ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest | 2 bots
Pages: 1
Posted on 08-10-17, 08:51 am (rev. 1 by ጮሌው on 08-10-17, 08:51 am)


Karma: 100
Posts: 249/760
Since: 03-20-17

Last post: 18 days
Last view: 2 days
መሰረት መብራቴ እና ንብረት ገላው ተጣመሩ የተባለው ወሬ ሀሰት ነው Ethiopian artist’s #Meseret Mebrate and #Nibret Gelawe make their relationship official.- FALSE NEWS
አርቲስት መሠረት መብራቴ ጋር ደውልኩላት፤ ‹‹… በተዛመተው ሀሰተኛ ወሬ በጣም አዝኛለሁ፤ የሀሰት ወሬውን ሳያረጋግጡ የሚቀባበሉትም ይገርማል፡፡ እንዲህ ሀሰተኛ ወሬ እየወለዱ የሚያሰራጩ፤ የግለሰቦችን ሕይወት የሚበጠብጡ ልዑል እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው፡፡ … እኔ የራሴ ሕይወት አለኝ፡፡ … እንዲህ አይነት ልቦለድ ታሪክ ማራባት በባህላችንም ነውር፤ በእምነታችንም ኃጢአት ነው፡፡ … #Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)ስለደወልክልኝ አመሰግናለሁ፡፡
አርቲስት ንብረት ገላው፤ (እከ) ጋርም ደወልኩ፡፡ እንዲህም አለ፤ ‹‹ሠርጌን በፌስቡክ አይቼዋለሁ፡፡ የመልስ ጥሪ እየጠበኩኝ ነው፡፡ ... ወሬው ሀሰት ነው!›› ብሏል
***በማኅበራዊ ድረ ገጽ የተናፈሰው እና በቅብብሎሽ የሄደው ወሬ እንዲህ ይላል
የመሲና እከ ጉዳይ . . .
ከአርቱ ባሻገር በቤተ ክርስቲያን አገልጋይነታቸው የሚታወቁት ሁለቱ ተዋንያን ለለፉት 3 አመታት በድብቅ ግንኙነታቸውን ይፋ ማድረግ ጀምረዋል:: ላለፉት ሳምንታት በዱባይ እና ታይላንድ የሽር ሽር ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ጥንዶቹ ትላንት በአራራት ሆቴል የአትሌት ደራርቱ ቱሉ 25ኛ ዓመት የባርሴሎና ድልን በማስመልከት የተገኙት መሲና እከ በአደባባይ ፍቅሬ ብሎ ወደ መድረክ በመጥራት ጭምጭምታውን ይፋ አድርጎታል:: አትሌት ደራርቱ ቱሉም በመምጣታቸው ምስጋና ካቀረበች በኋላ ‹‹ለሠርጋችሁ ያብቃን ስትል መርቃቸዋለች›› መሉ ቪዲዮውን እሁድ በJTV ልዩ ልዩ ፕሮግራም ላይ ይቀርባል::
የሀበሻ ቆንጆ


Pages: 1