ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-20-17, 05:38 am (rev. 2 by ጮሌው on 08-20-17, 05:42 am)


Karma: 100
Posts: 269/769
Since: 03-20-17

Last post: 375 days
Last view: 375 days
⚽ አሌክሲስ ሳንቼዝ፣ ኬይላን ምባፔ፣ ማርኮ አሰንሲዮ፣ ጁሊያን ድራክስለር፣ ማቲዮ ኮቫቺች፣ ዴቪድ ዴሂያ፣ ዲማሪያ፣ ፊሊፕ ኮቲንዮ፣ ኒኮላ ካሊኒች እንዲሁም ሌሎችን የተመለከቱ የእሁድ ጠዋት ላይ የወጡ በርካታ የዝውውር ዜናዎች!

ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አትርሱ!
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
ምንም እንኳን አርሰናሎች ቺሊያዊውን አጥቂ ለመሸጥ ድርድር መቀመጥ ባይፈልጉም ማንቸስተር ሲቲዎች በአሌክሲስ ሳንቼዝ ላይ ተስፋ ባለመቁረጥ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት £70m ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል፡፡(The Mirror)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ኮንትራቱ በሚቀጥለው ክረምት መጠናቀቁን ተከትሎ አርሰናሎች ጃክ ዊልሸርን ለኤሲ ሚላን አቅርበዋል፡፡ዊልሸር ፕሪሚየር ሊጉን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባይሆንም ከሴሪኣው ክለብ ጋር ተያይዟል፡፡(Corriere dello sport)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ቼልሲዎች የአንቶኒዮ ኮንቴን የዝውውር ኢላማዎች ለማስፈረም £200m ሊበጅቱ ነው፡፡ቨርጂል ቫን ዳይክ፣ ሴድሪክ ሶሬስ፣ ሪያን በርትራንድ፣ ዳኒ ድሪንክዎተር እና አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌዬን ኢላማቸው ናቸው፡፡(Express)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
የኔይማር ፒኤስጂን መቀላቀል በማስመልከት ጁሊያን ድራክስለር ክለቡን እንዲለቅ ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ የፕሪሚየር ሊጉን ክለቦች ማንቸስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል እና ሊቨርፑል ትኩረት ስቦአል፡፡የዝውውር ዋጋውም £32m ነው፡፡(Mirror)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
አትሌቲኮ ማድሪዶች ዲያጎ ኮስታን ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ከቼልሲ ጋር በ€55m ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡€45m ወዲያው የሚከፈል ሲሆን €10m ብቃቱ እየታየ የሚጨመር ይሆናል፡፡(Radio Estadio, Programme on the Spanish Station Onda Cero, Via AS)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ፒኤስጂ የሞናኮውን አጥቂ ኬይላን ምባፔ ዝውውር ይፋ ሊያደርግ ነው፡፡የ19 አመቱ አጥቂ በ€180m በእግር ኳስ ታሪክ ሁለተኛው ወዱ ተጨዋች ይሆናል፡፡ምባፔ በፓርክ ዴስ ፕሪንስ በአመት €18m ይከፈለዋል፡፡(Mundo Deportivo)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ሪያል ማድሪዶች የማርኮ አሰንሲዮን ኮንትራት እስከ 2023 ድረስ በማደስ የውል ማፍረሻውን ወደ €500m ከፍ ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡አሰንሲዮ የአርሰናል ሁነኛ ተፈላጊ ቢሆንም ማድሪድ ለተጨዋቹ በአመት €4.5m በመክፈል በቤርናባኦ ለማቆየት ፍላጎት አለው፡፡(Marca)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ባርሴሎናዎች አዲስ ፈራሚዎችን በማፈላለግ መሆናቸውን ተከትሎ ለኒሱ አማካይ ጂያን ማይክል ሴሪ €30m አቅርበዋል፡፡ባርሳ ለፊሊፕ ኮቲንዮ ለ3ኛ ጊዜ የተሻሻለ ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ስለተደረገበት ከሴሪ ጋር በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሶአል፡፡(Sport)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ሪያል ማድሪድ ለማቲዮ ኮቫቺች ከጁቬንቱስ የቀረበለትን የ€75m የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡ጁቬንቱሶች የአማካይ ክፍላቸውን ለማጠንከር እየተመለከቱ ቢሆንም ማድሪዶች ተጨዋቹን እንደማይሸጡት ነግረውአቸዋል፡፡(AS)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ዌስትብሮሞች ተጨዋቻቸው ጆኒ ኢቫንስ በማንቸስተር ሲቲ መፈለጉን ተከትሎ የሊቨርፑሉን ተከላካይ ማማዱ ሳኮ ለማስፈረም እየተመለከቱ ነው፡፡ሻኮ ባለፈው አመት በክሪስታል ፓላስ በውሰት ቢያሳልፍም ሊቨርፑል £30m ለጥፎበታል፡፡(BBC)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
የማንቸስተር ሲቲው አጥቂ ፓትሪክ ሮቤርትስ በውሰት ውል ወደ ሴልቲክ ለመመለስ ተቃርቧል፡፡እስከ አሁን ይፋዊ የሆነ ስምምነት ላይ ባይደርሱም በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ተጨዋቹ ባለፈው አመት በሁሉም ውድድሮች 11 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡(Evening Times)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ባርሴሎና የፒኤስጂውን የመስመር ተጨዋች ዲ ማሪያ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሶአል፡፡ኔይማር ወደ ፒኤስጂ መዛወሩን ተከትሎ የካታላኑ ክለብ የቀድሞው የሪያል ማድሪድ የአጥቂ አማካይ ላይ አተኩሯል፡፡(The Sun)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
Sky Sources ተረዳሁ ባለው መረጃ ቶተንሃሞች 2ኛ ፈራሚያቸውን የሳውዝሃምፕተኑን ግብ ጠባቂ ፓውሎ ጋዛኒጋ ዝውውር ለማጠናቀቅ ተቃርበዋል፡፡የ25 አመቱ ግብ ጠባቂ ከሁጎ ሎሪስ እና ሚቼል ቮርም ቀጥሎ 3ኛ ተመራጭ ግብ ጨባቂ ይሆናል፡፡
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
አትሌቲኮ ማድሪድ የግሪሚዮውን አጥቂ ሉዋን ለማስፈረም £18.3m አቅርቧል፡፡አትሌቲኮ ማድሪድ ዝውውሩን የሚያጠናቅቀው ከሆነ ተጨዋቹ በሚቀጥለው አመት የስፔኑን ዋና ከተማ ይቀላቀላል፡፡(Hora Zero)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
የቶተንሃሙ አለቃ ሞርሺዮ ፖቼቲኖ ዳቪንሰን ሳንቼዝን ከአያክስ ካስፈረሙ በኃላ ሌሎች 3 ተጨዋቾችን ለማስፈረም ይፈልጋሉ፡፡ኬይታ ባልዴ፣ ቼክ ዲዮፕ፣ ሮዝ ባርክሌይ፣ ሰርጂ ኦሪዬር እና ፓውሎ ጋዛኒጋ ዋነኛ ኢላማቸው ናቸው፡፡(Daily Mirror)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ኤሲ ሚላኖች ካርሎስ ባካን ለቪላሪያል መስጠታቸውን ተከትሎ ኒኮላ ካሊኒችን በ£22.9m ለማስፈረም ተቃርበዋል፡፡የቀድሞው የብላክበርን ሮበርሱ አጥቂ የሴሪኣው ክለብ አዲስ አጥቂ ለመሆን ከፍተኛ ንግግር እያደረገ ነው፡፡(Gazzetta dello sport)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
ማንቸስተር ዩናይትዶች የኤሲ ሚላኑን ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ማግኘት የሚችሉ ከሆነ ዴቪድ ዴሂያን ለሪያል ማድሪድ ሊለቁት ይችላሉ፡፡ዴሂያ በኦልትራፎርድ እስከ 2019 የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖረውም ጆዜ ሞሪንሆ ተተኪ የሚያገኙ ከሆነ ሊለቁት ይችላሉ፡፡(The Sun)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ለፊሊፕ ኮቲንዮ ከባርሴሎና የቀረበለትን የ£118m የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡ብርሃን ስፖርት እንደተረዳችው ተጨዋቹ ወደ ካምፕኑ መዛወር ቢፈልግም ክለቡ በተጨዋቹ ላይ ያለው አቋም ለሽያጭ አይቀርብም የሚል ነው፡፡(Sky Sports)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
አርሰናሎች የፒኤስጂውን የመስመር ተጨዋች ጁሊያን ድራክስለር ለማስፈረም ድንገተኛ የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው፡፡ጀርመናዊው አማካይ በፒኤስጂ ሌላ ክለብ እንዲፈልግ ስለተፈቀደለት £32m የሚያወጣ ክለብ ዝውውሩን ሊያጠናቅቀው ይችላል፡፡(The Times)
◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯◯
.
የተጠናቀቁ እንዲሁም የተራዘሙ ዝውውሮች!

ቫሌንሲያ የኢንተር ሚላኑን የመሃል ተከላካይ ጄይሰን ሙሪሎ በሁለት አመት የውሰት ውል አስፈረመ፡፡እንደ አማራጭ ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ በቋሚነት የመግዛት ፍላጎትም ተካቶበታል፡፡
.
የሌስተር ሲቲው ተከላካይ ኤሊዮት ሞሬ በኪንግ ፓወር እስከ 2019 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ የሁለት አመት ኮንትራት ፈረመ፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
Pages: 1