ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-08-17, 11:08 pm


Karma: 100
Posts: 82/94
Since: 08-19-16

Last post: 268 days
Last view: 75 days
የሽሮ እርጥብ ቅመም
----------------

አስፈላጊ ነገሮች
------------

1. ነጭ ሽንኩርት
2. ዝንጅብል
3. ቀይ ሽንኩርት
4. ጤናዳም ፍሬ
5. በሶ ብላ
6. ጦስኝ
7. መክተፊያ
8. ቢላ
9. ወንፊት

አሰራሩ
------

ነጭ ሽንኩርትን በሶስት መንገድ ልጣችሁ ከገለባው ወይም ከልጣቹ መለየት ትችላላችሁ

1. መጀመሪያ ነጭ ሽንኩርቱን ፈልፍላችሁ ጨርሱና በውስጡ ያሉትን አላስፈላጊ ነገሮች ለዩና አስወግዱ
በመቀጠል በቀላሉና በፍጥነት ለመላጥ እንዲረዳ በጎድጓዳ ዕቃ ውስጥ አድርጉና በቀዝቃዛ ውሃ እስከሚርስ ዘፍዝፉት መራሱን ስታረጋግጡ ሁሉንም ልጣችሁ ጨርሱ እንዲጠነፍፍ ወንፊት ላይ አድርጉት

በወንፊቱ ገልበጥ ገልበጥ በማድረግ ውሃው መጠንፈፉን አረጋግጡ:: ሽንኩርቱን ከገለባው ለዩት እንደገና እጠቡና ጠንፈፍ እንዲል አድርጉት

ለመደለዝ ወይም ለመውቀጥ እንዲመች ትልልቁን መርጣችሁ ገርደፍ ገርደፍ አድርጋችሁ ክተፉት ከዛም ሁሉንም በአንድ አስቀምጡት

2. መክተፊያ ላይ እያንዳንዱን ነጭ ሽንኩርት በማስቀመጥ በቢላው ሰፊ ክፍል በመጫን ሲጨፈለቅ ቆዳውን ለይታችሁ መጣል

3. በደረቁ በቢላ አማካይነት ሽንኩርቱን ልጦ ማዘጋጀት ይቻላል

አሁን በተመቻችሁ መንገድ ነጭ ሽንኩርቱን አዘጋጅታችሁ ጨረሳችሁ ማለት ነው

የሚቀጥለው ዝንጅብሉን መጀመሪያ መልጭ አድርጋችሁ እጠቡት ልጣጩን በቢላ ላጡና ጨርሱ አሁንም እጠቡት ከዛም ወንፊት ላይ ጠፈፍ እንዲል አቆዩትና ገርደፍ ገርደፍ አድርጋችሁ ከትፋችሁ አዘጋጁት

ቀይ ሽንኩርት ልጣችሁ አጥባችሁ ገርደፍ ገርደፍ አድርጋችሁ በመክተፍ አዘጋጁት
-----------

ጤናዳሙን ፍሬውን ለይታችሁ በመንቀጠንስ አጥባችሁ አዘጋጁት
--------

በሶብላውን ፍሬውንና ቅጠሉን አንድ ላይ በመሸምጠት ከጨረሳችሁ በኋላ በጠቅጣቃ ወንፊት ላይ አድርጋችሁ ፍሬው እንዳይባክን ቀስ ብላችሁና ተጠንቅቃችሁ እጠቡና በወንፊቱ
--------- ገልበጥ ገልበጥ እያረጋችሁ ውሃውን እንዲያጠነፍፍ አድርጉት

የሚመቻችሁ ከሆነ ሳይሸመጠጥ እስከነዛላው እጠቡና በኋላ ሸምጥጡት በዚህ መንገድ አዘጋጁና አስቀምጡ

ጦስኙን ቅጠል ቅጠሉን ቀንጥሳችሁ በመጨረስ አጥባችሁ በወንፊት በማጥለል አዘጋጁት
------

ስድስቱንም እርጥብ ቅመሞች አንድ ላይ በመቀላቀል መደለዝ ወይም መለንቀጥ በሚችል ማሽን ካልተቻለም በባህላዊ ሙቀጫ መውቀት ወይም ፈጭታችሁ ማዘጋጀት አለባችሁ

በሙቀጫ ከሆነ በቀላሉ ነጭ ሽንኩርቱ ስለማይጨፈለቅ ጊዜ ወስዶ መውቀጥ ያስፈልጋል

ይህ የተዘጋጀ ቅመም ከተዘጋጀ የሽሮ ክክ ጋር አንድ ላይ በመደልዝ አድርቆና ሌላ አስፈላጊ ደረቅ ቅመሞችን ጨምሮ በማስፈጨት ሽሮን ማዘጋጀት ይቻላል

ማሳሰቢያ
-------
- ቅመም ከሚበዛ ቢያንስ ይሻላል
Pages: 1