ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Surprising Things ገራሚ ነገሮች . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-22-17, 02:54 am (rev. 1 by Ye Arada Lij on 07-22-17, 11:50 pm)


Karma: 90
Posts: 487/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
በአንድ ወቅት የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ንጉሱን እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል “ለመሆኑ ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? ”
እርሳቸውም ቆፍጠን ባለ አነጋገር “ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ትህትና ነው” አሉት።
ጋዜጠኛውም ቢሆን የዋዛ አልነበረምና “ይቅርታ ያድርጉልኝ ጃንሆይ ይሄ ሃምብልነስ እና ፕራውድነስ የሚሉት ነገር እርስ በርሱ የሚጣረስ ማንነት አይመስልዎትም?” የሚል ጥያቄ ያስከትላል።
ንጉሱም እንዲህ አሉ “አየህ አንድ በጣም ተራ የምትለው ገበሬ ቤት በእንግድነት ብትሄድ ያለውን አብልቶ፤ እግርህን አጥቦ፤ ያጠበውን እግርህን ስሞ፤ አልጋውን ላንተ ለቆ እርሱ ግን መሬት ላይ ይተኛል። በዚያው ልክ በሚስቱ፣ በርስቱና በሃገሩ ላይ ብትመጣበት ደግሞ በግንባርህ ላይ ጥይት ይቆጥርልሃል፤ ስለዚህ አይጋጭም፤ ነገር ግን ይሄንን ነገር ለመረዳት አንተ ራስህ ኢትዮጵያዊ መሆን አለብህ” ነበር ያሉት።
ኢትዮጵያዊነትን ለመረዳት ኢትዮጵያዊ መሆንን ይጠይቃል፤ ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነውና!!!
Pages: 1