ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-30-17, 05:32 am


Karma: 100
Posts: 289/741
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 19 days
⚽ ረቡዕ ጠዋት የወጡ በርካታ ተጨዋቾችንና ክለቦችን የተመለከቱ የዝውውር ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎች አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ ወሬዎች!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
አርሰናሎች ለአሌክሲስ ሳንቼዝ ከማንቸስተር ሲቲ የቀረበላቸውን የ£50m የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አደረጉ እንደ Sky Sources መረጃ፡፡

ኢንተር ሚላን ለአርሰናሉ ተከላካይ ሽኮድራን ሙስጣፊ አዲስ ጥያቄ አቀረበ፡፡ኢንተር ተጨዋቹን በውሰት በ£4.6m በመውሰድ በ£23m በቋሚነት የማስፈረም አንቀጽ እንዲካተትበት አድርጎአል፡፡(Sky in Italy)

ጆሽ ኪንግ በበርንማውዝ አዲስ የአራት አመት ኮንትራት ፈረመ፡፡የፕሪሚየርሊጉ ክለብም አረጋግጦታል፡፡በቪታሊቲ ስታዲየም እስከ 2021 ይቆያል፡፡

ሊቨርፑል ለማማዱ ሻኮ ከክሪስታል ፓላስ ለ3ኛ ጊዜ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡ያቀረቡት ዋጋ £22m + ብቃቱ እየታየ የሚጨመር £3m ሲሆን ሊቨርፑል ለተጨዋቹ £30m ለጥፎበታል፡፡(Sky Sources)

ቼልሲ የኤደን ሃዛርድን ወንድም ኪሊያን ሃዛርድ አስፈረመ፡፡ሃዛርድ በ2015 ከዙልቲ ዋሬግም አንሴትን ከተቀላቀለ በኃላ 42 ጨዋታዎችን አድርጎአል፡፡

ሞናኮ ኬይታ ባልዴን በ£27.9m ለማስፈረም ከላዚዮ ጋር ከስምምነት ላይ ደርሶአል፡፡ባልዴ ከቶማስ ሌማር ጋር በማጥቃት ዘይቤው ተመሳሳይ ሲሆን በቶተንሃም እና ጁቬንቱስ ይፈለጋል፡፡(Sky in Italy)

ምንም እንኳን በዋጋው አርሰናል እና ቼልሲ ቢስማሙም አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌይን ሊቨርፑልን መቀላቀል ይፈልጋል፡፡(BBC)

ቼልሲ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ስኳዳቸውን ለማጠናከር ለቶተንሃሙ አማካይ ሮዝ ባርክሌይ £25m አቅርበዋል፡፡(Daily Telegraph)

ጆዜ ሞሪንሆ የሌስተር ሲቲውን የክንፍ ተጨዋች ሪያድ ማህሬዝ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ማምጣት ይፈልጋሉ፡፡ተጨዋቹ ቀበሮዎቹን ለመልቀቅ ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ ሞሪንሆ የዩናይትድ ባለስልጣናት እንዲያስፈርሙላቸው እየሞከሩ ነው፡፡(SFR Sport)

አትሌቲኮ ማድሪድ ዲያጎ ኮስታን ከቼልሲ ዳግም ለማስፈረም ንግግር እያደረገ መሆኑን ተከትሎ በ£41m የቀድሞ ክለቡን ለመቀላቀል ተቃርቦአል፡፡(Evening Standard)

ዌስትብሮም የፒኤስጂውን አማካይ ግሪጎር ሪቾዋክ ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር በአሸናፊነት አጠናቀቀ፡፡ቼልሲ እና ጁቬንቱስ ከአማካዩ ጋር ቢያያዙም ባጌዎቹን በውሰት ውል ለመቀላቀል ተቃርቦአል፡፡(The Sun)

ሞናኮ ፋቢንሆን ለፒኤስጂ የሚለቅ ከሆነ በምትኩ ዊሊያም ካርቫልሆን ለማስፈረም ይመለከታሉ፡፡የስፖርቲንጉ አማካይ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ፍላጎት ቢሆንም በ€35m ወደ ስታዴ ሉይዝ || ሊዛወር ይችላል፡፡(L'Equipe)

ሞናኮዎች ለቶሪኖው አጥቂ አንድሪያ ቤሎቲ €80m ሊያቀርቡ ነው፡፡አጥቂው በክረምቱ ከአርሰናል፣ ቼልሲ እና ኤሲ ሚላን ጋር ተያይዞአል፡፡(La Stampa)

ሊቨርፑል የ25 አመቱን ብራዚላዊ አማካይ ፊሊፔ ኩቲንሆ በ£148m ለባርሴሎና ለመሸጥ ከስምምነት ላይ ደርሶአል፡፡(Yahoo Sport)

አርሰናሎች በመጨረሻም አሌክሲስ ሳንቼዝን ለማንቸስተር ሲቲ በ£30m + ራሂም ስተርሊንግ ሊለቁት ተዘጋጅተዋል፡፡(Mirror)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★

Pages: 1