ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-11-17, 06:15 am


Karma: 90
Posts: 560/879
Since: 02-29-16

Last post: 66 days
Last view: 66 days
ሴት ሆይ : የትዳር ምርጫሺን ስትመርጭ ብር ያለው ፣ቆንጆ የሆነ ተክለ ስውነቱ ያማረ፣ወይም ሀብታም ፣የተማር ድልቅቅ አርጎ የሚያኖርሺ ትፈልጊ ይሆናል አትሳሳች ።።።።።።
ትዳር በሀብት ብዛት የማትወሰን በመልክ ማማር የማትመካ ድንቅ የህይወት መንገድ ናት ።።
እህቴ ሆይ: መልኩ ሳይሆን ቆንጆ ልብ ቆንጆ የሆነውን፣ልብሱ ሳይሆን ንፁህ ልቡ ንፁህ የሆነውን የህይወት አጋርሺን ከፈለግሺ የምትወጂውን ወንድ ከማንም ጋር አታወዳድሪው ሀይማኖትን አክብሪና ፈጣሪውን የሚፈራ ባል እንዲሰጥሺ አስተምሪው በትዳርሺ ደስታ እንዲኖርሺ ከፈለግሺ ህይወትሺን ከማንም ጋር አታወዳድሪው ባልሺ ማለት የአባትሺ ምትክ ማለት ነው። ተከባከቢው እንጂ አትጨቃጨቂው ወንድ ባልሺ የደስታ ምንጭሺ ነው ከእቅፉ ውስጥ ገብተሺ ሌላ አለም ውስጥ የገባሺ እስኪመስልሺ የሚያስደስትሺ ባልሺ ነው። ያንችባል ላንች ውብና ቆንጆ ንጉስሺ ነው ። አክብሪው በደካማጎኑ ገብተሺ አበርችው ሀይል ሁኛው አጠንክሪው። ከተሳሳተ አስርጂው ደስታን ስጪው ብርታት ሁኛው ያኔ የህይወት ጣእሙን ታውቂያለሺና
ፈጣሪውን የሚፈራ ትዳሩን ያከብራልና።።
✍ # ወንዶች ሆይ: መልክ ትዳር አይሆንም የተስተካከ ተክለ ሰውነቷ ቤትህን አያቆመውም፣ ያ ትልቅ መቀመጫዋ ለቤትህ ሶፋ አይሆንህም ልብ በል ትዳር ማለት የህይወትን ጣዕም የምታውቅበት የምትደጋገፍበት በሳል የምትሆንበት አባት የምትሆንበት ከብቸኛነት ወተህ ሁለተኛ እናት የምታገኛበት፣ሀሳብህን የምትጋራልህ፣መፍትሄ የምስጥህ የህይወትህ ማጣፈጫ ደስታን የምሰጥህ ሴት ከፈለክ መልኳን ሳይሆን ከአስተሳሰቧ፣ከአለባበሷ ሳይሆን ከፈጣሪ ፈሪነቷ፣ ልብ ብለህ እያት በአሁኑ ስአት ፈጣሪዋን የምትፈራ ሴት ማገኛት መታደል ነውና ።።።

Posted on 09-11-17, 03:50 pm


Karma: 100
Posts: 403/610
Since: 08-27-16

Last post: 80 days
Last view: 6 hours
Pages: 1