ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 07-16-17, 03:29 am


Karma: 100
Posts: 84/94
Since: 08-19-16

Last post: 268 days
Last view: 75 days
ሙቀጫ
-------
ሙቀጫ ማለት ምን ማለት ነው?

- ሙቀጫ ማለት ለምግብነትና ለመጠጥነት ለምናዘጋጃቸው ጥሬ እቃዎች

1. አድቅቆ ለመውቀጥ
2. የቅባት እህሎችን ቅባታቸውን እስከሚተፉ ድረስ ለጥልጦ ለመውቀጥ
3. ለመሸክሸክ ማለትም ገለባ ያላቸው እህሎች ገለባቸው እንዲለቅ ለማድረግ
4. እርጥብ ቅመሞችን ለመደለዝ
5. ለመለንቀጥ
6. እርጥብና ደረቅ ምግቦችን አንድ ላይ ለማቀላቀል የሚጥቅመን ባህላዊ መሳሪያ ነው

መውቀጫው የሙቀጫ ግልገል ወይም ዘነዘና በመባል ይጠራል

ሙቀጫው የሚወቀጠውን ጥሬ ነገር የሚይዝ ሲሆን የሙቀጫ ግልገል ወይም ዘነዘናው ግን በሰው ሀይል አማካይነት ለመውቀጥ የሚጠቅም መሳሪያ ነው

የሙቀጫው መጥን እንደ ተጠቃሚው ሰው ፍላጎት ይወሰናል ምክንያቱም ከትንሽ እስከ ትልቅ ሙቀጫ መስራትም ሆነ መግዛት ይቻላል

ሙቀጫን በአብዛኛው ከማይሰነጠቅና ከማይፈረፈር እንጨት እንደ ወይራና ዝግባ ወዘተ... ከመሳሰሉት የዛፍ እንጨቶች ይሰራል

በተጨማሪ ለሙቀጫ የሚሆን ድንጋይ ተመርጦ ከድንጋይና ከእብነበረድ ይሰራል

በሙቀጫው ከተጠቀማችሁ በኋላ አጥባችሁ በማስቀመጥ ለምትፈልጉት ስራ በቀላሉ ልትጠቀሙበት የምትችሉት መሳሪያ ነው

ዘመናዊ ሙቀጫ ወይም መፍጫ ባልነበረበት ዘመን ይህን ባህላዊ ሙቀጫ ፈጥረው እና ሰርተው እንድንጠቀምበት በማድረግ ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ ስላሸጋገሩን ሳላስታውሳቸውና ሳላመሰግናቸው አላልፍም
Posted on 07-16-17, 10:03 am


Karma: 100
Posts: 232/610
Since: 08-27-16

Last post: 80 days
Last view: 20 hours
Pages: 1