ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Doctor's Help. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-22-17, 04:24 am


Karma: 100
Posts: 361/426
Since: 07-12-15

Last post: 34 days
Last view: 34 days
የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ

በከፍተኛ ራስ ምታት ተሰቃን ላላችሁን እነሆ መፍትሄ… በተመሳሳይ በራስምታት የሚሰቃዩ ሌሎች ሰዎችም ስላሉ እባክዎ ሼር በማድረግ እንታደጋቸው፡፡

1. አመጋገብዎን ያስተካክሉ

✔ መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎ

✔ ቁርስዎን መመገብ አይዘንጉ

✔ ማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት፣አይብ፣ቡና እና የአልኮል መጠጦች)

2. በቂ እረፍት ማድረግ

✔ መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎ

✔ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩ

✔ በቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል። ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላል

✔ እንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ

3. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ

✔ በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣

✔ የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ፣ ይህ ማለት ደግሞ

• ቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋል

• ሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸት

✔ ገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ

4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ

(ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና፤የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)

5.ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ

ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ።

✔ ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎ

✔ ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ

✔ የዕረፍት ጊዜ ይኑርዎ

✔ ለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎ

✔ ራስዎን ዘና ያድርጉ

6. የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ

✔ በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል፡፡
✔ለሌሎችም ሼር፣ በተን በተንተን እናድርግላቸው፡፡

......................................

ምንጭ - ዶ/ር ሆነሊያት

Pages: 1