ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-22-17, 09:18 am (rev. 1 by ጮሌው on 08-22-17, 09:19 am)


Karma: 100
Posts: 275/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
⚽ ፒኤስጂ ኬይላን ምባፔን እና ፋቢንሆን ለማስፈረም መቃረቡን፣ ጁሊያን ድራክስለር፣ አንድሬስ ፔሬራ፣ ማቲዮ ኮቫቺች፣ ሚቼል ሴሪ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ማክሰኞ ጠዋት ላይ የወጡ የዝውውር ዜናዎች!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
ፒኤስጂ የሞናኮውን ኬይላን ምባፔ እና ፋቢንሆ ለማስፈረም ተቃርቦአል፡፡ለዝውውሩ በአጠቃላይ £200m የሚያወጡ ሲሆን ብራዚላዊው አጥቂ ሉካስ ሞራ የዝውውሩ አካል ሆኖ ሞናኮን ሊቀላቀል ይችላል፡፡(Sky Sport)
.
ክላውዲዮ ማርሽሊዮ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ጁቬንቱስን መልቀቅ ይፈልጋል፡፡ቼልሲ ማረፊያው እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ሪፖርቱ እንደጠቆመው አማካዩ ከጁቬው አለቃ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ ጋር የጠበቀ ግንኙነት የለውም፡፡(Corriere della sera)
.
ሳውዝሃምፕተን በቨርጂል ቫን ዳይክ ላይ የያዘውን አቋም የሚቀይር ከሆነ ሊቨርፑሎች ተከላካዩን ወደ አንፊልድ ለማዛወር ፍላጎት አላቸው፡፡ሳውዝሃምፕተን የላዚዮውን ተከላካይ ዌስሌይ ሄድት ለማስፈረም መቃረቡን ተከትሎ £60m የተለጠፈበትን ተከላካይ ሊለቁት ይችላሉ፡፡(Liverpool Echo)
.
የሪያል ማድሪዱ አማካይ ማቲዮ ኮቫቺች በንግግር ደረጃ ሊቨርፑልን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡ቀዮቹ ፊሊፔ ኩቲንዮን በባርሴሎና የሚነጠቁ ከሆነ የሱ ተተኪ ይሆናል ብለው ያስባሉ፡፡(Diario Gol Via Daily Mirror)
.
ማንቸስተር ሲቲዎች በጆኒ ኢቫንስ ላይ ያላቸውን ፍላጎት በማቋረጥ የሚዲልስብሮውን ተከላካይ ቤን ጊብሰን ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል፡፡(The Independent)
.
ጋላታሳራይ በአርሰናል የተገፋውን ኬራን ጊብስ ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቶአል፡፡ሪፖርቱ እንደጠቆመው የቱርኩ ክለብ ዝውውሩን በ£4m እንደሚያጠናቅቁ ተስፋ አላቸው፡፡(The Times)
.
ማንቸስተር ዩናይትዶች የፉልሃሙን ሪያን ሴሴኞን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል፡፡ተጨዋቹ የቶተንሃም የዝውውር ኢላማ ቢሆንም ጆዜ ሞሪንሆ ዝውውሩን ካጠናቀቁት በውሰት ለሻምፒዮንሺፑ ክለብ እንዲጫወት ለማድረግ ፈቃደኛ ናቸው፡፡(Sky Sports)
.
ቫሌንሲያ የማንቸስተር ዩናይትዱን አማካይ አንድሬስ ፔሬራ በረዥም ጊዜ የውሰት ውል ለማስፈረም ተቃርቦአል፡፡ፔሬራ ባለፈው አመት በውሰት ለግራናዳ መጫወቱ ይታወቃል፡፡(Cadena Cer Valencia)
.
የኒሱ አማካይ ጂያን ሚቼል ሴሪ በባርሴሎና የአራት አመት ኮንትራት ለመፈራረም ተስማምቶአል፡፡ባርሴሎና በፊሊፕ ኮቲንሆ እና የኡስማን ዴምበሌ ዝውውር እክል ስለገጠመው ሴሪን በ€40m ለማስፈረም ድርድር እያደረገ ነው፡፡(L'Equipe)
.
ባየርሙኒክ የፒኤስጂውን አጥቂ ጁሊያን ድራክስለር ለማስፈረም እያጤኑበት ነው፡፡የጀርመኑ ሻምፒዮን ለቀድሞው የዎልፍስበርግ አጥቂ €40m ለማውጣት ፈቃደኛ ነው፡፡(Westdeutsche Allgemeine Zeitung)
.
የአርሰናሉ አጥቂ ቹባ አክፖም በሻምፒዮንሺፑ ክለብ ሊድስ ዩናይትድ እና በስኮቲሹ ሻምፒዮን ሴልቲክ ይፈለጋል፡፡አክፖም በመጀመሪያ ቡድን ለመሰለፍ ስለሚፈልግ አርሰናልን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው፡፡(Daily Mirror)
.
እንደ Sky Sports መረጃ ፒኤስጂ ለኬይላን ምባፔ የውሰት ውል አቅርቦአል፡፡ሉካስ ሞራም የዝውውሩ አካል ሆኖ ሞናኮን ይቀላቀላል፡፡እንደ መረጃው ከሆነ ከUEFA Financial Fair ጋር በተያያዘ ስምምነቱ በሚቀጥለው ክረምት በቋሚነት የመግዛት አማራጭ ተካቶበታል፡፡
.
እንደ The Sun ጋዜጣ መረጃ አትሌቲኮ ማድሪዶች ዲያጎ ኮስታን ከማስፈረማቸው በፊት ከቼልሲ ጋር ሰላም እንዲፈጥር ይፈልጋሉ፡፡
.
ሮናልድ ኪዩመን ከትናትናው ጨዋታ በኃላ አንድ ተከላካይ ከሳንድሮ ራሚሬዝ እና ዶሚኒክ ካልቨርት በተጨማሪ ሌላ አጥቂ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡(Sky Sport)
.
የፈረንሳዩ ክለብ ሊል የቼልሲውን አጥቂ ሚቺ ባትሹዋይ በ£36m ለማስፈረም ተዘጋጅቶአል፡፡ቼልሲ ተጨዋቹን ባለፈው ክረምት በ£33m ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡(Daily Mirror)
.
ዋትፎርድ የቤኔፊካውን አጥቂ አንቶሬ ካራሎ በውሰት ውል ለማስፈረም ተቃርቦአል፡፡የፔሩው ተጨዋች በአጥቂ እና በመስመር ላይ መጫወት ይችላል፡፡
.
ኒኮላ ካሊኒች ወደ ኤሲ ሚላን የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ የሜዲካል ምርመራውን እያደረገ ነው፡፡የጣሊያኑ ሚዲያ እንደጠቆመው የፊዮሬንቲናው አጥቂ በ£4.6m ለአንድ አመት በውሰት የሚቀላቀል ሲሆን በቋሚነት በ£18.3m የማስፈረም አማራጭ አለው፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★

Pages: 1