ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing General Foods. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-29-17, 08:13 pm


Karma: 100
Posts: 347/426
Since: 07-12-15

Last post: 65 days
Last view: 65 days
ስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች
8 ምርጥ ምግቦች

ውድ ቤተሰቦች… እናንተ ለእኛ ውድ ናችሁ…
ለስኳር ህሙማን የሚሆን መድሃኒት መስጠት ባንችልም እነሆ በአመጋገብ በኩል እንዳትቸገሩ ይቺን መረጃ ይዘንላችሁ መጥተናል… እንደምትወዱት እና ሼር እንደምታደርጉት አንጠራጠርም፡፡

1) አሳ:- የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል 40% ይቀንሳል።

2) ባቄላ እና ዘሮቹ:- ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና እንዳይርብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

3) እንቁላል(በመጠኑ):- እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል መብላት ኮለስትሮልንም ከፍ አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።

4) ገብስ:- ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።

5) የአበሻ አይብ:- የአበሻ አይብ ከአብዛኞቹ አይቦች የሚለየው ቅቤው የውጣለት መሆኑ ነው። አይብ በካልሲዩምና በፕሮቲን የበለጸገ ነው። እንደ አይብ አይነት የወተት ምርቶችን በበቂ መጠቀም insulin resistance (የስኳር በሽታ ዋነኛው ችግር) ይዋጋል።

6) የወይራ ዘይት:- በአንዳንድ የጤና አኳያ ሲታይ የወይራ ዘይት ፈሳሽ ወርቅ ነው ተብሎ በብዙዎች ተሰይሟል። የወይራ ዘይት ከፍተኛ anti inflamatory ባህሪይ አለው። ይህ ደግሞ ስኳርን እና የልብ በሽታን የሚዋጋ ባህሪይ አለው ማለት ነው።

7) ስኳር ድንች:- ለምሳሌ ያህል በድንች ፋንታ ስኳር ድንች መብላት ደም ውስጥ ያለው ስኳር 30% ያህል ከፍ እንዳይል ያግዛል። ስኳር ድንች በበሽታ ተከላካይ ፋይበር የበለጸገ ነው። ከዛ ውስጥ 40% የሚሟሟና ኮለስተሮልን የሚቀንሱና digestion በፍጥነት እንዳይካሄድ የሚረዱ ናቸው። ሌላ ደግሞ በ ኦሬንጅና ቢጫ carotenoids የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም ሰውነታችን ለ insulin respond እንዲያደርግ ይረዳሉ። ከዛ በተረፈ በ chlorogenic acid የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም የስኳር በሽታ መንስኤ የሆነውን insulin resistance ይዋጋሉ።

8) ቀይ ስጋ በመጠኑ:- ቀይ ስጋ በ ፕሮቲን የበለጸገ እና ሰውነታችን ጮማ ከሚሆን በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በጡንቻ እንዲተካ ይረዳል።

9) ውድ የሳይቴክ ቤተሰቦች… ለስኳር ህሙማን የሚሆን መድሃኒት መስጠት ባንችልም እነሆ በአመጋገብ በኩል እንዳትቸገሩ ይቺን መረጃ ይዘንላችሁ መጥተናል… እንደምትወዱት እና ሼር እንደምታደርጉት አንጠራጠርም፡፡

ጤና ለሁሉም!

--------------------------
ምንጭ - ጠቃሚ ብሎግ

Pages: 1