ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 08-12-17, 05:32 pm


Karma: 100
Posts: 253/760
Since: 03-20-17

Last post: 18 days
Last view: 2 days
Breaking News From Hello Habesha
"ፌስ ቡክ እንዴት ከሀገር ይበልጥብሻል? "
በለንደን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1500 ሜትር ውድድር ፍፃሜ ላይ መጨረሻ12ተኛ የወጣችው አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በከባድ የስሜት መረበሽ ውስጥ መሆኗ እየተነገረ ይገኛል። እንደምንጮቻችን ከሆነ ከውድድሩ በኋላ ወደ ሆቴል ያቀናችው ገንዘቤ ከእህቷ ጥሩነሽ ዲባባ ጋር በሚያድሩበት ክፍል ውስጥ ስታለቅስ የነበረ ሲሆን እህቷ፣ ሃይሌ ዱቤ ጁሎና ገብረእግዚአብሔር ሲያፅናኗት ነበር። ሃይሌም "ስፖርት ሁሌም አዲስ ነው አይገመትም ማሸነፍም መሸነፍም ባንቺ አልተጀመረም ግን እንደውም በ 5000 ከነ አልማዝ ጋር እሮጠሽ ጥሩ ውጤት ታመጫለሽ" ብሎ አፅናናት። ከዛም ይላሉ ምንጮቻችን ከዛም በእነ ሃይሌ ምክር የተፅናናችው ገንዘቤ ወደ አልጋ ታመራለች ከመተኛቷም በፊት በሞባይል ስልኳ ወደ ፌስቡክ መንደር ስትገባ ስሟን የሚያጎድፍና የሚያንቋሽሹ በተለይም "ለገንዘብ ሲሆን ብቻ ነው እንዴ የምታሸንፈው?............ ከሀገር ጉዳይ ገንዘብን ነው የምታስቀድመው" የሚሉ ትችቶችና "ስምን መልአክ ያወጣዋል...ድሮም ገንዘቤ ያሉሽ ወደው አይደለም" የሚሉ ምፀቶች የአትሌቷን ምስል እያስደገፉ ለጠፉ እሷም አየቻቸው። ከዚህ በኋላ ነገር ተበላሸ ይላሉ ምንጮቻችን። በወረደባት የስድብ ጋጋታ ስታለቅስ አደረች። እህቷ ጥሩነሽም እንቅልፏን ትታ ለማባበል ብትሞክርም አልቻለችም ከአቅሟ በላይ ሲሆንባትም በስልክ ሃይሌን የተኙበት ክፍል ድረስ አስጠራችው በነገሩ በጣም የተበሳጨውም ሃይሌ "ቅድም እንደዛ መክሪያት አሁን በማይረባ ፌስቡክ እንዲህ መሆን ምንድን ነው?" ብሎ ዛሬ ብቻዋን እንተዋትና ነገ ስትረጋጋ እናናግራታለን ብሎ ወደ ተኛበት ክፍል ይመለሳል። በነጋታውም የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ልምምድ ለማድረግ ሁሉም አትሌቶች ቢገኙም ገንዘቤ ትቀራለች። ስልክ በተደጋጋሚምም ቢደወልላት አላነሳ አለች። ሃይሌና ገ/እግዚአብሔርም ወደ ክፍሏ ሄደው ለልምምድ እንድትወጣ ይነግሯታል። ገንዘቤ ግን እምቢ አለች። "አሁን በጣም አሞኛል አልችልም" አለች። አለመታመሟን የተረዳው ሃይሌ ግን " ስሜትሽ ይገባኛል ግን ፌስ ቡክ እንዴት ከሀገር ይበልጥብሻል? ፌስቡክ ላይ ማንም ያሻውን ያወራል አንቺ ምን አስጨነቀሽ? ይኸው በኔ ስም ፌስቡክ ከፍተው ያላሉኩትን ሁሉ እየፃፉብኝ አይደል!" ብሎ ሊያፅናናት ቢሞክርም አሻፈረኝ አለች። ወዲያውም በአትሌት ገ/እግዚአብሔር እና አቶ ዱቤ ጁሎ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተጠርቶ ገንዘቤ በጀርባ ህመም ምክንያት በ 5000 ሜትር እንደማትሳተፍ ለጋዜጠኞች ተናገሩ። በዚህም ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሃይሌ አልገኝም ብሎ ቀረ። በቀጣይ አትሌቷ ላይ ምን አይነት እርምጃ እንደሚወሰድ ግልፅ አይደለም።
****ተጨማሪ መረጃ
አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ በስሜ የተከፈቱ ሁሉ የፌስቡክ አካውንቶች የኔ አይደሉም እኔ ፌስቡክ አልጠቀምም ማለቱ ታውቋል።

Posted on 08-12-17, 05:49 pm


Karma: 100
Posts: 340/610
Since: 08-27-16

Last post: 84 days
Last view: 2 days
አይዞሽ፡አይዞሽ፡ብሎ፡እንደ፡ማበረታት፡
የልጅቷን፡ሞራል፡ያዋድቃሉ፡ልክ፡አይደለም።
ምቀኛ፡የሴይጣናዊ፡ሥራ፡የሉሃል፡ይሄ፡ነው።
እግዚአብሄር፡ጽናቱን፡ይስጣት።
Pages: 1