ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Education - ትምህርት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-15-17, 07:22 pm


Karma: 90
Posts: 472/879
Since: 02-29-16

Last post: 34 days
Last view: 34 days
የብርሃን ባሕሪና የሚጓዝበት ፍጥነት
ብርሃን በዓይን ሊታይ የሚችል የኤሌክትሮ መግነጢስ ጨረራ ዓይነት ነው። የአንድ ኤሌክትሮመግነጢስ ማዕበል ሞገድ ርዝመት በ380-400 እና በ760-780 ናኖ ሜትሮች መካከል ከወደቀ ብቻ በዓይን ይታያል። ከዚያ ካነሰ ወይም ከበለጠ ለዓይን አይታይም፤ ለምሳሌ ማይክሮዌቭና ኤክስሬይ ቢኖሩም በዓይን አናያቸውም። የኮረንቲና ማግኔት ማዕበልን ተሸክመው የሚርገበገቡ ነገሮች ፎቶን ሲባሉ ክብደት የሌላቸው እኑስ (ፓርቲክል) ናቸው። ባጠቃላይ መልኩ ብርሃን እኑስ ብቻ ወይንም ሞገድ ብቻ ሳይሆን የሞገድና እኑስ ሁለትዮሽ ተፈጥሮን በተዋህዶ የያዘ ነው። ስለነዚህና ስለመሳስሉት መሰረታዊ የብርሃን ባህርያት የሚያጠናው የዕውቀት ዘርፍ ሥነ ብርሃን (ኦፕቲክስ) በመባል ይታወቃል።
የብርሃን ፍጥነት
ብርሃን የሚጓዘው ከመቅጽበት ሳይሆን በውሱን ፍጥነት እንደሆነ በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ እንዲሁም በተጨባጭ ሙከራዎች ተረጋግጧል። ለመጀመሪያ ጊዜ የብርሃንን ፍጥነት በተሳካ ሁኔታ በ1676 ዓ.ም. የለካው የዴንማርክ ሰው ሮመር ነበር። ከእርሱ በኋላ የተለያዩ ሳይንቲስቶች በሂደት በሚሻሻል መንገድ ፍጥነቱን ለክተዋል። በአሁኑ ዘመን የሚሰራበት የብርሃን የኦና ውስጥ ፍጥነት 299,792,458 ሜትር በሰከንድ ነው። በሌላ አነጋገር አንድ የብርሃን ጨረር በያንዳንዷ ሰከንድ ወደ ሶስት መቶ ሺህ ኪሎ ሜትር (300 ሺህ ኪሎ ሜትር) የሚጠጋ ርቀት ይጓዛል። ይህ የጠፈር ውስጥ ፍጥነት በ “c” ምልክት ሲወከል፣ ለተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው የተፈጥሮ ቋሚ ቁጥር ነው። በዚህ ላይ በተመሰረተ ስሌት መሰረት ብርሃን ከፀሐይ ተነስቶ ወደ ምድራችን ለመድረስ ከስምንት ደቂቃ በላይ ይፈጅበታል፤ ይህ ማለት ፀሐይ ድርግም ብላ በድንገት ብርሃኗ ቢጠፋ፣ ልክ ከጠፋችበት ጊዜ ጀምሮ ለስምንት ደቂቃዎች ያህል ምን እንደሆነች ሳናውቅ ብርሃኗ እኛ ዘንድ ይደርሳል ማለት ነው፡፡ ብርሃኑ የሚጓዘው ርቀት ደግሞ በአማካኝ ወደ 150 ሚሊየን ኪሎ ሜትሮች ነው፡፡ ብርሃን፣ ከኦና ወጥቶ በቁስ አካል ውስጥ (ለምሳሌ ብርጭቆ፣ ውሃ፣ አየር) ሲጓዝ ፍጥነቱ ይቀንሳል። የዚህ ቀስተኛ ፍጥነት መጠን በቁሱ ዳይኤሌክትሪክ ባህርይና በብርሃኑ አቅም ይወሰናል።
እኔ ሳይንሳዊ ሀሳቦች ደስ ይሉኛል የሚል ሼር ያድርግ `sharing is happiness`


ምንጭ - survival 101 info

Pages: 1