ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-21-17, 07:15 am


Karma: 100
Posts: 273/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
ሊዮኔል ሜሲ፣ ኬይላን ምባፔ፣ ሬናቶ ሳንቼዝ፣ አንድሬስ ኢኔስታ፣ ካሪም ቤንዜማ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ ኡስማን ዴምበሌ እንዲሁም ሌሎችን የተመለከቱ የሰኞ ጠዋት በርካታ የዝውውር ዜናዎች!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
አርሰናሎች ከቼልሲ የሚቀርብላቸውን ጥያቄ ለማቆም ለአሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌይን በሳምንት £125,000 የሚያስገኝለትን አዲስ የአራት አመት ኮንትራት አቅርበውለታል፡፡
.
ዝላታን ኢብራሂሞቪች በማንቸስተር ዩናይትድ አዲስ ኮንትራት ለመፈራረም ከጫፍ ደርሶአል፡፡ጆዜ ሞሪንሆ ተጨዋቹ ከጉልበት ጉዳቱ ሲያገግም እንደገና የማስፈረም ተስፋ አላቸው፡፡(ESPNFC)
.
ቼልሲዎች የቶተንሃሙን ተከላካይ ቶቢ አልደርዌርልድ የማስፈረም አቋም አላቸው፡፡ቤልጂየማዊው ተከላካይ በሰሜን ለንደን አዲስ ኮንትራት ባለመፈረሙ ሰማያዊዎቹ የሚያገኘውን ሳምንታዊ £49,000 ደመወዝ እጥፍ አድርገው ለመክፈል ፈቃደኛ ናቸው፡፡(The Sunday Times)
.
ማንቸስተር ሲቲዎች የባርሴሎናውን ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል፡፡የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ የሜሲን የውል ማፍረሻ €300m በመክፈል ወደ ኢትሃድ ለማዛወር ተዘጋጅቶአል፡፡(Yahoo Sports France)
.
የሞናኮው አጥቂ ኬይላን ምባፔ ባለፈው ማክሰኞ ከአንድሪያ ራጊ ጋር ከተነታረከ በኃላ የክለቡን የትሬይኒንግ ማዕከል ለቅቆ ወጥቶአል፡፡የ18 አመቱ አጥቂ በዚህ ክረምት ወደ ፒኤስጂ የሚያደርገው ዝውውር እንዲጠናቀቅለት እየገፋ ይገኛል፡፡(L'Equipe)
.
ቼልሲ የአማካይ ምርጫውን ለማስፋት የፒኤስጂው አማካይ ግሪዞር ክሪቶዋች ላይ አተኩሮአል፡፡ሰማያዊዎቹ የ27 አመቱን ፖላንዳዊ አማካይ በውሰት ውል ለማስፈረም ዝግጁ ናቸው፡፡(The Sun)
.
የኒውካስትሉ አለቃ ራፋኤል ቤኔቴዝ የዌስትሃሙን አንዲ ካሮል እና የአርሰናሉን አማካይ ጃክ ዊልሸር ለማስፈረም ይፈልጋሉ፡፡ባለቤቱ ማይክ አሽሊ ባለባቸው የፋይናንስ ችግር ምክንያት ሁለቱ ተጨዋቾች በውሰት ሊዛወሩ ይችላሉ፡፡(The Mirror)
.
ዌስትሃሞች ዊልያም ካርቫልሆን ከስፖርቲንግ ሊዝበን ማስፈረም ካልቻሉ የፒኤስጂው ግሪዜጎር ክሪቾዊያች ለማስፈረም ይመለከታሉ፡፡ክሪቾዊያች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ወደ እንግሊዝ መዛወር ይፈልጋል፡፡(The Mirror)
.
አንድሬስ ኢኔስታ በባርሴሎና ያለው ኮንትራት በሚቀጥለው ክረምት መጠናቀቁን ተከትሎ በክለቡ አዲስ ኮንትራት እንዳልተፈራረመ ገልጾአል፡፡(Sky Sport)
.
በማንቸስተር ሳቲ የተገፋው ሳሚር ናስሪ ወደ አንታሊስፖር የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ወደ ቱርክ አቅንቶአል፡፡ናስሪ ባለፈው አመት በውሰት ለሲቪያ የተጫወተ ሲሆን ሲቲ ለዝውውሩ £12m ይፈልጋል፡፡(The Mail)
.
BREAKING የሊድስ ዩናይትዱ አጥቂ ክሪስ ውድ ወደ በርንሌይ በ£15m የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ የሜዲካል ምርመራውን ለማድረግ ወደ ማንቸስተር ከተማ ተጉዞአል፡፡
.
ጆዜ ሞሪንሆ በቼልሲ ከ2012/13 በኃላ በማንቸስተር ዩናይትድ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለ2ኛ ጊዜ ለማንሳት የፒኤስጂውን የመስመር ተጨዋች ጁሊያን ድራክስለር እና የሪያል ማድሪዱን ተከላካይ ራፋኤል ቫራን ማስፈረም ይፈልጋሉ፡፡(Sky Sport)
.
ቦርሺያ ዶርትመንድ የባርሴሎናውን የዝውውር ኢላማ ኡስማን ዴምበሌ ክለቡን እንዲለቅ ሊፈቅዱለት ይችላሉ፡፡ነገር ግን ይሄ የሚሆነው የተጠቁት ዋጋ ሲከፈላቸውና ዝውውሩን ካስቀመጡት ቀን በፊት የሚያጠናቅቁት ከሆነ ብቻ ነው፡፡(Sportbild)
.
የሴሪኣው ሻምፒዮን ጁቬንቱስ ከባየርሙኒክ ጋር ያላቸውን አወንታዊ ግንኙነት በመጠቀም የኤሲ ሚላኑን የዝውውር ኢላማ ሬናቶ ሳንቼዝ ወደ ቱሪን የመውሰድ ተስፋ አላቸው፡፡(Calciomercato)
.
ኢንተር ሚላን እና ሮማ የሳምፕዶሪያውን ፓትሪክ ሼክ ወደ ሳን ሲሮ የመውሰድ ፍላጎት አላቸው፡፡ሳምፕዶሪያ የኢንተሩን አጥቂ ኤደን የዝውውሩ አካል አድርጎ መውሰድ ቢፈልግም ሉቺያኖ ስፓሌቲ ዝውውሩን አግደውታል፡፡(Gazzetta dello sport)
.
የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ካሪም ቤንዜማ በነሃሴ ወር መጨረሻ ላይ በቤርናባኦ የሚያቆየውን አዲስ የሁለት አመት ኮንትራት ሊፈራረም ይችላል፡፡ፈረንሳዊው አጥቂ በቤርናባኦ 9ኛ አመቱ ላይ ሲሆን አሁን ያለው ኮንትራት ያለው በ2019 ይጠናቀቃል፡፡(Journal du Dimanche)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
_______________________________________

Pages: 1