ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 6 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 07-07-17, 03:39 am


Karma: 100
Posts: 180/751
Since: 03-20-17

Last post: 2 days
Last view: 2 days
"ስለ ውበቷ ሳስብ፣ ቀኑ መሽቶ ይነጋል፡፡"

-

(ችግሩ ሲነጋ ነዋ! ጣጣው ያንን ኦሪጂናል ፊቷን በጧት ሳየው ነዋ!)

-

-

______________________________________

ሜካፕ/ ዊግ/ ቻክ/40-60 አርቲ ቡርቲ የማታበዛ፣ የተፈጥሮ ውበቷን የምትንከባከብን ሴት የመጥበስና የማግባት አስሩ ጥቅሞች፡፡

✿ ❀ ✿ ❀ ✿

1- ኮንፊደንስ አላት፡፡ በሰውነቷ፣ በተፈጥሮዋ፣ በአፈጣጠሯ insecure አይደለችም፡፡2- በሰው ፊት አታሳቅቅህም፡፡ ዘነጥኩ ብላ ቡጭራሬ መስላ አንገትህን አታስደፋህም፡፡3- ደደብ አይደለችም፡፡ የሚያምርባትንና የማያምርባትን ታውቃለች፡፡ ለምርጥ ዘር ትሆናለች፡፡4- ስትኳኳል፣ ስትለብስ ስታወልቅ፣ ስታነሳ ስትጥል፣ ስትመራርግ ቀኑንና ሰዓቱን እየፈጀች አንጀትህን አታሳርረውም፡፡ She knows that simplicity is the ultimate sophistication.5- ብኩን አይደለችም፡፡ ብሯን/ብርህን እንዲህ ጭራቅ ለሚያስመስላት አርቴ ኮስሜቲክስ ኢንደስትሪ የምትገብር፣ ዥልጥ ጅራሬ አይደለችም፡፡6- ትወዳታለህ፡፡ መልኳ ጧትና ማታ ስለማይቀያየር ውበቷና መልኳ ሠርክ consistent ነው፡፡ ሲነጋ ፊቷ ጉማሬ ፊት ስለማይሆን ቀንህን ደስ ብሎህ ትጀምራለህ፡፡ እናም ሰብኮንሸስህ ሳይታወቀው ይወዳታል፡፡7- ሐጢያት ትቀንሳለህ፡፡ እንደ ጠንቋይ ውሽማ ቋጯቋ ፊት መስላ ተኳኩላ አምሮብኛል ወይ ፍቅር ስትልህ አዎን ማሬ ብለህ በመዋሸት ፈጣሪህን አታሳዝንም፡፡8- ክላስ አላት፡፡ በትንንሽ ነገር የምትዋብ ተፈጥሮአዊ ሴት፣ ጨዋ ቤተሰብ ያሳደጋት የጨዋ ልጅ ናት፡፡8- Pro የተፈጥሮ ውበት ሴቶች ሰላምህን ይሰጡሃል፡፡ ዬል ዩንቨርሲቲ ከማሞ ክራንቻ አጠቃላይ የድለላ ስራ ድርጅት ጋር በመተባበር ያደረጉት ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ፣ ቡጭራሬያም ተኳኳይ ሴቶች ጨቅጫቃ፣ ጯሂና ዓይነ-ጉርጥርጣም ናቸው፡፡9- አታቀዣብርህም፡፡ የልደቷ ቀን ለት በስጦታ ያንበሻበሽካት፤ "ሆዴ - ማሬ - እናቴ - እኔ ያላንቺ ትቢያ ነበርኩ" ምፅ! ምፅ! እትት ግትት ናሬሽንህን እያደራህላት "አረጀሁ እኮ!" ብላ ሙድህን አትጦልበውም፡፡10- ተፈጥሮአዊ ሴት ጥልቅ ናት፡፡ ከቀለም ቅብ የላቁ አስደሳችና አስወዳጅ ነገሮችን ስለምታውቅ፣ ላንተ ሁሌም ውብ ናት፡፡

❀ ✿ ❀ ✿

(እናም እንዴት መሰለሽ እታበባዬ፣ "A smile is the best make up any girl could ever wear")

-

Pro ተፈጥሮ ሴቶች ይለምልሙ!!!.

______________________________________

Pages: 1