ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-24-17, 07:35 pm (rev. 2 by ጮሌው on 08-24-17, 07:40 pm)


Karma: 100
Posts: 278/755
Since: 03-20-17

Last post: 17 days
Last view: 17 days
⚽ ሃሙስ ምሽት የወጡ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ ሊዮኔል ሜሲ፣ ጋሪ ካሂል፣ አንሄል ዲማሪያ፣ ጁሊያን ድራክስለር፣ ዊሊያን፣ ኤደን ሃዛርድ እንዲሁም ሌሎችን የተመለከቱ በርካታ ሰፊ የዝውውር ዜናዎች!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!

ማንቸስተር ዩናይትዶች ዝላታን ኢብራሂሞቪችን በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈረሙ፡፡የ35 አመቱ አጥቂ በኦልትራፎርድ የ10 ቁጥር ማልያን ይለብሳል፡፡(Manchester United)

ጁቬንቱስ እንግሊዛዊውን የቼልሲ ተከላካይ ጋሪ ካሂል ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቶአል፡፡የሴሪኣው ሻምፒዮን ለሊዮናርዶ ቦኑቺ ተተኪ እያፈላለገ ነው፡፡(The Sun)

ጁሊያን ድራክስለር በፒኤስጂ ያለው ቆይታ ሊጠናቀቅ ይችላል፤ የተጨዋቹ ተወካይ ከባየርሙኒክ ጋር ለመደራደር ወደ ጀርመን አቅንቶአል፡፡(L'Equipe)

ማንቸስተር ሲቲዎች የሊዮኔል ሜሲን የውል ማፍረሻ €300m ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውን ተከትሎ የተጨዋቹ አባት ጆርጌ ከሲቲ ጋር ንግግር እያደረጉ ነው፡፡(The Sun)

ኬይላን ምባፔ ፒኤስጂን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱን ተከትሎ ሞናኮዎች ለሱ ተተኪ እየተመለከቱ ነው፡፡የአያክሱን አጥቂ ካስፐር ዶልበርግ በ€50m ወይም የሴልቲኩን ሙሳ ደምበሌ ሊያስፈርሙ ይችላሉ፡፡(L'Equipe)

✔ ጁቬንቱስ ሊቨርፑልን በመቀናቀን የሻልካውን ተከላካይ ቤኔዲክት ሆዌይስ ለማስፈረም አቅደዋል፡፡(Bild)

✔ የቼልሲው ኮከብ ኤደን ሃዛርድ ከማሬንጌዎቹ ጋር መያያዙን ተከትሎ ወደ ሪያል ማድሪድ ለመዛወር ማንኛውንም ድርጊት ሊያደርግ ይችላል፡፡(Don Balon)

ባርሰሴሎናዎች ለኔይማር ተተኪ የቼልሲውን የመስመር ተጨዋች ዊሊያን ለማስፈረም አቅደዋል፡፡ብራዚላዊው ተጨዋች በአንቶኒዮ ኮንቴ ስር ህይዎትን ለመልመድ አስቸጋሪ ሆኖበታል፡፡(France Football)

✔ ሻልካ ኮከባቸውን ሊዮን ጎሬዝካ በሚቀጥለው አመት በነጻ ለቡንደስሊጋው ተቀናቃኝ ባየርሙኒክ ከመልቀቅ ይልቅ ለባርሴሎና አቅርበውታል፡፡ጎሬዝካ በJune 2018 ኮንትራቱ ይጠናቀቃል፡፡(Mundo Deportivo)

✔ የማንቸስተር ሲቲው ተከላካይ ኤሊያኩም ማንጋላ ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል ተቃርቦአል፡፡በተጨማሪም ሽኮድራን ሙስጣፊ እና ሁዋን ፎይዝ ኢላማዎቹ ናቸው፡፡(Sky Sport)

✔ ባርሴሎናዎች አንሄል ዲማሪያ በ€50m ለማስፈረም ከፒኤስጂ ጋር ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡በመርህ ደረጃም ቢሆን ከአጥቂው ጋር ተስማምተዋል፡፡(Sport)

የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ጆዜ ሞሪንሆ አንድሬስ ፔሬራን በውሰት ለቫሌንሲያ መልቀቅ ባለመፈለጋቸው ዝውውሩን አግደውታል፡፡ሞሪንሆ ተጨዋቹን በመጀመሪያው ቡድን ስኳድ ውስጥ ማካተት ይፈልጋሉ፡፡(Marca)

✔ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት አርሰናሎች ሉካስ ፔሬዝን ለቀድሞ ክለቡ ዲፖርቲቮ ላካሮኛ በ£14m ለመልቀቅ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡(Evening Standard)

✔ የቶተንሃሞቹ ጥንዶች ቪንሴንት ጃንሰን እና ኬቪን ዊመር ወደ ዌስትብሮም የሚያደርጉትን ዝውውር ለማጠናቀቅ ተቃርበዋል፡፡ዌስትብሮም በአጠቃላይ ለዝውውሩ £30m የሚያወጡ ይሆናል፡፡(The Sun)

✔ የአርሰናሉ አለቃ አርሰን ቬንገር አሌክሲስ ሳንቼዝ ከኮንትራቱ መጠናቀቂያ ባሻገር በክለቡ እንደዲቆይ እንደሚፈልጉ እንዲሁም አሌክስ አክስሌድ ቻምበርሌይን በኤምሬትስ እንዲቆይ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡(Sky Sport)

ማንቸስተር ሲቲዎች የኢስፓኞሉን ተከላካይ አሮን ማርቲን ለማስፈረም እየሞከሩ ነው፡፡አሮን እስከ 2022 ኮንትራቱን ያራዘመ ሲሆን የውል ማፍረሻው €40m ነው፡፡(Sport)

✔ የሳውዝሃምፕተኑ ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ ያለምንም ፈቃድ ከቼልሲ ሰዎች ጋር ተገናኝቶአል፡፡(Star)

✔ የባርሴሎናው አማካይ አንድሬ ጎሜዝ ክለቡ ከጂያን ሚሼል ሴሪ ጋር መያያዙን ተከትሎ ባርሴሎናን መልቀቅ ይፈልጋል፡፡ማንቸስተር ዩናይትድ የተጨዋቹ ዋነኛ ፈላጊ ነው፡፡(Corriere dello sport)

ቶተንሃም የክለቡ ሪከርድ በሆነ ዋጋ የአያክሱን ተከላካይ ዳቪንሰን ሳንቼዝ አስፈረመ፡፡የ21 አመቱ ተከላካይ ረቡዕ ዕለት የሜዲካል እና የወረቀት ስራውን ያጠናቀቀ ሲሆን የ6 ቁጥር ማልያን ይለብሳል፡፡

_______________________________________

Pages: 1