ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Celebrities. | 2 guests
Pages: 1
Posted on 07-28-17, 05:26 am


Karma: 90
Posts: 494/840
Since: 02-29-16

Last post: 32 days
Last view: 32 days
ሰውን በመርዳት ከፍ እንበል | ‘’We rise by lifting others.’’ ~ Robert G. Ingersoll
#ETHIOPIA | ዶፍ ዝናብ፤ በረዶ የጣለ ለታ
በአዲስ አበባ ከተማ ዶፍ ዝናብ እየጣለ ነው፡፡ መኪኖች ከዶፍ ዝናብ፤ በረዶ ከቀላቀለው ዝናብ ለማምለጥ በሚመስል መልኩ ይከንፋሉ፡፡ ሲከንፉ በመንገድ ዳር ተጠልለው፤ የዝናብ ማባራት ለሚጠባበቅ መንገደኞች በጎማቸው ጎርፉን አልበስውት ይሄዳሉ፤ ይሮጣሉ፡፡
በዚህ መሀል ዘመናዊ መኪና፤ ፍሬቻ እያበራ ዝናብ ወደ ተጠለሉት በዝግታ ተጠጋ፡፡
ሾፌሩ መስታወቱን አውርዶ፤ እድሜ ጠገብ አዛውንቶችን በዝናብ ውስጥ መጫን ጀመረ።
ከአንድ አዛውንት በስተቀር ሌሎቹ ተሳፋሪዎቹ፤ ዝናብ ያዘለው ልብሳቸውን ይዘው ወደ መኪናው ውስጥ መግባት የፈለጉ አይመስሉም። ይልኙታ ይዟቸዋል፤ ይልኙታ ቀፍድዷቸዋል።
ማነው? ይሄ ደግ ልብ ያለው ኢትዮጵያዊ?
... ብዬ አንገቴን አስግጌ ስመለከት በቴሌቪዥን እና በፊልም ትወና የማውቀው አርቲስት ያየራድ ማሞ #Yayerad Mammo ነበር ።
በኢትዮጵያ ምድር እንዲህ ያሉ ደጋግ ልቦችን ያብዛልን ። አሜን!

Posted on 07-28-17, 05:32 pm


Karma: 100
Posts: 281/603
Since: 08-27-16

Last post: 34 days
Last view: 7 hours
Posted on 07-29-17, 12:13 am


Karma: 100
Posts: 328/439
Since: 07-20-15

Last post: 41 days
Last view: 41 days
ይመችህ ያይራድ
Posted on 07-30-17, 05:57 am


Karma: 90
Posts: 496/840
Since: 02-29-16

Last post: 32 days
Last view: 32 days
ጥሩ ስራን ማበረታታት ያስፈልጋል
Pages: 1