ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-06-17, 12:55 am


Karma: 100
Posts: 305/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች የእግር ኳስ ቡድኑን አፈረሰ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማኅበር የወንዶች የእግር ኳስ ቡድኑን ማፍረሱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማኅበር ዛሬ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንትና የስፖርት ማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ሰይፉ ቦጋለ ባንኩ ከ17 ዓመት በታች፣ ከ20 ዓመት በታች እና የዋናው የእግር ኳስ ቡድኖች መፍረሳቸውን ይፋ አደርጓል።

የሴቶች የእግር ኳስ ቡድንና የአትሌቲክስ ቡድኖቹ ግን ለጊዜው እንደማይፈርሱ የገለጹት አቶ ሰይፉ፥ ነገር ግን ውጤታቸው እየታየ ወደፊት ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

ውሳኔው የክለቡን ውጤት ብቻ መሰረት አድርጎ የተወሰነ ሲሆን፥ የስፖርት ማኅበሩ የእግር ኳስ ክለቡን ያለፉትን ስድስት ዓመታት ውጤቶች በሚገባ ከመረመረ በኋላ ውሳኔውን እንዳስተላለፈ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የሴቶቹ የእግር ኳስ ክለብ ከወንዶች የተሻለ ውጤት ቢኖረውም ላለፉት ሁለት ዓመታት ሻምፒዮን መሆን አልቻለም፤ ይሁን እንጂ የስፖርት ማኅበሩ ለሴቶቹ የእግር ኳስ ቡድን አንድ ተጨማሪ ዓመት እድል እንደሚሰጠው ገልጸዋል፡፡

የስፖርት ማኅበሩ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት በሚገባ የክለቡን አሰራር እንዳጠና ያስታወቁት ኃላፊው፥ ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በማሰብ እንዲሁም ክለቡ ለወጣትና ኣዳዲስ ተጫዋቾች እድል በመስጠት የሀገሪቱን እግር ኳስ ለመደገፍ በሚል ክለቡን ይዞ መቆየቱን ተናግረዋል።

ሆኖም ግን ይህ ግን በፍጹም ሊሆን አልቻለም፤ አሁን በሀገቱ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻርም ሊሆን የሚችል አይመስልም በሚል ክለቡን ለማፍረስ መገደዱን ኃላፊው አስታውቀዋል።

ባንኩ ሲገነባቸው የነበሩ የስፖርት መሰረተ ልማት ስራዎች በሙሉ እንደሚቀጥሉና ባንኩ እነዚህን ሥራዎች የመገንባት የመጠበቅና የመንከባከብ ግዴታ አለበት ብለዋል።

የስፖርት ማኅበሩ ለ2010 ዓ.ም ለክለቡ ይዞት ከነበረው 85 ሚሊየን ብር በጀት ከ50 በመቶ በላይ በመቀነስ በ30 ሚሊየን ብር ብቻ እንደሚንቀሳቀስ መወሰኑን ተናግረዋል።

የባንኮች የእግር ኳስ ክለብ በ1975 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን፥ በ1992 የግል ባንኮችን አባል አድርጎ የኢትዮጵያ ባንኮች ስፖርት ማህበር በሚል በአዲስ አደረጃጀት መጥቶ እንደነበር ይታወሳል።

ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስር በመሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስፖርት ማኅበር ተብሎ በሀገሪቱ እግርኳስ ላይ ቆይቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ እስከተጠናቀወው የውድድር ዓመት ድረስ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲወዳደር ቆይቶ ወደ ከፍተኛ ሊጉ መውረዱም ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእገር ኳስ ክለብ በ1996 በክለቡ ታሪክ ብቸኛው የጥሎ ማለፍ ዋንጫ አንስቷል ያነሳ ሲሆን፥ በ1997 እና በ2002 ዓ.ም የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ላይም ተሳትፏል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተለያዩ ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዳቸውን ተከትሎ በመፍረስ ላይ ይገኛሉ።

ከእነዚህም ውስጥ የሙገር ሲሚንቶ የእገር ኳስ ክለብ እና የዳሽን ቢራ የእግር ኳስ ክለብ ተጠቃሽ ናቸው።

Pages: 1