ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing General Healthcare . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-14-17, 09:18 pm


Karma: 100
Posts: 298/426
Since: 07-12-15

Last post: 7 days
Last view: 7 days
ኩላሊትዎን ሊጎዱ የሚችሉ 7 ሁኔታዎች

1. በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ - በቂ ውሃን አለመጠጣት የኩላሊት ሥራ የሆነውን አላስፈላጊ ቆሻሻን ከሰውነታችን ማስወገድ በሚገባ እንዳያከናውን ስለሚያደርግ ቆሻሻው በኩላሊታችን ውስጥ ተከማችቶ ጉዳት እንዲያስከትል ያደርጋል፡፡

2. የውሃ ሽንትን መቋጠር - የውሃ ሽንትን ማስወገድ በሚገባን ጊዜ ሳናስወግድ የምንይዘው ከሆነ እና ይህን ተግባር የምናዘወትር ከሆነ የሽንት ፊኛችንም ሆነ ኩላሊታችንን አደጋ ላይ የምንጥል መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡

3. ጨው የበዛበትን ምግብ መውሰድ - ጨዋማ ምግቦችን መመገብ የኩላሉትን ጨውን (sodium) ከሰውነታችን የማስወገድ ሥራ ጫና እንዲበዛበትና ሲቆይም ለችግር እንዲጋለጥ ያደርጋል፡፡

4. ካፊን በብዛት መውሰድ - በሚጠማን ጊዜ ውኃ ከመጠጣት ይልቅ ለስላሳ መጠጦችን እንደ ጥም ቆራጭነት እንጠቀማለን፡፡ ካፌን የደም ግፊት መጠናችንን በመጨመር ኩላሊትን ይጎዳል፡፡

5. ሕመም ማስታገሻ አለአግባብ መውሰድ - ቀላል ለሚባል የሕመም ስሜት ሕመም ማስታገሻዎችን መውሰድ አላስፈላጊ እና አልፎ ተርፎም ከባድ የሆነ የኩላሊት ጉዳትን ሊያደርስ ይችላል፡፡

6. የአልኮል መጠጥን በብዛት መጠጣት - ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥን ማዘውተር የኩላሊት ችግር ያስከትላል፡፡

7. ሲጋራ ማጤስ - ለኩላሊት መድረስ የሚገባውን የደም መጠን ስለሚቀንስ ሲጋራ ማጤስ እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡

source - Maderetena & Dr. Honeliat

Posted on 07-15-17, 01:36 pm


Karma: 100
Posts: 229/610
Since: 08-27-16

Last post: 22 days
Last view: 10 days
Pages: 1