ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Standards & Testing . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-28-17, 05:44 am


Karma: 90
Posts: 495/887
Since: 02-29-16

Last post: 343 days
Last view: 343 days
የፈተና ነገር … (ይህን ሳያነቡ እንዳያድሩ)
#ETHIOPIA | ሦስቱ ጓደኛሞች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ከዕለታት በአንዱ ቀን ወዲህና ወዲያ ሲንዘላዘሉና ዓለማቸውን ሲቀጩ… ምንም ሳያጠኑ ቀን ደረሰ።
ምን እናድርግ??? ምን ይሻላል???…ብለው ከተወያዩ በኋላ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ።
ሦስቱም ሙሉ ልብስ ለበሱ…በአቅራብያቸው ከሚገኘው ጋራዥ ገቡና ልብሳቸውን በመኪና ዘይትና ግራሦ አጨመላለቁና …ሆነ ብለው አርፍደው ወደ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ አቀኑ።
ወደ መፈተኛ ክፍላቸው አቅራብያ ሲደርሱ…ሌሎች ተማሪዎች ለፈተና ከተቀመጡ ቆይተዋል፤ ፕሮፌሰሩ ቆመው ፈተናቸውን እየፈተኑ ነው።
ሦስቱ ዘዴኛ ተማሪዎች እየተቅለሰለሱና ፀጉራቸውን እየፈተሉ ወደ ፕሮፌሰሩ ቀረቡና፦
"ፕሮፌሠር ይቅርታ! ለፈተናው በጊዜ ለመድረስ የተቻለንን ያህል ጥረናል… የውድ ጓደኛችን የሠርግ ፕሮግራም ላይ ነበርን…ለፈተናው ክብር በመስጠት ፕሮግራሙን አቋርጠን ወደዚህ እየመጣን እያለ መኪናችን ተበላሸች…እሷን ስንጠጋግን(የተበላሸ ልብሳቸውን እየጠቆሙ)ቆየንና…እየከነፍን ብንመጣም በሠዓቱ ለፈተናው መድረስ አልቻልንም…እኛም ይህን ሁሉ ሥንዘጋጅ ቆይተን ይሄ ነገር በመፈጠሩ አዝነናል…በእውነት ፕሮፌሠር በጣም ይቅርታ!!!…"
ፕሮፌሠሩም……… "አይዟችሁ ያጋጥማል…በቃ ከሦሥት ቀን በኋላ ሌላ ፈተና አዘጋጅቼ እፈትናችኋለሁ…እስከዚያው ሳትረበሹ ዝግጅታችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉ… አይዟችሁ ተረጋጉ…"
ብለው ተማሪዎቹን ይሸኟቸዋል።
ተማሪዎቹም…ፕሮፌሠሩን በማሞኘታቸውና ለዝግጅት ሦሥት ቀን ሙሉ በማግኘታቸው ተደስተው እየፈነጠዙ ሄዱ።
ሦስቱንም ቀን…ቀን ከሌት እያጠኑ በበቂ ሁኔታ ተዘጋጁ…የፈተናው ቀን ሲደርስ በልበ ሙሉነት ከሠዓቱ ቀድመው ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሄዱ።
ፕሮፌሰሩም በሠዓቱ ፈተናውን ይዘው መጡ…ሦስቱንም ተማሪዎች …ጥግ ለጥግ …አራርቀው ካስቀመጧቸው በኋላ…የጥያቄ ወረቀቱን አደሏቸው።
ሦስቱም ተማሪዎች ጥያቄዎቹን አንብበው…አመዳቸው ቡን አለ…ቀና ብለው ተያዩ…ዓይናቸው ላይ ተስፋ መቁረጥ ይነበብ ነበር።
የፈተና ወረቀቱ አራት ጥያቄዎችን ብቻ የያዘ ነበር………
እንዲህ ይነበባል………
1ኛ) ከሦስት ቀን በፊት የተጋቡትን ሙሽሮች ሥም ጥቀስ።(25 ነጥብ)
2ኛ) ሠርጉ የተካሄደበትን ትክክለኛ ቦታ ጥቀስ።(25 ነጥብ)
3ኛ) መኪናችሁ የተበላሸበትን ቦታ ሥም ፃፍ።(25 ነጥብ)
4ኛ) የተበላሸው መኪና የየትኛው ካምፓኒ ሥሪት ነው?(25 ነጥብ)
• ማሣሠብያ፦የሦስታችሁም መልስ ተመሳሳይ ካልሆነ ውጤታችሁ "F" ነው።
ተማሪዎቹ እስካሁን ፈተና ክፍል ውስጥ ናቸው።

Posted on 07-28-17, 08:56 am


Karma: 100
Posts: 248/365
Since: 07-14-15

Last post: 654 days
Last view: 95 days
Haha betam megerem neaw!
Posted on 07-28-17, 01:00 pm


Karma: 100
Posts: 279/627
Since: 08-27-16

Last post: 11 days
Last view: 1 day
Posted on 07-28-17, 08:12 pm


Karma: 100
Posts: 306/426
Since: 07-12-15

Last post: 476 days
Last view: 476 days
endezi aynet detective bahri yalachewn astemariwoch enaberetatalen
Pages: 1