ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing ልጅነት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-10-17, 07:16 pm


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 08-10-17

Last post: 1090 days
Last view: 1079 days
……" የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ ሁን፤ ቢሆንም ደግነትህን
አትናገር!!"
፦………" ራሱን ያጎበጠ ሰው መቼም ሌሎችን አቅንቶ አያውቅም!!"
፦………" ችግርን በጥቅም ላይ እንደማዋል ጣፋጭ ነገር የለም!!"
፦……" የእብደት የመጀመሪያ ምልክት እራስን አዋቂ አድርጎ ማሰብ ነው!"
፦……" መጥፎ ቀን የምንለው መጥፎ ሃሳብ ያሰብንበት ቀን ነው!!"
፦………" ድህነትን አትፈርበት! የሚያሳፍርህ ነገር ቢኖር የአዕምሮ ድህነት
መሆኑን እወቅ!!"
፦………" ቃል ለመግባት የዘገየህ፤ ከገባህ ደግሞ የፈጠንክ ሁኑ!!"
፦………"የአንተን ውድቀት ለሚመኙ ስትል ራስህን አሻሽል!!"
፦………" መጀመሪያ ራስህን እወቅ! ጠንካራ ጎኖችህን ይበልጥ አጠንክርህ
በድክመትህ ላይ ፈጥነህ ዝመትባቸው!!"
፦………" የተፃፈውን ሁሉ አንብበህ በህሊና መዝገብህ ከመፃፍህ በፊት
በህሊናህ ሚዛንህ አብጠርጥር!!"
፦………" ምላስህን ካልጠበካት እስዋ አትጠብቅህም!!"
፦………"መከራን እና የተወረወረ ድንጋይን ዝቅ ብሎ ማለፍ ብልህነት
ነው!!"
፦………" መስጠት የማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ!!"
፦……" ራሱን ያወቀ ሰው ሁልጊዜ በኑሮው ደስተኛ ነው!!"
፦………" ጠንካራ ሞራል የህይወት ተስፋ ነው!!"
፦………" ጨዋ አንደበት የተዘጉ በሮችን ይከፍታል!!"
፦………" ዛሬን ስለነገ በመጨነቅ ካሳለፍከው ዛሬን በቅጡ መኖር
ተስኖሃል!!"
፦………" ቁርጡን ያወቀ ሰው ምርጫ ይኖረዋል!!"
Posted on 08-10-17, 07:40 pm


Karma: 100
Posts: 333/627
Since: 08-27-16

Last post: 41 days
Last view: 6 hours
በሄሎ፡ሀበሻ፡ሥም፡እንኳን፡ደህና፡መጣህ፡
የሚያጠግብ፡እንጀራ፡ከምጣዱ፡ያስታውቃል።
በዚሁ፡ቀጥል።
Posted on 08-11-17, 05:23 am


Karma: 90
Posts: 519/887
Since: 02-29-16

Last post: 373 days
Last view: 373 days
እንኳን ወደ ሄሎ ሀበሻ ቤተሰብ ተቀላቀልክ
Pages: 1