ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing አማርኛ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-19-17, 11:16 pm


Karma: 90
Posts: 478/840
Since: 02-29-16

Last post: 32 days
Last view: 32 days
1. ትላንት ኮሶ ጠጣሁ ዛሬ መረረኝ፤
እስቲ አራዳ ልውጣ ብርቱካን ባገኝ።
ሰም......
ወርቅ.....

2. ይህችን ሙሽራ አታይዋትም ወይ፤
መርገፏን ደርባ በጥበቧ ላይ።
ሰም......
ወርቅ.....

3. ያባቴን አገር ደጋውን፣
ባስከለክለው ሣሩን፣
አበሉት አሉ ዘመዶቼ፣
እርሻ ማረጌን ትቼ።
ሰም......
ወርቅ......
Posted on 07-20-17, 11:59 am


Karma: 100
Posts: 247/603
Since: 08-27-16

Last post: 34 days
Last view: 7 hours
1. ትላንት ኮሶ ጠጣሁ ዛሬ መረረኝ፤
እስቲ አራዳ ልውጣ ብርቱካን ባገኝ።
ሰም......የሚበላው፡ፍሬ
ወርቅ.....ወይዘሪት፡ብርቱካን፡ወይም፡የበረታ፡ካህን፡

2. ይህችን ሙሽራ አታይዋትም ወይ፤
መርገፏን ደርባ በጥበቧ ላይ።
ሰም......ያጌጠ፡ካባ፡
ወርቅ.....መሞቷ፡

3. ያባቴን አገር ደጋውን፣
ባስከለክለው ሣሩን፣
አበሉት አሉ ዘመዶቼ፣
እርሻ ማረጌን ትቼ።
ሰም......ሣሩን፡ለግጦሽ፡ሰጡት፡
ወርቅ....ክብርናዬ፡ገበሬነቴ
Pages: 1