ ነው
ያመሸችው፡፡
ጓደኛ፡ አንተ ጅል እሷ ዝም ብላ ነው ለጊዜ ማሳለፊያ የምትጠቀምብህ
እሱ፡ አፍህ ብትይዝይሻላልአንተ ሰውዬ የሷ ክፉ ነገር እንድትናገረኝ
አልፈልግም፡፡
ጓደኛ፡ ወዳጄ ከዚህ ውጭ ምንም ልልህ አልችልም፡፡
የዕለቱ የትምህርት ክፍለጊዜ አልቆ ወደ ዶርማቸው ሄዱ፡፡ ፍቅረኛውን ደወለላት፡፡
እሷ፡ ሃይ እንዴት ነህልኝ?
እሱ፡ ደህና ነኝ ተሽሎኛል አላልሽም እንዴ? ዛሬስ ለምን ቀረሽ?
እሷ፡ የዶክተር ቀጠሮ ነበረኝ፡፡
እሱ፡ አሁን ገባኝ በእኔ ላይእየቀለድሽ እንደሆነ፡፡ቀጠሮሽ አያልቅ!
እሷ፡ እናቴ በቤት ስልክ እደወለች ነው ቻው እሷን ላናግር ነው
እሱ፡ ችግር የለም ጨርሺ እጠብቅሻለሁ
እሷ፡ ኖኖ ትንሽ ጊዜይወስዳል ነገ እደውልላሃለሁ
እሱ፡ በፍፁም ከዚች ንቅንቅ አልልም እያልኩሽ
ልጂቱ ከእናቷ ጋር ይሁን ከሌላ ሰው ጋርየነበራትን ወሬ ጨርሳ ወደ ፍቅረኛዋ
ተመለሰች፡፡
እሷ፡ ለደቂቃዎች በዝምታ ተውጣ ከቆየች በኋላ……..ስማ የኔ ውድ ስሜትህ
በመጉዳቴ ይቅርታአድርግልኝ ከዛሬ ጀምሮ ግንኙነታችን እዚህ ላይ እንዲቋጭ
ወስኛለሁ፡፡
እሱ፡ ምን!
እሷ፡ አዎ ለሁለታችን የሚያዋጣውግንኙነታችን እዚህ ላይ እንዲቋጭ ማድረግ
ነው፡፡
እሱ፡ ለምን ግን ምን በደልኩሽ?
እሷ፡ ምንም የበደልከኝ የለህም በጣም እወድሃለሁ ቻው
እሱ፡ አንቺ አስመሳይ ችግር የለውም የኔ ግፍ ይሰጥሻል ቻው መልካም ሕይወት
ፍቅረኛው ወደ ዩኒቨረስቲው ከመጣች ሦስት ሳምንታት አለፉ፡፡ ፍቅረኛዋ
ተጣላልቶት ወደነበረው ጓደኛው ጋር በመሄድ ይቅርታ ጠየቀው፡፡
እሱ፡ ጓደኛዬ ይቅርታ አድርግልኝ ለእኔ እንደምታስብልኝ አሁን ነው የገባኝ፡፡
ጓደኛው፡ ምንድን ነው? ምን ተፈጠረ?
እሱ፡ ፍቅረኛዬ ግንኙነታችን እንደተቋረጠ ነገረችኝ
ጓደኛው፡ እኔኮ ይሄ እንዳይፈጠርነው ሙሉ በሙሉ ልብህ ከፍተህ አትስጣት
ያልኩህ፡፡ ወይኔቁማር ተበላህ፡፡ አይዞህ ሴት ብትሄድ ሴት ትመጣለች፡፡ እዚህ
ካምፓስ ያሉ የሚያማምሩ ሴቶች ያንተው ናቸው፡፡
እሱ፡ በምንም ተአምር ከአሁን በኋላ ሴት የምትባለው አጭበርባሪ ፍጥረት
አላይም፡፡
ጓደኛው፡ የእሷ ጓደኛ ታውቃታለህ አይደለእቺ ማህሌት የምትባለው ይሄ ስልክ
ስጠው ብላ ሰጥታኛለች፡፡ ከክላስ በኋላ በዚህ ስልክ ደውለን ልክ ልክዋን
እንነግራታለን፡፡
ክላስ አልቆ ጓደኛሞቹ በግ ተራ ቁጭ ብለው ወደተሳጣቸው ስልክ ደወሉ፡፡
ነርስ፡ ሄሎ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ማን ልበል?
እሱ፡ በድንጋጤ ትንፋሽ እያጠረው…..በዚህ ስልክ ደውሉ ተብለን ነበር?
ነርስ፡ የሄርሜላ ፍቅረኛ ነህ?
እሱ፡ አዎ
ነርስ፡ ፍቅረኛህ ታማ ሆስፒታል ውስጥ ተኝታ ነው ያለችው፡፡ ከቻልክ መጥተህ
እንድታያት ትፈልጋለች፡፡ ክፍል ቁጥር 320 ነው የተኛችው፡፡ አሁን ስራ ስለያዝኩ
ብዙ ላወራህ አልችልም ቻው!
ከዚያበኋላ እሱና ጓደኛው ኮንትራት ታክሲ ይዘው ወደ ሆስፒታሉ ሄዱ፡፡ እውነትም
ፍቅረኛው በሞትና በሕይወት መካከል ሆናአገኛት፡፡
እሱ፡ ምነው ማሬ ደህና አይደለሽም እንዴ?
እሷ፡ ቃላት ማውጣት አቃታት፡፡ ፍቅረኛው በእንዲህ ዓይነት ሁኔታስላገኛት በሐዘን
ኩምትር ብሎ አምርሮ አለቀሰ፡፡ በዚህ መሃል የፃፈቸው ማስታወሻ እንዲያነበው
በእጇ አመላከትችው፡፡ ወረቁቱን አንስቶ ማንበብ ጀመረ፡-
"ወዴ ዛሬ የጠራሁህ ልሳነበትህ ነው፡፡ ካንተ ጋርብኖር ደስታዬ አልችለውም ነበር
ግን አልቻልኩም፡፡ ካንሰር የተባለው ሕመም ይዞኝ በመጨረሻዋ የሕይወቴ
ምዕራፍ እገኛለሁ፡፡ ግንኙነታችን ቀደም ብሎ እንዲቋረጥ የፈለግኩት የኔ
ዘላለማዊ መለየት ድንገት እንዳይሆንብህ፣እየተለማመድክ እንድትቆይ ብዬ
ነው፡፡ ቻው እስከዘላለሙ አፈቅራሃለሁ" ይል ነበር፡፡
ፍቅረኛዋ እጅዋን ይዞ ደም አነባ፡፡ በደምብ አልቅሶ ሳይወጣለት ነርሷ መጥታ
ከክፍሉ እንዲወጣ አዘዘችው፡፡ በነጋታው ወደ ሆስፒታሉ ሲሄድ ፍቅረኛው
አርፋለች፡፡ የሚወዳትን ፍቅረኛውን ከቀበረ በኋላ እርሱም በተራው በሻወር ቤቱ
ውስጥ ራሱን አጥፍቶ ተገኘ፡፡ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት የፃፈውማስታወሻ ሲነበብ
እንዲህ ይል ነበር፡
"ውዴ ታስታውሺ ከሆነያላንቺ እንደማልኖር ገልጬልሽ ነበር፡፡ አዎ አንቺ ለእኔ
ብለሽ እንደሞትሽ ሁሉእኔም ላንቺ ብየ ለመሞት ወስኛለሁ፡፡ ቃልሽን ጠብቄም
ተከትየሻለሁ!"
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»

Pages: 1