ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-19-17, 05:43 am


Karma: 90
Posts: 536/879
Since: 02-29-16

Last post: 69 days
Last view: 69 days
የስፖርት ማዕድ- ስፖርታዊ መረጃ ዎች እና የዝውውር ወሬዎች
የስፖርት መዓድ አብይ የዛሬ የውጪ ስፖርታዊ መረጃዎችንና የዝውውር ወሬዎችን እንደሚከተለው አቅርቦላችዋል
በቅርቡ ከቼልሲ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ በ40 ሚሊየን ፓውንድ የተዘዋወረው ሰርቢያዊው አማካኝ ኒማኒያ ማቲች ማንቸስተር ዩናይትድ ከቼልሲ የተሻለ ትልቅ ክለብ መሆኑን ተናግሯል፡፡’’ ማንቸስተር ይፈልግሀል ከተባልክ ለውሳኔ ምንም አትቸገርም፡፡ ቼልሲ ትልቅ ክለብ እንደሆነ አውቃለው፡፡ ቤኒፊካም በፖርተ,ቹጋል ትልቅ ክለብ ነው፡፡ ነገር ግን ማንቸስተር እይታ ሲታዩ ግን እንደሚበለጡ አያጠራጥርም፡፡ ምክንያቱም ማንቸስተር በቃ ማንቸስተር ነው፡፡ የገዘፈ ስም ያለው ክለብ፡፡’’ ሲል ሰርቢያዊው ተጫዋች አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ማንቸስተር ሲቲዎች የቀድሞውን የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ጆኒ ኢቫንስን ከዌስብሮም ለማስፈረም ከፍተና ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሲቲዎች ቀድሚያ ለተጫዋቹ ዝውውር ያቀረቡት የ18 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ ውድቅ ከተደረገባቸው በኋላ በድጋሚ 22 ሚሊየን ፓውንድ አቅርበዋል፡፡ የሰሜን አየርላንዱን የ29 ዓመት ለቀድሞ የዩናይትድ ተከላካይ ሲቲዎች በሳምንት 140 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ ለመክፈል አስበዋል፡፡ዝውውሩ ተሳክቶ የሚጠናቀቅ ከሆነ ኢቫንስ ለቀድሞ ከለቡ ተቀናቃኝ የመጫወት ዕድሉን ያገኛል፡፡ኢቫንስ በዩናይትድ ቤት አማራጭ ተከላካይ በመሆን ስኬታማ የሚባል ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ እስካሁን ባዘዋወሯቸው ተጫዋቾች ደስተኛ የሆኑ አይመስሉም፡፡ አሁንም በተለይ የተካላካይ ተጫዋች ለማስፈርም ከፍተኛ ጥረትና ትግል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊትም የጁቬንቱሱን ብራዚላዊ ተከላካይ ሳንደሮን ለማስፈረም ለሶስተኛ ጊዜ በ63ሚሊየን ፓውንድ ጥያቄ ቢያቀርቡም በጣሊያኑ ክለብ ግን ተቀባይነት ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ጁቬዎች የቼልሲን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡ ይህ በእንዲ እንዳለ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አጥቂው ዲያጎ ኮስታ ወደ ለንደን ተመልሶ ልምምዱን እንዲጀምር ጥያቄ ቢያቀርብም ተጫዋቹ ግን ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ በድጋሚ መመለስ እንደማይፈልግ አስረግጦ ተናግሯል፡፡
የብራዚላዊው አማካኝ ፊሊፕ ኩቲንሆ የዚህ የውድድር ዓመት ክለብ ማን ይሆናል የሚለው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም፡፡ የዝውውር መስኮቱ ሊጠናቀቅ ቀናት የቀሩት ሲሆን ባርሳዎች ተጫዋቹን ለማዘዋወር ተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረቡ ነው፡፤ ሊቨርፑሎችም ተደጋጋሚ እምቢታቸውን ቀጥለውበታል፡፡ኩቲንሆ በበኩሉ ቀዮቹን ለቆ ወደ ባርሴሎና ማምራት የሚፈልግ ሲሆን እንዲህ ዓይነት መልካም አጋጣሚ በህይወት ዘመን አንዴ ሊገኝ የሚችል መሆኑን ያምናል፡፡ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በበኩላቸው ተጫዋቹ እንደማይሸጥ በተደጋጋሚ በየሚዲያው እየወተወቱ ቢሆንም የሚናፈሰውን የዝውውር ወሬ ግን በፍፁም ለማስቆም አልተቻላቸውም፡፡ ባርሳ ኩቲንሆን ካላገኘው እያለ ነው፡፡ ሊቭርፑሎች ደግሞ በየትኛውም ዋጋ ፊሊፕ አንሸጥም ምላሻቸው ሆኗል፡፡ የዝውውር መስኮቱ ሊጠናቀቅ የሚቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ቢሆኑም ግን በውስጣቸው ለእግር ኳስ አፍቃሪው ይፋ የሚያደርጉት ትልቅ መልስ ይዘዋል፡፡
በካታሎኗ ውብ ከተማ ባርሴሎና በደረሰ ጥቃት 13 ሰዎች ከመሞታቸውም ባሻገር ብዙ ሰዎች መቁሰላቸው ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም ብዙዎች ጥልቅ ሀዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ሊዮኔል ሜሲም በኢንስታግራም ባስተላለፈው መልዕክት ’’የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ከተጎጂ ወገኖች ጎን መቆሜን ለማሳወቅ እወዳለው፡፡ የዓለም ህዝቦች ሳንከፋፈል በመዋደድ ያለ አንዳች ጥላቻ አብረን ብንኖር መልካም እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡’’ ሲል የፍቅር ያሸኝፋል መልዕክቱን ለዓለም ህዝብ አስተላልፏል፡፡

Pages: 1