ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Athletics. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-04-17, 02:26 am


Karma: 90
Posts: 507/879
Since: 02-29-16

Last post: 7 days
Last view: 7 days
ኢትዮጵያ በዓለም ሻምፒዮና ያላት ውጤት
ኢትዮጵያ 15 ጊዜ በተካሄዱት የዓለም ሻምፒዮናዎች በሁሉም ላይ ስትሳተፍ ከአንዱ በስተቀር በሁሉም ሻምፒዮናዎች ላይ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ገብታለች፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም ሻምፒዮና በ25 ወርቅ፣ 22 ብር እና 25 ነሀስ በአጠቃላይ በ72 ሜዳሊያ ስታስመዘግብ፤ አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ኬኒያ፣ ጀርመን፣ ጃማይካና እንግሊዝን ተከትላ 7ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ከአፍሪካ ደግሞ ከኬኒያ ቀጥሎ 2ኛ ነች፡፡
ኢትዮጵያ ሻምፒዮናው ላይ ያገኘቻቸው 72 ሜዳሊያዎች በ19 ወንድና በ19 ሴት በድምሩ በ38 አትሌቶች የተመዘገቡ ናቸው፡፡
ለኢትዮጵያ ከተመዘገቡት 25 የወርቅ ሜዳሊያዎች ውስጥ 5ቱ በአትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ 5ቱ በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ 4ቱ በአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ በጠቅላላ በ3 አትሌቶች ብቻ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የወርቅ ሜዳሊያ ለአገራቸው በማስመዝገብ በሻምፒዮናው ስማቸውን በደማቁ ለማጻፍ ችለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በ15ቱም የዓለም ሻምፒዮናዎች 25 ወርቅ፣ 22 ብር እና 25 ነሀስ በአጠቃላይ በ72 ሜዳሊያዎች ስታስመዘግብ በፊንላንድ ሄልሲንኪ በተካሄደው በ10ኛው ፣ በሩሲያ ሞስኮ በተካሄደው በ14ኛው እና በቻይና ቤጂንግ በ15ኛው የተካሄዱት በቅድመ ተከተል ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡

ነገ ሐምሌ 28 በ16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አባዲ አዲስ፣ ጀማል ይመርና አንዱአምላክ በልሁ የሚሳተፉ ሲሆን በሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ ደግሞ ገንዘቤ ዲባባ፣ ጉዳፍ ፀጋዬ፣ በሱ ሳዶ እና ፋንቱ ወርቁን ይዛ ትሳተፋለች፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Posted on 08-04-17, 02:23 pm


Karma: 100
Posts: 310/610
Since: 08-27-16

Last post: 22 days
Last view: 10 days
አትሌቶቻችንን፡ቸርነቱ፡የማያልቅበት፡አምላክ፡ይርዳቸው።
እስቲ፡በሌላው፡ካልሆነ፡በነሱ፡ሥራ፡በጥሩ፡ሥም፡እንጠራ።
Pages: 1