ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing General Foods. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-29-17, 08:20 pm


Karma: 100
Posts: 349/426
Since: 07-12-15

Last post: 472 days
Last view: 472 days
የስኳር ድንች 7 የጤና በረከቶች

1. በጣፋጭ ጣዕሙ የሚታወቀው ስኳር ድንች በቫይታሚን ቢ የበለጸገ ሲሆን፥ ይህም በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ሆሞሳይቶሲን በመቀነስ ለልብ ህመም የመዳረግ እድልን ይቀንሳል፡፡

2. ስኳር ድንች በቫይታሚን ሲ የበለጸገ ነው፤ በመሆኑም ለአጥንት ጥንካሬና ለሰውነታችን የምግብ መፈጨት ሂደት ሁነኛ ግብዓት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በስኳር ድንች ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ሲ ቁስል በፍጥነት እንዲደርቅ ይረዳል፡፡

3. ስኳር ድንች ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ዲ የሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅምን በማሳደግ ለአጠቃላዩ ጤናችን መጠበቅ ይረዳል፡፡

4. በስኳር ድንች ውስጥ ያለው የብረት ማዕድን ለቀይ እና ለነጭ የደም ህዋሳት ምርት ይረዳል፡፡

5. በስኳር ድንች ውስጥ ከፍተኛ ማግኒዚየም በመኖሩ ሳቢያ፥ ስኳር ድንችን አዘውትሮ መመገብ በከፍተኛ ሁኔታ የመጨናነቅ ስሜትን ያስወግዳል፡፡

6. ስኳር ድንች በፖታሲየም የበለጸገ መሆኑም የልብ ምትን የማስተካከልና የነርቭ ህዋሳትን ስራ የማነቃቃት ብቃት አለው፡፡

7. ስኳር ድንች በተፈጥሮ በስኳር የበለጸገና እንደመሆኑ መጠን ፥ ስኳር ድንች ውስጥ ያለው ስኳር ወደ ደም የሚሰራጨው ቀስ በቀስ ነው፤ ይህም የተመጠነና የተስተካከለ ስኳር ወደ አካላችን ስርዓት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

8. ሼር፣ ላይክ እና ታግ ማድረግዎን አይርሱ


ምንጭ፦ ጤና አዳም

Posted on 08-30-17, 07:05 am


Karma: 100
Posts: 302/365
Since: 07-14-15

Last post: 651 days
Last view: 92 days
Tn'x Melu
Posted on 08-30-17, 02:06 pm


Karma: 100
Posts: 374/627
Since: 08-27-16

Last post: 8 days
Last view: 1 day
Pages: 1