ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Pregnancy & Parenting . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-23-17, 05:53 am (rev. 2 by  ማማዬ on 08-23-17, 05:54 am)


Karma: 100
Posts: 88/95
Since: 08-19-16

Last post: 400 days
Last view: 400 days
እናት ከመውለዷ በፊት ብታቃቸው የሚጠቅሙ ነገሮች
--------------------------------------------------

ሴት ልጅ እናትነትን የምትረከብ የተፈጥሮ ፀጋ የተሰጣት ሰው ናት ስለዚህ ሴቶች እርግዝናን ስንጀምር እናትነትን ጀመርን ማለት ነው

ወደ ቤታችን የመጣን እንግዳ አስደስተን ለማጫወት የተለያዩ ምግቦችንና መጠጦችን በማቅረብ እንደምናስተናግድ ሁሉ አልፎ ተርፎም በሞቴ አፈር ስሆን ብሉልኝ ጠጡልኝ በማለት ግብዣችንን እናከናውናለን

ልጆች ለወላጆቻቸውና ለቤተሰብ እንዲሁም ለሀገር አስደሳችና ጠቃሚ እንግዶች ናቸው ስለዚህ ከፅንስ ጀምሮ እስከ ወሊድ ከዛም አሳድጎ እራስ እስከ ማስቻል ድረስ የሚመለከተው ሁሉ ኃላፊነት ስላለበት እንደ እንግዳ ቅድሚያ ተዘጋጅተን መጠበቅ ያስፈልጋል

ስለዚህ ፅንሱ ለመሰነፁ የተፈጥሮ ምልክቶች ሲታዩ ሀኪም ቤት ተሂዶ ማረጋገጥ ያስፈልጋል መሰነፁ ከተረጋገጠ በኋላ እናቶች ከመውለዳቸው በፊት ምን ቢያውቁ እና ምንና ምን ቢያዘጋጁ ጥሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ በሚል ከራሴም ልምድ በመነሳት የምችለውን ላካፍል ብዬ ነው

እነርሱም

1. እናት ጤነኛና ጠንካራ እንድትሆን የተመጣጠኑ ምግቦችንና ጤናማ መጠጦችን መመገብ አለባት

2. ያለአስፈላጊ ውፍረትና ቅጥነት እንዳይመጣ መጠንቀቅ አለባት

3. ከበፊቱ የበለጠ ንፅህና መጠበቅ አለባት

4. የህክምና ምርመራ መከታተል አለባት

5. አመቺ የሆነ ልብስና ጫማ መልበስ አለባት

6. ከሀኪም ትዕዛዝ ውጭ መድሀኒት መውሰድ የለባትም

7. ከአቅሟ በላይ የሆነ ስራ መስራት የለባትም

8. ዕረፍት ማድረግ አለባት

9. የመውለጃዋ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ለእራሷና ለቤተሰብ ወዘተ የሚሆን የበሰሉና ለማብሰል ቀላል ሆነው የተዘጋጁ የምግብ ጥሬ ግብአቶችን አዘጋጅቶ ማስቀመጥ ያስፈልጋል

10. በአካባቢው በአፋጣኝ ሀኪም ማግኘት የማይቻል ከሆነ የልምድ አዋላጅ ማዘጋጀት ያስፈልጋል

11. መውለጃ ጊዜ ሲደርስ ራቅ ያለ መንገድ ለብቻ መሄድ አይመከርም የግድ ከሆነ ከሰው ጋር መሄድ ይመረጣል

12. መውለጃ ቀን ሲደርስ በግቢና በቤት ውስጥ ብዙ እንቅስቃሴ ማድረግ ይመከራል

13. ለህፃኑ መቀበያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች ቅድሚያ ተዘጋጅተው መቀመጥ አለባቸው

14. ወዲያው ልጁን እንደተገላገለች ስለሚርብና ስለሚበርድ አጥሚት ወይም ቅባት ያልበዛበት ሾርባ መስጠትና ልብስ መደረብ ያስፈልጋል

15. በእርግዝናዋ ወቅት እንዳትወድቅ በመጠንቀቅ ቀስ ብላ መራመድና መሄድ አለባት

16. ድንገት ለመውለድ ባልተመቻቸ ቦታ ላይ ምጥ ቢመጣ ራስንና ሌላም ሰው ለመርዳት ሁሉም ሰው ስለ እትብት አቆራረጥ ተምሮ ቢገኝ እጅግ ጠቃሚና ነፍስ አትራፊ ሙያ ነው እላለሁ ስለሆነም በተፈለገው ቦታ ለመጠቀም ዝግጁ ሆና መጓዝ ያስፈልጋል

ይኸውም

ሀ. ተቀቅሎና ደርቆ የተዘጋጀ መቀስ ወይም ምላጭ
ለ. ንፁህ የሆነ ተገምዶ የተዘጋጀ ክር
ሐ. የህፃን መጠቅለያ ፎጣ
መ. ሞዴስ በቆሻሻ እንዳይበከል በንፁህ ጠቅልሎ እስከሚወለድ ድረስ በቦርሳ ይዞ መጓዝ ጠቃሚ ነው

የምጥ ምልክቶችንም ማወቅ ያስፈልጋል

እነርሱም

ሀ. አልፎ አልፎ ወደ ታች ጫን ጫን የሚል ምልክቶች መሰማት
ለ. ወደ ታች ጫን ጫን የሚለው ስሜት ፍጥነት መጨመር
ሐ. የእንሽርት ውሃ መፍሰስ
መ. መራመድ አለመቻል እና ከላይ የተጠቀሱት የመውለጃ ሰዓት መድረስ ምልክቶች ስለሆኑ ምጡ ሳይፋፋም በመጀመሪያው ምልክት ጊዜ ፈጥኖ ሀኪም ቤት መሄድ ወይም ከሌለ የልምድ አዋላጅ መጥራት ያስፈልጋል

ማሳሳቢያ

- ሀኪም ቤት የመጀመሪያ ምርጫ ነው ግን ከሌለ የልምድ አዋላጅ መጥራት የተሻለ ነው
Pages: 1