ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-27-17, 05:56 pm


Karma: 100
Posts: 285/741
Since: 03-20-17

Last post: 29 days
Last view: 21 days
⚽ Transfer Updates እሁድ ከሰአት በኃላ የወጡ ትኩስ የዝውውር ዜናዎች፣ የተጠናቀቁ ዝውውሮች፣ በርካታ ክለቦችንና ተጨዋቾችን የተመለከቱ አዳዲስ መረጃዎች እንዲሁም ሌሎች አጫጭር የእግር ኳስ ወሬዎች!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ! ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ሊቨርፑሎች የአርሰናሉን አማካይ አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌይን ለማስፈረም £40m+£1m አቅርበዋል፡፡እንግሊዛዊው አማካይ በአርሰናል አዲስ ኮንትራት አለመፈረሙን ተከትሎ በሊቨርፑል እና በቼልሲ ይፈለጋል፡፡(The Sun) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ማንቸስተር ሲቲ ጆኒ ኢቫንስን ለማስፈረም £30m እንዲሁም ኤሊያኩም ማንጋላ በውሰት ለዌስትብሮም አቅርበዋል፡፡ፔፕ ጋርዲዮላ የቀድሞውን የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ በማስፈረም የተከላካይ ክፍላቸውን እንደሚያጠናክሩ ተስፋ አድርገዋል፡፡(The Sun) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ዜናዎቻችን ይቀጥላሉ...!
➖➖ ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ አርሰናሎች የሪያል ማድሪዱን አጥቂ ማርኮ አሰንሲዮ በዝውውር ፍላጎታቸው ውስጥ አሰልፈውታል፡፡የ21 አመቱ አጥቂ በአለም ዋንጫው ለመሳተፍ በሳንቲያጎ በርናባኦ አዲስ ኮንትራት አልፈረመም፡፡(Sunday Express) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ሊቨርፑሎች በፊሊፔ ኩቲንዮ ዝውውር ጉዳይ ከባርሴሎና ጋር ለመደራደር እስከ ሰኞ ድረስ ቀነ-ገደብ አስቀምጠዋል፡፡የካታላኑ ክለብ የኡስማን ዴምበሌን ዝውውር ማጠናቀቁን ተከትሎ የቀዮቹ ኮኮብ ቀጣይ ኢላማቸው ነው፡፡(Onda Cero) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ሌስተር ሲቲዎች የማንቸስተር ዩናይትዱን ተከላካይ ክሪስ ስሞሊንግ ለማዛወር ኢላማቸው አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡(Daily Mirror) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ኤቨርተን የቼልሲ የዝውውር ኢላማ የሆነውን የሌስተር ሲቲውን አጥቂ ጄሚ ቫርዲ በ£40m ለማስፈረም አቅደዋል፡፡(Sky Sport) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ አርሰናሎች አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌይንን በዚህ ሳምንት ለቼልሲ ሊለቁት ይችላሉ፡፡(Mirror) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ የአርሰናሉ ተከላካይ ሽኮድራን ሙስጣፊ ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል ከስምምነት ደረሰ፡፡ነገር ግን ሁለቱ ክለቦች ድርድሩን አላጠናቀቁም፡፡ኢንተር ሙስጣፊን በረዥም ጊዜ የውሰት ውል ወስደው እንደ አማራጭ የመግዛት አንቀጽ እንዲካተት ይፈልጋሉ፡፡(Sky in Italy) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ሞናኮ ኬይላን ምባፔን ለፒኤስጂ የሚለቅ ከሆነ ለሌስተር ሲቲው አጥቂ ኢስላም ስሌማኒ ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ሞናኮዎች ኬይላን ምባፔን ለፒኤስጂ በሚቀጥሉት 72 ሰአታት ውስጥ እንደሚሸጡት ይጠበቃል፡፡(Sky Sources) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ አሁን በወጡ አዲስ መረጃዎች ሽኮድራን ሙስጣፊ አርሰናልን ለቅቆ ኢንተር ሚላንን በውሰት የሚቀላቀል ከሆነ አርሰን ቬንገር የዌስትብሮሙን ተከላካይ ጆኒ ኢቫንስ ለማስፈረም ይመለከታሉ፡፡(The Mail) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ጆዜ ሞሪንሆ እንዳረጋገጡት ዝላታን ኢብራሂሞቪች ለማንቸስተር ዩናይትድ በጥር ወር መጫወት እንደሚጀምር ታውቆአል፡፡ስዊዲናዊው አጥቂ በኦልትራፎርድ የአንድ አመት ውል ፈርሞአል፡፡ ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ የባርሴሎናው አለቃ ኤርነስቶ ቫልቬርዴ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ተጨማሪ ተጨዋቾችን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡(Sky Sports) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ እንደ Sky Sports መረጃ ሰርጂ ኦሪዬር በ£23m ወደ ቶተንሃም የሚያደርገውን ዝውውር እውን ለማድረግ የሜዲካል ምርመራውን አጠናቅቆአል፡፡ ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ አርሰናሎች አሌክሲስ ሳንቼዝ ማንቸስተር ሲቲን የሚቀላቀል ከሆነ የሪያል ማድሪዱን የ29 አመት አጥቂ ካሪም ቤንዜማ ሊያስፈርሙ ይችላሉ፡፡(Diario Gol) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ዋትፎርድ የአርሰናሉን ተከላካይ ኬራን ጊብስ ለማስፈረም ከመድፈኞቹ ጋር ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡ነገር ግን ከተጨዋቹ ጋር በመርህ ደረጃ ከስምምነት አልደረሱም፡፡(Sky Sources) ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★

Pages: 1