ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 07-08-17, 08:55 pm (rev. 1 by  ማማዬ on 07-08-17, 11:09 pm)


Karma: 100
Posts: 81/94
Since: 08-19-16

Last post: 268 days
Last view: 75 days
የሽሮ ደረቅ ቅመም
---------------
የሚያስፈልጉ ነገሮች
----------------
1.በሶ ብላ
2. ነጭ አዝሙድ
3. የኮረሪማ ፍሬ
4. ጦስኝ
5. ጥምዝ
6. ድንብላል
7. ጨው
8. ወንፊት
9. ሰፌድ
10. ማመሻ ምጣድ
11. መጋፊያ ዕቃ
12. መቁያ

አሰራሩ
------
- ከጨው በስተቀር ሁሉንም ቅመሞች ስትገዟቸው ንፅህናቸውን ዓይታችሁ ይሁን
መጀመሪያ ቅመሞቹን እያንዳንዳቸው ለይታችሁ ንፁህ እስከሚሆኑ ድረስ ደጋግማችሁ እጠቧቸው:: ፈሰው እንዳይባክኑ ተጠንቅቃችሁ ጠቅጣቃ ወንፊትን በመጠቀም በደንብ ውሃው እስከሚያልቅ አጥባችሁ ባላችሁ ትሪ መሰል ማድረቂያ ዕቃ ላይ በማድረግ ፀሀይ ላይ አስጡት:: ቦታው ቆሻሻ የማይደርስበት መሆን አለበት

ቶሎ እንዲደርቅ አስጣጡት መድረቁን ስታረጋግጡ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰፌድ ከሌለ በትሪ በማበጠር ከቅመሙ ውጪ የሆኑ ያላስፈላጊ ነገሮች ለዩና ጣሉ:: አልለይ ያሉ ደቃቅ ነገሮች ካሉ በድጋሚ በወንፊት ንፉት

መጀመሪያ ቅመሞችን የምታጥቡበት ምክንያት ሲታጠብ የሚሟሙ አፈሮችንና በውሃ ላይ የሚንሳፈፉ አላስፈላጊ ነገሮችን በቀላሉ ጊዜ ሳይወስድ ማፅዳት እንዲቻልና በበለጠ በንፁህ ለማዘጋጀት ሲባል ነው

በዚህ መልክ ያዘጋጃችኋቸውን ቅመሞች እያንዳንዳቸው ለየብቻ በጣም ባልሰማ ምጣድ ወይም ሌላ ማመስ በሚችል ዕቃ እንደ ቆሎ ጣ፣ ጣ እንዳይል በመጠንቀቅ አምሱት። በመቀጠል በማውጣት እንዲቀዘቅዙ አድርጉና ሲቀዘቅዙ ለየብቻ ንፁህና ክዳን ባለው ዕቃ ደረቅና ንፁህ ቦታ አስቀምጡት

በምግብ ላስቲክም ቋጥሮ ማስቀመጥ ይቻላል

ይህንን ደረቅ ቅመም የተደለዘ የሽሮ ክክ ላይም ሆነ ያልተደለዘ የሽሮ ክክ ላይ እንደ አስፈላጊነቱ ጨምሮ እንዲሁም ከተፈለገ ጨውም ጨምሮ አስፈጭቶ ሸሮን ማዘጋጀት ይችላል

ማሳሰቢያ
--------
- ቅመም መብዛት የለበትምPages: 1