ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Relationship - ግንኙነት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-11-17, 07:04 am


Karma: 90
Posts: 463/879
Since: 02-29-16

Last post: 92 days
Last view: 92 days
ሚስት ባልዋ ከስራ ወደ ቤት ሲመጣ ትንሽ ልታናድደው ታስብና እጥር ምጥን ያለች
ደብዳቤ ፅፋለት አልጋ ላይ አስቀምጣለት አልጋው ስር ትደበቃለች።
ባል በስራ የደከመ ሰውነቱን እየጎተተ ወደ ቤቱ ገብቶ ሚስቱን ሲጠራት አቤት የሚለው በማጣቱ ተኝታ ይሆናል ብሎ ወደ መኝታ ቤት ሲገባ... ሚስቱ የፃፈችለትን
ደብዳቤ ያገኛል። ደብዳቤው እንዲ ይላል፦ " ሌላ ሰው ስለወደድኩ ካሁን በዋላ ካንተ ጋር መኖር ስለማልፈልግ ቤቱን ትቼልህ ሄጃለው" ይላል...ባል ሆዬ ወዲያው ፈገግ
ይልና ስልኩን አውጥቶ ደወለ፦
✆ "ሀይ የኔ ቆንጆ
እንደነገርኩሽ ያቺ ጅል ሚስቴ በራሱዋ ጊዜ ትታኝ
ሄደች.....ደስ
አይልም? መጣው ጠብቂኝ"
ብሎ
ስልኩን ዘግቶ ከቤት
ይወጣል።
ይሄን ጊዜ ሚስት ብሽቅ ብላ አያነባች
ከተደበቀችበት ስትወጣ አልጋው ላይ ሌላ ደብዳቤ
ታገኛለች፤ እንዲ ይላል:-
"የኔ ማር አልጋ ስር እንደተደበቅሽ
አውቂያለው ፤ አሁን ወተት ገዝቼ እስክመጣ ቆንጆ ራት
ሰርተሽ ጠብቂኝ....እወድሻለው የኔ ቆንጆ" ይላል።
እግዚአብሔር እንደዚህ አይነቱን ትዳር ይስጠን !!!!!

Posted on 07-11-17, 10:57 am


Karma: 100
Posts: 213/614
Since: 08-27-16

Last post: 2 days
Last view: 1 day
እኔ፡እንደዚህ፡አይነት፡ጠባይ፡አይገባኝም።
ባልየው፡ከኔ፡የተሻለ፡ሰው፡ነው፡በዚህ፡ቀልድ፡የለም።
ሴትዮዋ፡ለምን፡ያልመሰለ፡ያልሆነ፡ነገር፡ታደርጋለች።
አንደዚሁም፡አንድ፡ቀን፡ባልና፡ሚስት፡ሲጨቃጨቁ፡ባልየው፡
እንግዲህ፡ሴይጣኔን፡አታስመጭብኝ፡ሲል፡ሴጣኑ፡ጠራችሁኝ፡
እንዴ፡ብሎ፡ገጭ፡አለ፡ይባላል።
ይሄ፡በእሳት፡መጫወት፡ነውና፡መቃጠል፡አይቀርም።
ከብት፡ካልዋለበት፡ኩበት፡ለቀማ።
Posted on 07-11-17, 11:40 pm


Karma: 90
Posts: 464/879
Since: 02-29-16

Last post: 92 days
Last view: 92 days
ልክ ብለሃል ከተደጋገመ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል
Pages: 1