ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing General Foods. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-24-17, 09:26 pm


Karma: 90
Posts: 491/879
Since: 02-29-16

Last post: 37 days
Last view: 37 days
ሰባት የነጭ ሽንኩርት ጥቅሞች
ነጭ ሽንኩርት አሊውም( Alium) ወይም ከሽንኩርት ቤተሰብ አንዱ ነው። ይህ የሽንኩርት ቤተሰብ አንዱ የሆነው ነጭ ሽንኩርት ለጤናችን ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል ከነዚህ ውስጥ ፲ እንመልከት።
፩፦ ነጭ ሽንኩርት ለጤና
አሊሰን የተባለ ለጤና ጠቃሚ የሆነ ንጥረ ነገር ይዟል በተለይ ከጥንት ግሪክ፡ ግብፅ፡ ባቢሎን ጀምሮ ነጭ ሽንኩርት በጥሬው በመመገብ ጤናቸውን ይጠብቁ ነበር።
፪፦ ነጭ ሽንኩርት አንደ አልሚ ምግብ
ነጭ ሽንኩርት ከፍተኛ የሆነ አልሚ ምግብ ቢሆንም ትንሽ መጠን የሆነ የካሎሪ (calories) ይዙአል
28 ግራም ነጭ ሽንኩርት
~ ማግኒዝየም 23%
~ ቫይታሚን ሲ 15%
~ ሌሊዬም 6%
~ ፋይበር 1 gram
፫፦ ነጭ ሽንኩርት በሽታን በመከላከል፦
ጥናቶች አንደሚያመለክቱት በቀን 2.56 ግራም መመገብ የጉንፋን በሽታ በሰውነታችን ላይ የሚቆይበትን ቀናት በመቀነስ የመያዝ እድላችን ይቀንስልናል።
፬፦ ነጭ ሽንኩርት የደም ግፊትን ለመከላከል
የልብ ችግር፣እራስን መሳት፣የደም ግፊት እነዚህ በአለማችን ላይ በገዳይነታቸው የሚታወቁ በሽታወች ናቸው።
ነጭ ሽንኩርት አዘውትረው የተመገቡ ሰወች ከለሌቹ የተሻለ ሁኔታ የደም ግፊት በሽታ መከላከል ችለዋል።፭፦ ነጭ ሽንኩርት በደማችን ውስጥ ያለውን ቅባት ለመቀነስ
በሰውነታችንው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል( cholestrol ) መጠን ያለባቸው ሰወች ነጭ ሽንኩርት በመመገብ ከ10~15% መቀነስ ይችላሉ።
፮፦ ነጭ ሽንኩርት እንደ አንቲ ኦክሲዳንቴ
ከዚህም በተጨማሪም የመርሳት በሽታ (alzheimer) እንዲሁም እራስን የመሳት በሽታ (Dermetia) በሽታወች የመከላከል አቅም አለው።
የደማችንን ቅባት(Cholostrol ) እና የደም ግፊታች ከመከላከል በተጨማሪ የአንቲ ኦክሲዳንት ባህሪ አለው ፡ ይህ ደግሞ እንደየመርሳት ችግር እንዲሁም እራሳችንን እንዳንስት ይከላከልናል።
፯፦ ነጥ ሽንኩርት ለረዝም እድሜ
መቸም እድሜያችንን ለመጨመር በሰው እንደማይቻለን ሁላችንንም እናቃለን ነገር ግን ለሞት ሊዳርጉን የሚችሉ በሽታወች እንደ ደም ግፊት፣ የልብ በሽታ፣ ተላላፊ ለሆኑ በሽታወች በመከላከል ጤናችን ጠብቆ እረጂም እድሜ እንድኖር ያረገናል።
Posted on 07-24-17, 09:53 pm


Karma: 100
Posts: 264/610
Since: 08-27-16

Last post: 52 days
Last view: 1 day
የአራዳ፡ልጅ፡ሰለጥቅሙ፡በደንብ፡አቅርቦታል።
በእኔ፡የደረሰብኝን፡ለማሳሰብ፡የምፈልገው፡
ጉንፋን፡ይዞኝ፡ነጭ፡ሽንኩርት፡ብላበት፡ብለውኝ፡
ተቃጥዬ፡ልሞት፡ደረስኩኝ።
ዘዴው፡ጉንፋን፡ከያዘ፡በኋላ፡ሳይሆን፡ገና፡በአቅማሚያው፡
ላይ፡መሆን፡አለበት።
Pages: 1