ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Computing. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 07-12-17, 05:24 pm


Karma: 90
Posts: 468/879
Since: 02-29-16

Last post: 33 days
Last view: 33 days
---ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች!--
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው? ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች!
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር አስቀምጠንላችዋል፡፡
1.➡የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፤ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፡፡በዋጋም ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ የሆን
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻልም
ይነገርለታል፡፡
2.➡የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደ የስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡ ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3.➡ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4➡.ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6➡.የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080 የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7➡.የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8➡. ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
• ከመለዋወጫ አንፃር በሃገራችን Toshibaን የሚያክል
ላፕቶፕ የለም፡፡ከተበላሸ እና እክል ካጋጠመው በተመጣጣኝ
ዋጋ መለዋወጫ ማግኘት ይቻላል፡፡ Acer ላፕቶፕም የተሻለ
መለዋወጫ አለው፡፡
• ከጥራት አኳያ ደግሞ APPLEን የሚደርስ የለም፡፡ HP እና
DELLም የተሻሉ ብራንዶች ሆነው መለዋወጫ ግን እንደልብ
ማግኘት አይቻልም፡፡

Posted on 07-13-17, 06:26 pm


Karma: 100
Posts: 219/610
Since: 08-27-16

Last post: 48 days
Last view: 6 days
Great!

በአዲሱም፡ሆነ በዱሮው፡ላፕቶፕ፡
የአማርኛውን፡ፊደል፡ለመጠቀም፡
Thanks to Dr. Abera Mamo ከዚህ፡
http://freetyping.geezedit.com
ጎራ፡ይበሉ።
Posted on 07-13-17, 11:04 pm


Karma: 95
Posts: 588/850
Since: 07-22-15

Last post: 53 days
Last view: 5 days
Waw thanks bro yedrow laptopEan endaltlew sleredahegn lol
Posted on 07-14-17, 08:22 am


Karma: 100
Posts: 225/365
Since: 07-14-15

Last post: 211 days
Last view: 211 days
Tn'x Bro
Pages: 1