ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-23-17, 08:37 am


Karma: 100
Posts: 276/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
⚽ ስለ ኢቫን ፔሪሲች፣ ፊሊፔ ኩቲንሆ፣ ናቢ ኬይታ፣ አሌክስ ሳንድሮ፣ አሌክሲስ ሳንቼዝ፣ ቻምበርሌይን፣ አንድሬ ጎሜዝ እንዲሁም ሌሎችን የተመለከቱ የረቡዕ ረፋድ በርካታ ሰፊ የዝውውር ዜናዎች!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
ባርሴሎና £138m በማቅረብ ለ4ኛ ጊዜ የሊቨርፑሉን ኮኮብ ፊሊፔ ኩቲንሆ ለማስፈረም ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው፡፡እንደ Sky Sports መረጃ £101m ወዲያው የሚከፈል ሲሆን £37m በጉርሻ መልክ ይከፍላሉ፡፡
.
የቼልሲው አጥቂ ሚቺ ባትሹዋይ ስታምፎርድ ብሪጅን ለቅቆ ሊልን የመቀላቀል ፍላጎት የለውም፡፡የሊግ ዋኑ ክለብ ለዝውውሩ £36m አቅርቦ ነበር፡፡(London Evening Standard)
.
ኤቨርተኖች ለቤኔፊካው አጥቂ ራውል ጊሜንዝ £27.5m አቅርበዋል፡፡ነገር ግን የፖርቹጋሉ ክለብ ተጨዋቹን ለመልቀቅ £40m ይፈልጋል፡፡(The Sun)
.
ቼልሲ የሌስተር ሲቲውን አማካይ ዳኒ ድሪንክዎተር በ£30m ለማስፈረም ተቃርቦአል፡፡እንደ ጋዜጣው መረጃ ሰማያዊዎቹ ከዚህ በፊት £15m አቅርበው ውድቅ ሲደረግባቸው £40m ደግሞ ሌስተሮች የለጠፉበት ዋጋ ነው፡፡(The Mirror)
.
DONE DEAL| ሳውዝሃምፕተኖች የላዚዮውን ተመላላሽ ዌስሌይ ሆዬት ማስፈረማቸውን ይፋ አደረጉ፡፡
.
DONE DEAL| የቫሌንሲያው ተጨዋች ጆኦ ካንስሎ የሴሪኣውን ክለብ ኢንተር ሚላን ተቀላቀለ፡፡ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክለቡን በውሰት እስከ June 30 2018 የተቀላቀለ ሲሆን በቋሚነት የመግዛት አማራጭ አለው፡፡
.
ምንም እንኳን 2 ጊዜ ጥያቄዎችን አቅርበው ውድቅ ቢደረግባቸውም ቼልሲዎች ለጁቬንቱሱ ተመላላሽ አሌክስ ሳንድሮ €70m አቅርበዋል፡፡የጣሊያኑ ሻምፒዮን የተሻሻለ ኮንትራት በማቅረብ በቱሪን እንደሚያቆዩት እርግጠኛ ሆነዋል፡፡(Calciomercato)
.
አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌይን አርሰናልን መልቀቅ እንደሚፈልግ መናገሩን ተከትሎ ቼልሲ £35m ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡አማካዩ ኮንትራቱ ሊጠናቀቅ አንድ አመት ቀርቶታል፡፡(The Sun)
.
ማንቸስተር ዩናይትዶች የቫሌንሲያው ተከላካይ ኢዜኩዬል ጋሬይ እየተከታተሉ ካሉ ክለቦች ውስጥ ሆነዋል፡፡ቀያይ ሰይጣኖቹ ተወካያቸውን ባለፉት ሳምንት ወደ ስፔን ቢልኩም የቶተንሃም፣ የጁቬንቱስ እና የቤኔፊካ ኢላማ ነው፡፡(The Sun)
.
ማንቸስተር ዩናይትዶች ኢቫን ፔሪሲችን ለማስፈረም ከኢንተር ሚላን ጋር በከፍተኛ ደረጃ በንግግር ላይ ናቸው፡፡ነገር ግን ክሮሺያዊው አማካይ በክለቡ አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ይችላል፡፡(Star)
.
ባርሴሎና ለ2ኛ ጊዜ ፈረንሳዊውን አጥቂ ኡስማን ዴምበሌ ለማስፈረም £119m አቅርቦአል፡፡ነገር ግን ቦርሺያ ዶርትመንድ በትንሹ £138m ይፈልጋል፡፡(Sky Deutschland Via AS)
.
ጃክ ዊልሸር ከአርሰን ቬንገር ጋር መነጋገሩን ተከትሎ በአርሰናል ሊቆይ ነው፡፡ዌንገር የተጨዋቹ ስም ከኒውካስትል እና ሚላን ጋር ቢያያዝም በኤምሬትስ በመቆየት ቦታውን እንዲያስጠብቅ ነግረውታል፡፡(Daily Mirror)
.
የሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ የሻልካው ተከላካይ ቤኔዲክት ሆዌዲስ ላይ አተኩረዋል፡፡ቀዮቹ ቨርጂል ቫን ዳይክን ከሳውዝሃምፕተን እንደሚያስፈርሙት ተስፋ አድርገዋል፡፡(DW Sports)
.
ቶተንሃሞች በሰርጂ ኦሪዬር ዝውውር ከፒኤስጂ ጋር በ€25m ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበዋል፡፡ኦሪዬር የቼልሲ እና የማንቸስተር ዩናይትድ ኢላማ ቢሆንም ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር በግሉ ከስምምነት ላይ ደርሶአል፡፡(L'Equipe)
.
አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌይን በሊቨርፑል እና ቼልሲ መፈለጉን ተከትሎ በአርሰናል የቀረበለትን የኮንትራት ማራዘሚያ ውድቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡(The Telegraph)
.
አርሰናሎች አሌክሲስ ሳንቼዝን በ£70m ሊለቁት ይችላሉ፡፡ነገር ግን አርሰን ዌንገር በተጨዋቹ ላይ ያላቸው አቋም ክለቡን እንደማይለቅ ነው፡፡አሌክሲስ በኮንትራቱ መጨረሻ አመት ላይ መሆኑን ተከትሎ ከማንቸስተር ሲቲ £70m ቀርቦለታል፡፡(Daily Mirror)
.
ቼልሲዎች ለዲያጎ ኮስታ ተተኪ ለሌስተር ሲቲው አጥቂ ጄሚ ቫርዲ ድንገተኛ ጥያቄ ለማቅረብ እያጤኑ ነው፡፡ቼልሲ አልቫሮ ሞራታን ከሪያል ማድሪድ ካስፈረመ በኃላ ሌላ ሁነኛ አጥቂ ለማስፈረም ወደ ገበያው ወጥቶአል፡፡(Daily Mirror)
.
ጁቬንቱሶች የባርሴሎናውን አማካይ አንድሬ ጎሜዝ በረዥም ጊዜ የውሰት ውል የማስፈረም አቋም አላቸው፡፡በተጨማሪም እንደ አማራጭ ጁቬ የሮማውን ኬቪን ስትሮትማን ኢላማቸው አድርገውታል፡፡(Tuttosport)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★

Pages: 1