ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-18-17, 06:36 am


Karma: 100
Posts: 339/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
⚽ የቀድሞው የአርሰናልና የባርሴሎና ኮከብ ቴሪ ዳንኤል ሄንሪ የእግር-ኴስ የህይዎት ታሪክ፣ የዝውውር ሁኔታዎቹ፣ የግል ህይዎቱ እንዲሁም ሌሎች ተጨዋቹን የተመለከቱ ዳሰሳዎች!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በAugust 17,1977
የተወለደው ምታተኛው የቀድሞ ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋችና የአሁኑ የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ እየሰራ ያለው ቴሪ ዳንኤል ሄነሪ በተጫዋችነት ዘመኑ ድንቅ አጥቂ በመሆንና ድንቅ ብቃቱን ለመላው አለም በማሳየት ይታወቃል፡፡
የዘር ግንዱ ከAntillean የሚመዘዘው ሄነሪ፡ ተወልደው ያደገው በፈረንሳዩ ፓሪስ ከተማ Les Ulis መንደር ስሆን አባቱ Antoine_Guadeloupe ከLa Désirade islandand ስሆን እናቱ Maryse ደግሞ ከMartinique እንደ ሆኑ ይነገራል፡፡
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ ገና በ7 አመት ጨቅላ እያለ በመንደሩ ጎዳናዎች ላይ በሚያሳየው ድንቅ የእግር ኳስ ክህሎቱ ያዩት ClaudeChezelle ለCO Les Ulis ለተባለች መለስተኛ ክለብ እንዲጫወት እድል ለመስጠት ተገደዱ፡፡
ከዛም በሚያሳየው ድንቅ ብቃት በ1989 US Palaiseau ለተባለ ክለብ ለመጫወት በቃ፡፡ ከዚህ ክለብ ጋርም ብዙ ሳይቆይ ES Viry Châtillon በመቀላቀል ለሶስት አመታት ተጫወተ፡፡
ከዛም አሰልጣኙን በመከተል ወደ Clara Fonte ተዘዋወረ፡፡
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ ሄነሪ የፕሮፌሽናል እግር ኮስ ተጫዋችነቱን በ1994 አንድ ብሎ የጀመረው በፈረንሳይ ክለብ ሞናኮ ነበር፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1998 ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በመጠራት ሀገሪቱ ያዘጋጀችው የአለም ዋንጫ ላይ የሀገሩን ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ማልያ በመልበስ ታሪክ ከሰሩት የፈረንሳይ የምንግዜም ወርቃማ ልጆቿ አንዱ ለመሆን ቤቃ፡፡
በተመሳሳይ አመት ሄነሪ ለጣሊያን ክለብ ጁቬንቱስ ፈርሞ በአንድ አመት ቆይታው የሴሪኣ ዋንጫን አንስቶአል፡፡ በጁቬንቱስ ከአንድ አመት ቆይታው በኃላ በ1999 ወደ እንግሊዙ ክለብ አርሰናል በ11 ሚለየን ዮሮ ተዘዋወረ::
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ ቴሪ ዳንኤል ሄነሪ አርሰናል ከገባ በሗላ በሞናኮ የረጅም ግዜ አሰልጣኙ በሆኑት በአርሴን ቬንገር ስር እየሰለጠነ በአለማችን አሉ ከተባሉት ምርጥ ተጫዋቾች ግንባር ቀደም ሆነ፡፡ የአለማችን አስፈሪና ቁጥር 1 አጥቂ በመሆኑም ለአርሰናል 228 ጎሎችን በማስቆጠር የክለቡ የምንግዜም የጎል አግቢነት ሪከርዱን ከመያዝም አልፎ ክለቡን ሁለት ጊዜ የፕሪሚየር ሊግና ሶስት ግዜ የኤፍ ኤ ዋንጫ ባለቤት እንዲሆን ጉልህ አስታውፆ አበርክቷል፡፡
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2003 እና 2004
በፊፋ የአለም ኮከብ ተጫዋች ምርጫን በሁለቱም አሸንፏል፡፡ሁለት ግዜ የፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ምርጫ አሸናፊው ሄነሪ የመጨረሻዎቹን ሁለት አመት ለአርሰናል አምበል ሆኖ ክለቡን ለሻምፕዮንስ ሊግ ፊፃሜ አድርሰዋል፡፡ሶስት ግዜም የFWA Footballer of the Year ሶስት ግዜ አሸንፏል፡፡
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሰኔ; 2007 ከስምንት ወርቃማ አመታት በሗላ ወደ ባርሴሎና በ24£ የተዘዋወረው ሄነሪ በ2009 ለክለቡ ላሊጋ፣ ኮፓ ዴላሬ እና ሻምፕዮንስ ሊግ ዋንጫን በአንድ አመት በማንሳት ታሪክ ከሰሩት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ለመሆን ቻለ፡፡ በዚህም ሳያበቃ ሱፐርኮፓ ዴ ኢስፓና UEFA ሱፐር ካፕ እና FIFA ክለብ ወርልድ ካፕ በማግኘት ሄነሪ በተጫዋችነት ህይወቱ ማግኘት ከምጠበቁት ዋንጫዎች በላይ ያገኘው ተጫዋች ለመሆን ችሏል::
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 ወደ አሜሪካው ክለብ ኒውዮርክ ቡልስ በማቅናት ከክለቡ ጋር የEastern Conference ዋንጫንና የMLS Supporters Shield ለማሸነፍ ችሏል ገና በልጅነቱ ከሀገሩ ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር በ1998 የአለም ዋንጫ፣ በ2000 የአውሮፓን ዋንጫ እና በ2003 የኮንፈደሬሽን ዋንጫን በማንሳት ድልን ማጣጣም የቻለው ሄነሪ በ2007 ለረጅም አመታት በሚሽን ፕላቲኒ ተይዘው የነበረውን የምንግዜም የጎል አግቢነት ሪከርድን በ51 ጎሎች ለመያዝም ችሏል፡፡
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
☞ ቴሪ ሄነሪ ከ2010 በሗላ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋችነት ራሱን አገለለ፡፡
★ በግሉ ያገኛቸው ሽልማቶች
☞በ2003 የአለም ኮከብ ተጫዋች 2ኛ
☞በ2004 የአለም ኮከብ ተጫዋች 2ኛ ☞በተመሳሳይ አመታት በተከታታይ 2 ግዜ
የፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች
☞3 ጊዜ የFWA የአመቱ ኮከብ ተጫዋች በማሸነፍም የአለማችን ብቸኛው ተጫዋች ነው፡፡
☞የFrench ኮከብ ተጫዋች 4 ግዜ በማሸነፍም ብቸኛው ተጫዋች
☞የ10 አመታት ለፕሪሚየር ሊግ ምርጥ
☞በFIFA የዘመኑ 100 ምርጥ ተጫዋች ☞የአውሮፓ ወርቅ ጫማ 2 ግዜ አሸናፊ
በ2002፣ 2004፣2005፣ 2006 የፕሪሚየር ኮከብ ጎል አግቢ በመሆን ለአራት ግዜ ያሸነፈ ብቸኛው ተጫዋች ተብሏል፡፡
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ የሄነሪና የአርሰናል ቤተሰቦች
ሄነሪ አርሰናልን ለቆ ከሄደ በሗላም ለክለቡ ጥልቅ ፍቅር እንዳለው ደጋግሞ ይናገር ነበር "ወደ ፊት በአርሰናል ምንም ስራ እንኳን ቢያጣ ለተጫዋቾች ውሃ አቀባይ ሆኜ ብሰራ ደስታዬን አልችልም" እስከማለት ደርሷል፡፡
ሄነሪ በአርሰናል ክለብ ደጋፊዎችና መላው የአርሰናል ቤተሰቦች ዘንድ በጣም ከመወደዱና እሱም በነሱ ፍቅር በማበዱ የተነሳ ክለቡን ለቆ ወደ ባርሴሎና ከተጓዘ በሗላ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2008 የሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ እጣ ድልድል አርሰናል ከ ባርሴሎና በመድረሱ የአለም መነጋገሪያ ርዕስ የሆነው ሄነሪ በጣም ከምወዱትና በጣም ከምወዳቸው የቀድሞ ክለቡ ተቃራኒ ሆነው ስለ መጫወቱ ነበር፡፡
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✍ ሄነሪም "የአርሰናል ተቃራኒ ሆኖ መጫወት የማይታሰብ ነው፡ ቢቻል ቢቻል አሰልጣኙ ችግሬን ተረድቶ እንዳያሰልፈኝ እማፀናለው" ብሎ እንደ ነበር ይታወሳል፡፡
በጫወታው እለት ሄነሪ ከቋሚ አሰላለፍ ውጪ ብሆንም ከ80 ደቂቃ በሗላ ተቀይሮ ወደ ስታዲየም ስገባ ስታዲየሙን የሞላው 62 ሺ መላው የአርሰናል ደጋፊ ከመቀመጫው ላይ ተነስተው በእግር ኳስ ታሪክ ተደርገው የማይተወቀውን ልብ የሚነካ ደማቅ አቀባበል ሲያደርጉለትና የስታዲየሙን ድባብ የተመለከቱት ተጫዋቾችም ሆነ ጋዘጠኞች እንባ ሲተናነቃቸው ተመልክተናል የሄነሪም እምባ አላባራ እስክል ደርሶ ለእግርኳስ አፍቃሪዎች የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
_______________________________________

Pages: 1