ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 09-02-17, 08:58 am (rev. 1 by ጮሌው on 09-02-17, 08:58 am)


Karma: 100
Posts: 294/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
⚽ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ የክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዶሳንቶስ አቪየሮ የእግር-ኴስ የህይዎት ታሪክ፣ የዝውውር ሁኔታዎቹ፣ የግል ህይዎቱ እንዲሁም ሌሎች ተጨዋቹን የተመለከቱ ዳሰሳዎች! - ክፍል አንድ
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
በፕላኔታችን ኳስን በላቀ ደረጃ ከሚጫወቱ ሁለት ተጨዋቾች አንዱ ፤እንደ አጥቂም እንደ ክንፍ ተጨዋችም ቢጫወት ጎል እንዳሻው የሚያገባ፤ኳስ ከፍጥነቱ ከፍጥነቱ ሳይደናቀፍ የሚያንከባልል ጨራሽ የፍፁም ቅጣት ምት ስፔሻሊስት፤አንድ ለአንድ ማንኛውንም ተከላካይ የሚያሸብር ...
_______________________________________
✔ ይህ የዛሬ ኮከብ የሴት ቅድመ አያቱ ኤልዛቤል ዳፒዳድ በአፍሪካዊቷ ሀገር ኬፕ ቨርዴ የተወለዱ ናቸው፤ከአንድ ወንድሙ እና ከሁለት እህቶቹ ጋር በአንዲት ክፍል ውስጥ ኑሮን ለማሸነፍ እንደተጋ የልጅነት ታሪኩ ያስረዳል፤ታዲያ በአንድ ወቅት ይህንን ህይወታቸውን በእግር ኳስ ብቻ ለመቀየር ከእናቱ ጋር ይስማማል፤ለዚህም የሀገሩን ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ይቀላቀላል በ15 አመቱ ግን እግር ኳስን እንዲያቆም የሚያስገድድ የልብ ህመም እንዳለበት ይታወቃል፤በእናቱ ስምምነት መሰረት ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ወደ እግር ኳስ ይመለሳል፡፡
_______________________________________
✔ ስፖርቲንግ ሊዝበን እያለ በ2002 ከአርሰን ቬንገር ጋር ተገናኝቷል ወደ ሊቨርፑል የመሄድ እድልም ነበር በመሀል ግን ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና ዩናይትድ ትኩረት ውስጥ ገባ፤በ2003 ስፖርቲንግ ሊዝበን ማንቼስተር ዩናይትድን በወዳጅነት ጨዋታ 3ለ1 አሸነፈ፤ያኔ የማንቼስተር ተጨዋቾች ወሬ ሁሉ ስለ ሮናልዶ ሆነ ወዲያውኑ ይሄ ልጅ ወደ ማንቼስተር ዩናይትድ እንዲመጣ ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን መወትወት ጀመሩ፡፡
_______________________________________
✔ በ2003-04 የውድድር ዘመን በ£12.4m ሮናልዶ ቀያይ ሰይጣኖቹን ተቀላቀለ ፤እነ ጆርጅ ቤስት፣ብሪያን ሮብሰን፣ኤሪክ ካንቶና ዴቪድ ቤካም የለበሱትን 7ቁጥር መለያ ለበሰ፤ባለተሰጥኦ ተጨዋች የማንቼስተርን ውድ ቁጥር ፈርጉሰን መረጡለት፤የክርስቲያኖ ሮናልዶ ተዐምር ገና በመጀመሪያው ጨዋታ ከቦልተን ወንደረርስ ጋር ታየ፤አዲስ የእግር ኳስ ሰው መወለዱ እውን ሆነ፤ከሁለት የውድድር አመታት በኃላ ደግሞ ክርስቲያኖ ሮናልድ የኦልድትራፎርድ ቁንጮ ተጨዋች ሆነ፡፡
_______________________________________
✔ በ2006-07 የውድድር ዘመን ከ20 በላይ ጎሎችን አስቆጠረ ፤በሊጉም በ2008 ከዩናይትድ ጋር ፕሪሚየር ሊጉን እና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን አነሳ፤በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 42 ጎሎችን በማስቆጠር ምርጥ ተጨዋችነቱን አስመሰከረ ፤በ2008 በዩናይትድ ባሳየው ምርጥ እንቅስቃሴ የተነሳ ክርስቲያኖ ሮናልድ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማትን አገኘ፡፡
_______________________________________
✔ ያኔ ኮከብ የሚያሳድዱት ማድሪዶች የኦልድ ትራፎርድን በር ማንኳኳት ጀመሩ፤ሮናልድ ከኦልድ ትራፎርድ ይለቃል እየተባለም ግን ማን ዩናይትድ በዚህ ጥበበኛ ፖርቹጋላዊ ጎል አምራችነት ለተከታታይ 3አመታት የፕሪሚየር ሊጉን አነሳ(ከ2007-09)፡፡በ2009 ዩናይትድ እንደገና ከባርሴሎና ጋር ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ደረሰ፤ባርሰሎና በዚህ ጨዋታ 2ለ0 አሸነፈ፤ያ ጨዋታ ሮናልዶ የዩናይትድን ማሊያ የለበሰበት የመጨረሻው ትልቅ ጨዋታ ሆነ፡፡
_______________________________________
✔ ከሳምንታት በኃላ የዝውውር ሪከርድ በጥበበኛው ኮከብ ተሰበረ ማድሪድ £80m ከፈለ፤ሮናልዶ የልጅነት ህልሜ ወዳለው ሳንቲያጎ ቤርናቦ ተዘዋወረ፤አዲሱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ታታሪው ጋላክቲኮን ተቀላቀለ፡፡
_______________________________________
✔ በሳንቲያጎ ቤርናቦ በመጀመሪያው አመት ብቻ በ35 ጨዋታዎች 32ግቦችን አስቆጠረ ፤በ2010-11 የውድድር ዘመን ደግሞ የላሊጋው ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ የፒቺቺው አሸናፊ ሆነ፤በ34 ጨዋታዎች 40ግቦችን በማስቆጠር፤ሪያል ማድሪድ ባርሰሎና በኮፓ ዴል ሬይ በዚህ ዘመን ሲያሸንፍ የማሸነፊያ ጎሏ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሆነች፡፡
_______________________________________
✔ በሪያል ማድሪድ ሮናልዶ መነሳቱን አላቆመም በየጊዜው የሚጨምር የማይታመን ብቃት የሚያሳይ የጎል ማሽን ሆነ፤በ2011-12 ላሊጋውን ከማድሪድ ጋር ወሰደ፤በ38 ጨዋታዎች 46 ጎል በማስቆጠር ኮከብ ሆነ በዚህ ወቅት የፊፋ ባሎንዶርን ሌላ ልዩ ብቃት ባሳየው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ተነጠቀ እንጂ ሮናልዶ መሸለም ነበረበት ብለው የሚከራከሩት በርካታ ናቸው ከዚህ በኃላም ሁለት ባሎንዶሮችን ሁለት ሻምፒዮንስ ሊጎችን እና ባሳለፍነው አመት ደግሞ የአውሮፓ ዋንጫን ከሀገሩ ጋር አሳክቷል...ቀጣይ የህይወት ታሪኩ ይቀጥላል በክፍል ሁለት ይጠብቁን!

Pages: 1