ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing አማርኛ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-31-17, 02:32 am


Karma: 90
Posts: 501/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
- ንካው -

ጨርቄን ማቄን ጥዬ አንዲያ ሰቀባጥር፤
መዉደድህ አስክሮኝ አሞኝ ያንተ ፍቅር ፤
ከጎዳና ዉዬ ከጎዳና ሳድር፤
"በእንትና ያበደች" ብለዉ ሲያሽሟጥጡኝ፤
ያሣዘንኳቸዉ ደግሞ ከንፈር ሲመጡልኝ ፤
ካንተ ዉጪ ማየት አይኔም አልሆን ብሎት፤
ካንተ ዉጪ መስማት ጆሮዬም ተስኖት ፤
ለስምህ አዚሜ በስምህ ሰምልበት ፤
ስምህ ስሜ ሆኖ ኖሪያለሁ ስጠራበት፤
- ኧረ አነደዉም ዉዴ-
ከእግርህ ስር ወድቄ ስልህ እዘንልኝ ፤
ብዬ ስለምንህ ፍቅሬን ተረዳልኝ ፤
ከእኔጋር ለመኖር ለክብሬ አትመጥኝም፤
ከእኔ ለመጣመር ለትዳር አትሆኝም ፤
ብለህ ገፍትረከኝ ጥለከኝ ሄደሀል ፤
"አሰኪ አተለቃቅስ ንኪዉ" ብለኸኛል ፡፡
- ዛሬ -
ለክብሬ የሚመጥን ከእኔ ለመጣመር ፤
ለትዳር የሚሆን ከእኔ ጋር ለመኖር ፤
የእኔውን የጎድን አጥንት ፈጣሪ ሲሰጠኝ ፤
ልቤ ተደላድሎ ቀንቶኝ ስኖር አይተህ ፤
ይቅርታ ጠየቅከኝ ከእግሬ ስር ተደፍተህ፤
ይልቅስ ቀና በል ከእግሬ ላይ ተነሳ ፤
አንተ በሰራኸዉ ግፍ አንተዉ አታልቅሳ፤
እ ና ማ የ ኔ ዉ ድ
የፈሰሰ ዉሀ ዳግም ላይታፈስ፤
ከአፍ የወጣ ቃል ወደ ሗላ ላይመለስ፤
ባንተዉ አነጋገር ባንተዉኛ ቋንቋ ፤
ዛሬ የሌላነኝ አንተም " ንካዉ" በቃ ፡፡

Posted on 07-31-17, 03:35 pm


Karma: 100
Posts: 293/610
Since: 08-27-16

Last post: 21 days
Last view: 9 days
Pages: 1