ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-02-17, 07:11 am (rev. 1 by Ye Arada Lij on 09-02-17, 07:13 am)


Karma: 90
Posts: 550/887
Since: 02-29-16

Last post: 206 days
Last view: 206 days
"ለሰው ልጅ መልካም ትልቁ ደስታ መልካም ትዳር ነው!
:
# ሴት ሆይ ለትዳርሽ ብቁ ነሽን?!"
:
➊.ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ
{ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➋.ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➌.ባለቤትሽ በተቆጣ ጊዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት ከሆነ፣ድምፅሺን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➍.ከባለቤትሽ አጠገበ በተቀመጥሽ ጊዜ ጠረንሽ ጥሩ ካልሆነ፣የልብስሽን ንፅህና ካልጠበቅሽ፣እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➎.ከሱጋ በተጣላሽ ወቅት ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➏.ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የሱን ቤተሰቦች መልካምን በማድረግ የማትንከባከቢ ከሆንሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➐.በፀሎት ጊዜ እሱን የማትቀሰቅሺ ከሆንሽ፣ ፈጣሪን በመታዘዝ ላይ የማተበረታቺው ከሆነ፣ ክልክል ነገራቶችን እንዲተው የማታደርጊ እና ወደ ተውበት የማትገፋፊው ከሆንሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➑.ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
❖❖~❖❖~❖❖< >❖❖~❖❖~❖❖
:
# ወንድ ሆይ ለትዳርህ በቁ ነህን?
:
➊.ሚስትህ ምቾት እና እንክብካቤ ስለምትፈልግ
ካልተንከባከብካት እና ያለህን ነገር በሙሉ ሳትሰስት ካላጋራሃት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➋.ሚስትህ ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። ባገኘከው አጋጣሚ ከንፈሯን እየሳምክ ፍቅርህን የማትገልፅላት ከሆነ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➌.ሚስትህ ግትር ባል ትጠላለች። ደካማ ባልን ደግሞ ትንቃለች አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር መሆንን ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➍.ሚስትህ መልካም ንግግር፣ ወንዳ ወንድ ገጽታ፣ በስፖርት የተገነባ ሰውንት፣ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ይማርካታል እነዚህን ማድረግ ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➎.ለሚስትህ ቤቷ ቤተ መንግስት ነው። ይህን ቤተመንግሥቷን ካስደፈርክባት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➏.ሚስትህ እጅግ በጣም ብትወድህም ቤተሰቦቿን ማጣት አትፈልግም። ቤተሰቦቿን ብትንከባከብ ከነበረው ፍቅር ላይ ሌላ ፍቅር ትጨምራለህ ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➐.ሚስትህ አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ይህን ባህሪዎቿን ባትወድላት ሌሎች የሚወደዱ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት ከዘነጋህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➑.ሚስትህ አካላዊ ድካም፣ ተፈጥሯዊ ወይንም ወራዊ ህመም እና ስነልቦናዊ ጫና እየተፈራረቁ ስለሚያጠቋት ልትነጫነጭ ትችላለች። ይህን ዘንግተህ እሷን ከመንከባከብ ፈንታ አንተም
እንደሷ ከተነጫነጭክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➒.ባገኘሁ አጋጣሚ ሚስትህን እቀፍ፣ ሳም፣ ፀጉሯን ወገቧን እሽ ሚስትህ ላንተ ሁሌም ቆንጆ እንደሆንች አስመስክር። ሚስትህ እንደ አንተ አልጋ ላይ የፍቅር ጨዋታ ያምራታል በግልፅ ፍላጎቷን በሚገባ አርካት ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➓.ሚስትህ እንደ አቅሟ ተውባ እና አጊጣ መታየትን ትፈልጋለች።
:
✔የመጀመሪያ የውበቷ አድናቂ ቧልዋ መሆኑን አትዘንጋ ስለዚህ ሁሌም ውበቷን አድንቅላት።
:
✔ሚስትህ ተውባ እና አጊጣ ማየት ካልፈለክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
➊➊.ደስታን፣ ሀዘንን፣ ችግርን እና ቅሬታን ለሚስትህ በግዜ ንገራት። ደስታውን አመስግኑ። ሀዘኑን ተፅናኑ፣ ችግርን እና ቅሬታን ብቻችሁን በውይይት ፍቱ። ሚስትህን በፍፁም አታኩርፍ እንዚህን መምራት ካቃተህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➊➋.ሚስትህ ስትናገር እስከመጨረሻው በጥሞና ካላደመጥካት ችግሯን ካልፈታህላት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➊➌.ከፈጣሪ ቀጥሎ ከምንም እና ከማንም በላይ መጀመሪያ አንተ፣ ሚስትህ፣ እና ልጆችህን ብቻ አስቀድም። ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት እና ሌላው ከእናንተ ቀጥሎ ናቸው። ይህን ማስተዋል
ከተሳነህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
❖❖~❖❖~❖❖< >❖❖~❖❖~❖❖

# ወዳጆቼ፥

እንግዲህ ፈጣሪ የራሳችሁ በሆነ ሰው ባርኮ የስጣችሁ፡፡

በተረፈ ፈጣሪ ላገባነውም ላላገባነውም ማስተዋል ይስጠን

Posted on 09-03-17, 04:49 pm


Karma: 100
Posts: 383/625
Since: 08-27-16

Last post: 160 days
Last view: 20 days
Pages: 1