ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-26-17, 12:14 am


Karma: 100
Posts: 280/755
Since: 03-20-17

Last post: 17 days
Last view: 17 days
አርብ ከሰአት በኃላ የወጡ በርካታ ተጨዋቾችንና ክለቦችን የተመለከቱ የዝውውር ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎች አጫጭር ትኩስ ሰፊ የእግር ኳስ ወሬዎች!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
✔ የሞናኮው የክንፍ ተጨዋች ቶማስ ሌማር አርሰናልን ከመቀላቀል ይልቅ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ መዛወር ይመርጣል፡፡ፈረንሳዊው ኮከብ በክረምቱ ከመድፈኞቹ ጋር ቢያያዝም የቀድሞ የቡድን አጋሩን አንቶኒ ማርሻል ፈለግ በመከተል ቀያይ ሰይጣኖቹን ለመቀላቀል ይፈልጋል እንደ Duncan Castles መረጃ፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ጁቬንቱስ አንድሬ ጎሜዝን ለማስፈረም ፍላጎት ማሳደሩን ተከትሎ ከባርሴሎና ጋር ከስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም፡፡ባርሳ ተጨዋቹን በውሰት ለቅቆ በግዴታ የመግዛት አንቀፅ እንዲካተትበት ቢፈልግም ጁቬ ተጨዋቹን በውሰት ወስዶ ብቃቱ እየታየ በቋሚነት የማስፈረም አንቀፅ እንዲካተት ይፈልጋሉ፡፡(Tuttosport)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ሰርጂ ኦሪየር ቶተንሃምን ለመቀላቀል ተቃርቦአል፡፡የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ከፒኤስጂ ጋር ከስምምነት የደረሰ ሲሆን ከተጨዋቹ ጋር በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሶአል፡፡(L'Equipe)
✔ ቼልሲ የስዋንሲ ሲቲውን አጥቂ ፈርናንዶ ሎሬንቴን የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት በ£15m ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል፡፡(Daily Telegraph)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ኦሊቨር ዥሩድ በአርሰናል ለመቆየት መወሰኑን ተከትሎ ማርሴይ የሊቨርፑሉን አጥቂ ዳይቮክ ኦሪጊ ለማስፈረም እያጤኑበት ነው፡፡(Marseille Mercato)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★

✔ ኤሲ ሚላኖች የባርሴሎናውን አማካይ ራፊንሃ የክረምቱ የመጨረሻ ፈራሚያቸው በማድረግ ለማዛወር ፍላጎት አሳይተዋል፡፡(Calciomercato)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ የናፖሊው ግብ ጠባቂ ፔፔ ሬይና ፒኤስጂን ለመቀላቀል ተቃርቦአል፡፡የቀድሞው የሊቨርፑል እና የባርሴሎና ተጨዋች ለዝውውሩ €7.5m ይወጣበታል፡፡(Goal)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ከሳምንታት ድርድር በኃላ ባርሴሎና ኡስማን ዴምበሌን ለማስፈረም ከቦርሺያ ዶርትመንድ ጋር ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡የዝውውር ዋጋው £110m ሲሆን የአምስት አመት ኮንትራት ለመፈረም በግሉ ተስማምቶአል፡፡(Sky Sources)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ [የተረጋገጠ] ምንም እንኳን ክላውዲዮ ራኒዬሪ መልቀቃቸውን ተከትሎ በጥር ወር የመልቀቂያ ደብዳቤ ቢያስገባም ሊዮናርዶ ዮላ በሌስተር ሲቲ እስከ 2019 የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ፈርሞአል፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ [የተረጋገጠ] የሳውዝሃምፕተኑ ተከላካይ ማያ ዮሺዳ በክለቡ የሚያቆየውን አዲስ የ3 አመት ኮንትራት ፈርሞአል፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ [የተረጋገጠ] ዌስትብሮም በ£15m የRB Leipzig የክንፍ ተጨዋች ኦሊቨር ቡርኬን ዝውውር አጠናቀቀ፡፡የ20 አመቱ ተጨዋች የአምስት አመት ኮንትራት የፈረመ ሲሆን የ17 ቁጥር ማልያን ይለብሳል፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ የዌስትሃሙ አለቃ ስላቪያን ብሊች የስፖርቲንግ ሊዝበኑን አማካይ ዊልያም ካርቫልሆ ዝውውር እንደሚያጠናቅቁት እርግጠኛ ሆነዋል፡፡(Guardian)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ፒኤስጂ ለአንሄል ዲማሪያ ከባርሴሎና የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡ዲማሪያ የረዥም ጊዜ የባርሴሎና ኢላማ ቢሆንም የካታላኑ ክለብ €35m አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበታል፡፡(AS)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ቀያይ ሰይጣኖቹን ዳግም ለመቀላቀል ከሳምንታዊ ደመወዙ ላይ ከ£200,000 በላይ ቀንሶአል፡፡(Times)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ ቼልሲዎች በሚቀጥለው ሃሙስ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የአርሰናሉን አማካይ አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌይን እንደሚያስፈርሙት እርግጠኛ ሆነዋል፡፡(Daily Telegraph)
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
Pages: 1