ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Relationship - ግንኙነት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-07-17, 05:05 am


Karma: 100
Posts: 181/760
Since: 03-20-17

Last post: 18 days
Last view: 2 days
" የኔ ብቻ እንዲሆን "
ቃል ገብተህ ነበረ ላልለይሽ ብለህ
ጥለከኝ ላትሄድ በፈጣሪ ምለህ
ከእኔው ጋር ልትኖር በህይወት ዘመንህ
እስከመጨረሻ እስከ እልፈት ህይወትህ
ከኔ ሌላ ላታይ ላይታዘዝ አይንህ
,,
ምለክልኝ ነበር
,,
ጥዬሽ የሄድኩ ዕለት ቁሜ ሰው አይየኝ
ካልጋየም አልውረድ ጠያቂ አይጠይቀኝ
ብርዱ ይበርታብኝ ቆፈኑም ይግረፈኝ
ዶፉ ይውረድብኝ ውሽንፍሩ ይምታኝ
,,
ምለከልኝ ነበር
,,
አንቺን ያስከፋሁ ለት
መራመድ ያቅተኝ እግሮቼ ያንክሱ
ማየት ይሳናቸው አይኖቼም ይፍሰሱ
ምለክልኝ ነበር በፍቅር ፊት ብለህ
ቃሉን ልታከብር ጥለከኝ ላትሸሽ
,,
ግና ወዴ ትተከኝ ሸሽተሻል
እኔን አሳዝነክ አስከፍተከኛል
የፍቅር ቃልህን ማሀላህን ክደሀል
አንተቺን ያስከፋሁ ቀን
ብለህ መማልህን ከቶ ዘንግተሀል
,,
ፍቅሬ እንደመሃላህ እግሮችህ ያንክሱ
ማየት ይሳናቸው አይኖችህ ይፍሰሱ
ውሽንፍር በላይህ ዶፉ ያባሩብህ
ብርዱ ይበርታብህ ቆፈኑ ይግረፍህ
ካልጋም አትውረድ ህመም ያሰቃይህ
የሚቀርብህ ይጥፋ ሰው ሁሉ ይራቅህ
,,
ሁልግዜ እየመጣሁ እኔ እንድጠይቅህ
ማንም ሳይነካብኝ የግሌ እንዳደርግህ

Pages: 1