ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Computing. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-03-17, 05:58 am


Karma: 90
Posts: 551/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
አራተኛው_ትውልድ ኮምፒዩተር ከ1970 ጀምሮ
.
ቀድሞ ከነበሩት ለየት የሚያደርጉት ነጥቦች
:->የማይክሮ ፕሮሰሰር በአዲስ መልክ መጠቀም መቻል
:->መረጃን መያዣ,ዳታን መቀበያና ውጤትን መግለጫ መሳርያዎች በተሻሻለ መንገድ መፈጠራቸው::
.
በአሁኑ ዘመን ያሉ ኮምፒዩተሮች ለየት የሚያደርጋቸው ዋነኛ ነጥብ በስፋት የተቀናጀ የኤሌክትሪክ ሲስተም በአንድ ቦርድ ላይ በቀላሉ በማቀናበር ስለሚጠቅሙ ነው:: በዚህ ምክንያት የግል ኮምፒዩተሮች በቅርፅና መጠናቸው እጅግ በጣም አነስተኛ ሆነው መሰራት አስችለዋል:: ከዚህም በተጨማሪ እንደ ክራይ (Cray) እና ሳይበር (Yyber) የተባሉ ሱፐር ኮምፒዩተሮችን ለትልልቅ አገልጎሎቶች እንደ ጠፈር ምርምር ያሉ አገልግሎቶችን ለማቅለል ያግዛሉ::
.
ማይክሮ ፕሮሰሰር (Microprocessor) የምንለው ከአተር ፍሬ ያነሰ አንድ ኮምፒዩተር ማድረግ የሚችለው የቁጥር እና ነገሮችን የማገናዘብ ስራ ማከናወን የሚችል የኮምፒዩተር አካል ነው:: ከዚህም የተነሳ አራተኛ ትውልድ ኮምፒዩተሮች...
.
->እጅግ ፈጣን በዋጋም ከቀድሞ ይልቅ እየረከሰ መምጣቱ የተሰጠውን ስራ በተሻለ መልኩ ማከናወን መቻሉ::
->በዋጋ በብዙ ያልተወደዱ ለግለሰብ የሚያገለግሉ ኮምፒዩተሮች በብዛት መወራታቸው::
->ከዚህም በተጨማሪ እጅግ በጣም አነስተኛ ለአያያዝ የሚመቹ ኮምፒዩተሮች መሰራታቸው ከማይክሮ ፕሮሰሰር መሰራት የተነሳ ነው::

Pages: 1